የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም.

✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም. ከ30 ሺህ በላይ የሚኾኑ ኢትዮጵያውያን፣ በፋሺስት ኢጣሊያ ጦር፣ ለሦስት ቀናት ባልተቋረጠ ግድያ፣ ሕይወታቸውን በግፍ አጥተዋል።

ሙሶሊኒ አሁንም እንደ በጣም ክፉ ግለሰብ ይታወሳል። በተለይ ኢትዮጵያን በግፍ ወይም በጭካኔ ለመያዝ የጣረ ሞኝ ወይም እብድ ሰው ነበር። በዘመናችንም እንደ ሙሶሊኒ የመሳሰሉ ሰዎች፡ በኢትዮጵያ በተለይ በጣልያንና ጀርመን ብቅ ብቅ በማለት ላይ ይገኛሉ። እንንቃ! በተለይ በሶማሊያና ሱዳን በኩል፡ ልክ በጣልያን ጊዜ እንደነበረው፡ በጣም ተንኮለኛ የሆነ ሴራ አሁንም ተጠንስሷል።

መሶሎኒ ከዓረቦችና ሶማሌዎች ጋር በመተባበር ነበር በ1929 ዓ.ም ቂሙን ለመወጣት ኢትዮጵያን የወረረው። ኢትዮጵያ ደግሞ ገና የሽግግር ወቅት ላይ የነበረች በመሆኑ የተደራጀ መንግሥት እና ጦር አልነበራትም። ፋሽስት ኢጣሊያ ደግሞ አሉ የተባሉ ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎችን መርዝ ከሚተፉ አውሮፕላኖች ጋር ይዛ ኢትዮጵያን ወረረች።

ወረራው የተደራጀ ስለነበር በቀላሉ ሊቀለበስ አልቻለም። ስለዚህ ንጉሠ ነገስቱ እዚሁ ሆነው የከፉ ነገር ከሚመጣ ወደ ውጭ ወጥተው መታገልን የዘመኑ ሹማምንቶች እንደ አማራጭ መከሩ። እናም ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ከመንበረ ስልጣናቸው ተነስተው ኢትዮጵያን ለቅቀው ወደ እንግሊዝ ተሰደዱ። ሀገር አልባ ሆኑ።

ኢጣሊያም የኢትዮጵያን መንግሥት ተቆጣጠረች። ሮም በደስታ ተቀጣጠለች። ኢትዮጵያዊያንን ደግሞ ለሁለት ተከፈሉ። አብዛኛው በአርበኝነት ተሰማራ። ቀሪው ደግሞ ለኢጣሊያ ፋሽስቶች ባንዳ ሆነ። አርበኞቹ ፋሽስቶችን ለመፋለም በዱር በገደሉ ተሰማሩ። ጦርነቱ በየፈፋው ይካሄድ ጀመር። ኢጣሊያ በመርዝ ጋዝ አባቶቻችንን፥ እናቶቻችችንና ልጆቻቸቸውን ሁሉ መፍጀት ጀመረች። በጣም ብዙ ሕጻናት፣ ሴቶችና እናቶች አረጋውያን አለቁ። በአንድ ዕለት፤ በየካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም ብቻ ከ30 ሺህ በላይ የአዲስ አበባ ነዋሪ በፋሽስቶች ተጨፈጨፉ።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment