የአመክንዮና የሕግ ጥያቄ ለአሸባሪው አገዛዝ ወያኔ/ኢሕአዴግ‼️

✍  ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

አሸባሪ ያው አሸባሪ ነውና ሕግና ሥርዓት አያውቅም ብየ ማለፍ ስላልፈለኩ ወይም ተጠያቂነታቸውን ለማረጋገጥ ነው ለአሸባሪው አገዛዝ ይሄንን ጥያቄ መጠየቅ የፈለኩት። በእርግጥ ጥያቄየ አዲስ አይደለም። ይሄው "secular ነኝ!" የሚለው አሸባሪው አገዛዝ ከsecular ሥርዓት በመውጣት የዋቄፈታ ወይም የዋቄፈና ባዕድ አምልኮ በዓል የሆነውን ኢሬቻን ስፖንሰር እያደረገ በድምቀት እንዲከበር ማድረግ ከጀመረበት ዐሥር ዓመታት በፊት ጀምሬ በተደጋጋሚ ያነሣሁት ጥያቄ ነው። ታሪክ መዝግቦት እንዲያልፍ ለማድረግ ጥያቄውን ዛሬም ሆነ ወደፊት ደጋግመን የምናነሣው ይሆናል‼
አስቀድሜ ግን ብዙዎቻቹህ የማታስተውሉትን ነገር መግለጥ እወዳለሁ። ፎቶዎቹ ላይ እንደምትመለከቱት ኢሬቻ የሚሉት የባዕድ አምልኮ በዓል በመጣ ቁጥር አገዛዙ ኢሬቻ የማይመለከታቸውን የጀግኖች አባቶቻችንን አደባባዮችና ሐውልቶችን ጨምሮ መላ አዲስ አበባን የሜዳ አህያ አስመስሎ የሚያዥጎረጉርበት ከላይ ጥቁር፣ መሀሉ ቀይና ከታች ነጭ ቀለም ያለው ጨርቅ አለ። ብዙዎቻቹህ ይሄ ጨርቅ አገዛዙ "የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ባንዲራ!" የሚለው ጨርቅ ይመስላቹሃል ግን አይደለም። ይሄኛው ጨርቅ ዋቄፈታ የሚባለው የባዕድ አምልኮ ጨርቅ ወይም ምልክት ነው። አገዛዙ "የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ባንዲራ!" የሚለው ጨርቅ ግን ቀለሙ ከላይ ጥቁር፣ መሀሉ ነጭና ከታች ቀይ ነው እንጅ ጥቁር፣ ቀይና ነጭ አይደለም። ቀለሞቹ ተመሳሳይ ቢሆኑም አደራደራቸው ግን በገለጽኩት መልኩ የተለያየ ነው‼
አሁን ወደ ጥያቄየ ልሻገርና ጥያቄየ ምን መሰላቹህ አሸባሪው አገዛዝ ርካሽ የፖለቲካ ቁማር ለመቆመር ሲል እከተለዋለሁ የሚለውን የsecular ሥርዓትን ሕግ ጥሶ በተለየ ሁኔታ ኢሬቻ የሚባለውን የዋቄፈታ ባዕድ አምልኮ በዓልን ከነኮተቱ ስፖንሰር በማድረግ በድምቀት እንዲከበር እያደረገ ባለበት ሁኔታ ያውም "ሕገመንግሥቴ!" በሚለው ሰነዱ ላይ ሳይቀር "ሰጥቻለሁ!" የሚለውን "ምንም ይሁን ምን ማንም የመሰለውን በነጻ የማምለክ መብት አለው!" በሚለው መብት መሠረት የፈለግነውን ብናደርግ ጣልቃ ሳይገባ መታቀብ ሲኖርበትና በሃይማኖታዊ ጉዳያችን ውስጥ ገብቶ ፈጽሞ "ይሄንን መያዝ ትችላላቹህ ይሄንን መያዝ አትችሉም!" ማለት በማይችልበት ሁኔታ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስታያን ዘፍ. 9፤8-17 ያለውን ቃለ እግዚአብሔር መሠረት በማድረግ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀዩን ቀስተ ደመና ወይም የቃልኪዳን ምልክት ቀደም ሲል የነበሩት የኢትዮጵያ መንግሥታት ሰንደቁን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ከማድረጋቸው ሽዎች ዓመታት በፊት ጀምሮ ቅድስት ቤተክርስቲያን የቃልኪዳን ምልክቷ አድርጋ ስትጠቀምበት የኖረችውን ይሄንን የቃል ኪዳን ምልክት ወይም ንዋዬ ቅዱስ የመጠቀም መብታችንን በመንፈግ ወይም በመግፈፍ በዓላትን በምናከብርበት ጊዜ ሁሉ ይሄንን የቃልኪዳን ምልክት የሆነውን ንዋዬ ቅዱስ እራሱንና ቀለሙን የሚጠቀሙ ሌሎች ንዋዬ ቅድሳቶቻችንን እንዲሁም አልባሳቶቻችንን ጭምር እንዳንገለገልበት ወይም እንዳንጠቀምበት የሚከለክልበት አመክንዮ እና ሕጋዊ አሠራር ምንድን ነው??? ለዋቄፈታ የባዕድ አምልኮ አምላኪዎች የተፈቀደ የመሰላቸውን በነጻ የማምለክ፣ የመጠቀምና ሥርዓት የመፈጸም መብት ለምንድን ነው እሱ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ሲሆን የሚከለከለው!
እንደ እውነቱ ከሆነ ይሄንን ጥያቄ በመጠየቅ የቅድስት ቤተክርስቲያንንና የአማኞቿን ወይም የተከታዮቿን መብት የማስከበር ኃላፊነትና ግዴታ የነበረባቸው "ቤተክርስቲያንን እንመራለን!" የሚሉት አካላት ነበሩ። ነገር ግን እንዳለመታደል ሆኖ እነኝህ አካላት ለቤተክርስቲያን መሥራትና እግዚአብሔርን ማገልገል ትተው የቤተክርስቲያንን ጥቅም በሚፃረር መልኩ ለአሸባሪው ፀረ ቤተክርስቲያን አገዛዝ የሚሠሩና እሱንም ተግተው የሚያገለግሉ በመሆናቸው ጥያቄውን የሚያቀርቡና የቅድስት ቤተክርስቲያንን መብት የሚያስጠብቁ ሊሆኑ አልቻሉም። ጭራሽ እንዲያውም የቃል ኪዳን ምልክቱን እንዳንይዝና እንዳንጠቀም የሚያስጠነቅቁት እነሱው ናቸው። ከዚህም አልፈው ምን ወደ ማድረግ ተሸጋግረዋል መሰላቹህ በፎቶዎቹ ላይ እንደምትመለከቱት የዋቄፈታን የባዕድ አምልኮ መለያ ቀለም የሆነውን ጥቁር ቀይና ነጭ ምልክት ያለበትን ልብስ ለብሰውና የዚሁ ባዕድ አምልኮ መለያ የሆነውን በትር ይዘው በድፍረት በዐውደ ምሕረቱ ላይ በመቆም "እንዘምራለን" የሚሉ የባዕድ አምልኮ ተከታዮች እና "እንሰብካለን፣ እንባርካለን!" የሚሉ "የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ጠባቂ ነኝ!" የሚለው አቡነ ጎርጎርዮስ የተባለውን ትግሬ እያያቹሃቸው ነው‼
ካህናትንና ምእመናንን የቃልኪዳን ምልክት ያለበትን ልብስ እንዳንለብስ የከለከሉት ካድሬዎቹ እነ አቡነ አብርሃም ግን በቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ የባዕድ አምልኮ ምልክት ያለበት ልብስና በትር ተይዞ ቅድስት ቤተክርስቲያንን ለማርከስ በተደጋጋሚ ጥረት ሲደረግ ግን ምንም ያሉትና ያደረጉት ነገር የለም። አብረው ተማክረው ነውና ይሄንን ጥፋት እየፈጸሙ ወይም ቅድስት ቤተክርስቲያንን እየወጉ ያሉት⁉️ 

ወዮ ለእኛ! ይሄ አሸባሪ አገዛዝና ውሾቹ ካድሬ የውሸት ጳጳሳት እንዲሁም ካህናት በዚህ ደረጃ ተቀናጅተው በቅድስት ቤተክርስቲያን ላይ በመዝመት ጥፋት እየፈጸሙና ቅድስት ቤተክርስቲያንን እየወጉ እንደሆነ በዓይናችን እያየንና በጆሯችን እየሰማን ሐዋርያው "ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽማ ስለተሰጠች ሃይማኖት እንድትጋደሉ እያሳሰብኩ እጽፍላቹህ ዘንድ ግድ ሆነብኝ!" ይሁ. 1፤3 በማለት አጥብቆ እንዳሳሰበን ጠላትን በመፋለም ሃይማኖታችንን የመጠበቅ ግዴታንን ተወጥተን ቅድስት ቤተክርስቲያንን ከጥፋት መታደግ ሲኖርብን ዝም ጭጭ ብለን በመመልከት ቅድስት ቤተክርስቲያንን እያስበላን እያስጠፋን ላለነው ወዮ‼️ 
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment