ዶናልድ ትራምፕ ከሳውዲ ዓረቢያ እና ከግብፅ ጋር በክርስቲያን ኢትዮጵያ ላይ ስላሴሩ ተረግመዋልን?


✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

👨‍⚖️ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በታሪካዊው የክስ ሂደት በቀረቡባቸው ክሶች በጠቅላላ ጥፋተኛ ተባሉ። ፕሬዝዳንቱ ከንግድ መዝገቦች ማጭበርበር ጋር በተያያዘ በቀረቡባቸው 34 ክሶች በሙሉ ጥፋተኛ ተብለዋል።

በአሜሪካ ታሪክ በሥልጣን ላይ ያለም ይሁን ከሥልጣን የወረደ ፕሬዝዳንት በወንጀል ክስ ጥፋተኛ ሲባል ትራምፕ የመጀመሪያው ናቸው።

የጥፋተኝነት ውሳኔ የተላለፈባቸው ትራምፕ ሐምሌ ፲፩/11/፳፻፲፮/2016 ዓ.ም. የቅጣት ፍርድ ይተላለፍባቸዋል ተብሏል።

ፍርድ ቤቱ ስድስት ሳምንታት በዘለቀው ችሎት ላይ ከ22 ሰዎች ምስክርነትን ሰምቷል። ከእነዚህ መካከል የቀድሞ የልቅ ወሲብ ተዋናይት ስቶርሚ ዳንኤልስ ትገኝበታለች።

ዳንኤልስ ከትራምፕ ጋር የወሲብ ግንኙነት መፈጸሟን እና ከ፳፻፲፮/2016ቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በፊት ስለጉዳዩ ላለማውራት ተስማምታ ከትራምፕ ጠበቃ ፻፴/130ሺህ ዶላር መቀበሏን ገልጻለች።

እንግዲህ ይህ ምናልባት በአሜሪካ ታሪክ እጅግ ቅሌታም የሆነው ክስተት አስበውበትም ሆነ ሳያስቡበት ምናልባት ሁሉም በጋራ ካቀዱለት የእርስበርስ እና የዓለም ጦርነት ሤራ ጋር የሚቆራኝ ክስተት ሊሆን ይችላል። Thesis-Antithesis-Synthesis (ተሲስ ፣ ፀረ-ፀረስታ እና ውህደት/መደመር)።

እኛ ግን ደጋግመን እንደምንለው፤ የፋሺስቱ ጋላ-ኦሮሞ አገዛዝ፣ ህወሓት እና ሻዕቢያ በአክሱም ጽዮን ላይ የዘር ማጥፋት እንዲከፍቱ ትዕዛዝ፣ ፈቃድና ድጋፍ የሰጠችው ሃገር አሜሪካ ናት። በዚህም ተጠያቂዎቹ ፕሬዚደንቶች ዶናልድ ትራምፕ እና ጆ ባይደን ናቸው። ጦርነቱ መንፈሳዊ ነው፤ ኤዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ ይህን መንፈሳዊ ጦርነት እየተሸነፉ ስለሆነ በአዳም ዘር ላይ የዘር ማጥፋት ጦርነቱን እንደ በቀል አድርገው እየተጠቀሙበት ነው። ነገር ግን እግዚአብሔር አምላክ የበቀል እርምጃውን በሁሉም ላይ እየወሰደ መሆኑን እያየነው ነው።

የሉሲፈራውያኑን ተልዕኮ ለማሳካት ሲሉ በአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ እና ቤተ ክርስቲያኗ ላይ በጋላ-ኦሮሞዎቹ እና ኢ-አማኒያኑ ህወሓቶች አጋሮቻቸው ሥራ አስፈጻሚነት እየተሠራ ያለውን ዲያብሎሳዊ ሥራ ሁሉ እግዚአብሔር አምላክ መዝግቦታል። የተሠራው ወንጀል ሁላችንም ከምናስበው እና ከምናውቀው በላይ እጅግ በጣም የከፋ ነው። ገለልተኛ አጣሪ ቡድን እንዳይገባ፤ ብሎም ፍትሕና ተጠያቂነት እንዳይኖሩ ሁሉም በጋራ ጸጥ ብለው አዳዲስ አጀንዳ እየፈጠሩ ጊዜ ለመግዛት የሚሞክሩበት ምክኒያት ለዚህ ነው። አይይይ!

❖❖❖[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፹፫፤]❖❖❖

  • ፩ አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነውአቤቱ፥ ዝም አትበል፥ ቸልም አትበል።
  • ፪ እነሆ፥ ጠላቶችህ ጮኽዋልና፥ የሚጠሉህም ራሳቸውን አንሥተዋልና።
  • ፫ ሕዝብህን በምክር ሸነገሉአቸው፥ በቅዱሳንህም ላይ ተማከሩ።
  • ፬ ኑ ከሕዝብ እናጥፋቸው፥ ደግሞም የእስራኤል ስም አይታሰብ አሉ።
  • ፭ አንድ ሆነው በአንተ ላይ ተማከሩ፤ በአንተ ላይ ቃል ኪዳን አደረጉ፤
  • ፮ የኤዶማውያን ድንኳኖች እስማኤላውያንም፥ ሞዓብም አጋራውያንም፥
  • ፯ ጌባል አሞንም አማሌቅም፥ ፍልስጥኤማውያንም ከጢሮስ ሰዎች ጋር፤
  • ፰ አሦርም ከእነርሱ ጋር ተባበረ፥ ለሎጥ ልጆችም ረዳት ሆኑአቸው።

❖❖❖[ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ ፴፩፥፩]❖❖❖

ስለ እርዳታ ወደ ግብጽ ለሚወርዱ በፈረሶችም ለሚደገፉ፥ ስለ ብዛታቸውም በሰረገሎች፥ እጅግ ብርቱዎችም ስለ ሆኑ በፈረሰኞች ለሚታመኑ፥ ወደ እስራኤልም ቅዱስ ለማይመለከቱ እግዚአብሔርንም ለማይፈልጉ ወዮላቸው!“

✞✞✞[ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ ፩፥፳፫]✞✞✞

"አለቆችሽ አመጸኞችና የሌቦች ባልንጀሮች ሆኑ፤ ሁሉ ጉቦ ይወድዳሉ፥ ዋጋም ለማግኘት ይሮጣሉ፤ ለድሀ አደጉ አይፈርዱም፥ የመበለቲቱም ሙግት ወደ እነርሱ አይደርስም።"

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment