በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
በኢትዮጵያ ጽኑ መናወጥ ይሆናል! የሞሳህና የቶቤል ዋነኛ አለቃ ጎግ ማን ነው? ሳባና ድዳን ማን ናቸው?በመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ 38 በሙሉ!
ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ 38
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦
² የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን በጎግ ላይና በማጎግ ምድር ላይ፥ በሞሳሕና በቶቤል ዋነኛ አለቃ ላይ አቅናበት፥ ትንቢትም ተናገርበት፥
³ እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሞሳሕና የቶቢል ዋነኛ አለቃ ጎግ ሆይ፥ እነሆ፥ እኔ በአንተ ላይ ነኝ።
⁴ እመልስህማለሁ በመንጋጋህም ልጓም አገባብሃለሁ፥ አንተንና ሠራዊትህንም ሁሉ፥ ፈረሶችንና ፈረሰኞችን የጦር ልብስ የለበሱትን ሁሉ፥ ጋሻና ራስ ቍርን ሰይፍንም ያያዙትን ሁሉ፥ ታላቁን ወገን አወጣለሁ፥
⁵ ፋርስንና ኢትዮጵያን ፉጥንም ከእነርሱ ጋር ጋሻና የራስ ቍርን የለበሱትን ሁሉ፥
⁶ ጋሜርንና ጭፍሮቹን ሁሉ፥ በሰሜን ዳርቻም ያለውን የቴርጋማን ቤትና ጭፍሮቹን ሁሉ፥ ብዙዎችንም ሕዝቦች ከአንተ ጋር አወጣለሁ።
⁷ አንተና ወደ አንተ የተሰበሰቡ ወገኖችህ ሁሉ ተዘጋጁ፥ አንተም ራስህን አዘጋጅተህ አለቃ ሁናቸው።
⁸ ከብዙ ዘመንም በኋላ ትፈለጋለህ፤ በኋለኛውም ዘመን፥ የዘላለም ባድማ በነበሩ በእስራኤል ተራሮች ላይ ከብዙ ሕዝብ ውስጥ ወደ ተሰበሰበች፥ ከሰይፍ ወደ ተመለሰች ምድር ትገባለህ፤ እርስዋም ከሕዝብ ውስጥ ወጥታለች ሁሉም ሳይፈሩ ይቀመጡባታል።
⁹ አንተም ትወጣለህ፥ እንደ ዐወሎ ነፋስም ትመጣለህ አንተና ጭፍሮችህ ሁሉ ከአንተም ጋር ብዙ ሕዝብ ምድርን እንደ ደመና ትሸፍናላችሁ።
¹⁰ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚያ ቀን ነገር ወደ ልብህ ይገባል፥
¹¹ ክፉ አሳብንም ታስባለህ፥ እንዲህም ትላለህ፦ ቅጥር ወደሌላቸው መንደሮች እወጣለሁ ተዘልለው ወደሚኖሩ፥ ሁላቸው ሳይፈሩ ያለ ቅጥርና ያለ
መወርወሪያ ያለ መዝጊያም ወደሚቀመጡ እገባለሁ፤
¹² ምርኮን ትማርክ ዘንድ ብዝበዛንም ትበዘብዝ ዘንድ፥ ባድማም በነበሩ አሁንም ሰዎች በሚኖሩባቸው ስፍራዎች ላይ፥ ከአሕዛብም በተሰበሰበ፥ ከብትና ዕቃንም ባገኘ፥ በምድርም መካከል በተቀመጠ ሕዝብ ላይ እጅህን ትዘረጋ ዘንድ።
¹³ ሳባና ድዳን የተርሴስም ነጋዴዎች መንደሮችዋም ሁሉ፦ ምርኮን ትማርክ ዘንድ መጥተሃልን? ብዝበዛንስ ትበዘብዝ ዘንድ ብርንና ወርቅንስ ትወስድ ዘንድ ከብትንና ዕቃንስ ትወስድ ዘንድ እጅግስ ብዙ ምርኮ ትማርክ ዘንድ ወገንህን ሰብስበሃልን? ይሉሃል።
¹⁴ አንተ፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለዚህ ትንቢት ተናገር ጎግንም እንዲህ በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚያ ቀን ሕዝቤ እስራኤል ሳይፈራ በተቀመጠ ጊዜ አንተ አታውቀውምን?
¹⁵ አንተም፥ ከአንተም ጋር ብዙ ሕዝብ ሁላቸው በፈረሶች ላይ የተቀመጡ፥ ታላቅ ወገንና ብርቱ ሠራዊት፥ ከሰሜን ዳርቻ ከስፍራችሁ ትመጣላችሁ።
¹⁶ ምድርንም ትሸፍን ዘንድ እንደ ደመና በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ትወጣለህ። በኋለኛው ዘመን ይሆናል፥ ጎግ ሆይ፥ በዓይናቸው ፊት በተቀደስሁብህ ጊዜ አሕዛብ ያውቁኝ ዘንድ በምድሬ ላይ አመጣሃለሁ።
¹⁷ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእነርሱ ላይ እንደማመጣህ በዚያች ዘመን ብዙ ዓመት ትንቢት በተናገሩ በባሪያዎቼ በእስራኤል ነቢያቶች በቀደመው ዘመን ስለ እርሱ የተናገርሁ አንተ ነህን?
¹⁸ በዚያም ቀን ጎግ በእስራኤል ምድር ላይ በመጣ ጊዜ መቅሠፍቴ በመዓቴ ይመጣል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
¹⁹ በቅንዓቴና በመዓቴ እሳት ተናግሬአለሁ፦ በእርግጥ በዚያ ቀን በእስራኤል ምድር ጽኑ መናወጥ ይሆናል፤
²⁰ ከፊቴም የተነሣ የባሕር ዓሣዎችና የሰማይ ወፎች የምድረ በዳም አራዊት በምድርም ላይ የሚንቀሳቀሱ ተንቀሳቃሾች ሁሉ በምድርም ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ይንቀጠቀጣሉ፥ ተራሮችም ይገለባበጣሉ ገደላገደሎችም ይወድቃሉ ቅጥርም ሁሉ ወደ ምድር ይወድቃል።
²¹ በተራሮቼም ሁሉ በእርሱ ላይ ሰይፍን እጠራለሁ፥ የሰውም ሁሉ ሰይፍ በወንድሙ ላይ ይሆናል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
²² በቸነፈርና በደም እፈርድበታለሁ ዶፍም የበረዶም ድንጋይ እሳትና ድኝም በእርሱና በጭፍሮቹ ከእርሱም ጋር ባሉ በብዙ ሕዝብ ላይ አዘንባለሁ።
²³ ታላቅ እሆናለሁ እቀደስማለሁ በብዙ አሕዛብም ዓይን የታወቅሁ እሆናለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
እንግዲህ የሞሳህ እና የቶቤል ዋነኛ አለቃ ጎግ ማን ነው? ብለን ነው መርመር ያለብን እንደገናስ እስራኤል የተባሉት የሚኖሩበት እስራኤል የተባለው ሳባና ድዳን እነማን ናቸው?ይህን ነው እንግዲህ ማወቅ ያለብን ።
የሞሳህ እና የቶቤል ዋነኛ አለቃ ጎግ ማን ነው? ጎግ ማጎግ ማን ነው?ሳባና ድዳንስ ማን ናቸው?ይህን ካወቅን ማን ወደ የት እንደሚሄድ እንለያለን ማለት ነው።ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ 10:2 የሞሳህና የቶቤል ዋነኛ አለቃ ጎግን ማን እንደሆነ ይነግረናል እንዲህም ይላል የያፌት፡ልጆች ጋሜር፥ማጎግ፥ማዴ፥ያዋን፥ይልሳ፥ቶቤል፥ሞሳሕ፥ቴራስ፡ናቸው።እንግዲህ ኦሪት ዘፍጥረት እንደሚነግረን እግዚአብሔር የያፌት ልጆች ናቸው ማን እነ ማጎግ እነ ቶቤል እነ ሞሳሕ።የያፌት ልጆች ማን ናቸው የያፌት ልጆች ማለት አውሮፓውያን አሁን ነጮች ማለት ነው በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ነጮች የያፌት ልጆች ናቸው።ስለዚህ ጎግና ማጎግ ማን ናቸው የያፌት ልጆች የአውሮፓና የሰሜን አሜሪካ ፈረንጆች ናቸው ማለት ነው።እንግዲህ እነዚህ ናቸው እስራኤል ወደ ተባለው ወደ ሳባና ድዳን የሚሄዱት እነዚህ ናቸው። የያፌት ልጆች የአውሮፓና የሰሜን አሜሪካ ፈረንጆች ናቸው።አሁን ሳባና ድዳን እነማን ናቸው? ጎግ ሊረግጣቸውና ሊበዘብዛቸው የመጣው እስራኤል የተባሉት ያሉበት ሳባና ድዳን እነማን ናቸው?
ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 10:7 እንዲህ ይላል«...የኵሽም፡ልጆች፡ሳባ፥ኤውላጥ፥ሰብታ፥ራዕማ፥ሰበቃታ፡ናቸው።የራዕማ፡ልጆችም፡ሳባ፥ድዳን፡ና ቸው።.....'' እንግዲህ ምን ይለናል ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 10:7 እስራኤል የተባሉት መጽሐፍ ቅዱስ በትንቢተ ሕዝቅኤል ላይ ሳባና ድዳን መጣን ከብትና እህልም ወርቅንም ብርንም ልትወስድ መጣሃልን የሚሉት እስራኤል እንደዚህ ብለው የሚናገሩት ሳባና ድዳን የኩሽ ልጆች ናቸው ይላል መጽሐፍ ቅዱስ።አክሱም አለት ላይ ደግሞ ተቀርጾ የሚኖረው የንጉሡ የኢዛና መልእክት በግዕዙ እንዲህ ይላል ኢዛና ንጉሠ አክሱም ወሑመራ ወረዳ ወካሱ ወሳባ ወሰለሃኑ ወፀርድ ወህብስት ወበጌ ንጉሠ ነገሥት ።ኢዛና ንጉሠ አክሱም፡ ንጉሠ ሑመራ፡ ንጉሠ ረዳ ፡ንጉሠ ድዳን ፡ንጉሠ ኩሽ፡ ንጉሠ ሳባ፡ ንጉሠ ሠለሃኑ፡ ንጉሠ ፀርድ፡ ንጉሠ ህብስት ፡ንጉሠ በጌ ነው የሚለው።እንግዲህ እንደምናየው ሳባና ድዳን የኩሽ ልጆች እግዚአብሔር እስራኤል የሚላቸው የኢትዮጵያ ሰዎች ናቸው ማለት ነው።እስራኤልነታቸው በብሉይ ሴም የልጅ ልጅ የዮቅጣን ልጆች ከኩሽ ጋር ተጋብተው የተገኙበት ሁኖ ሳለ ዋና ዋና እስራኤል የሚያሰኛቸው ክርስቲያኖች መሆናቸው ነው።ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ እንደሚነግረን በመጨረሻ ቀን አውሮፓውያን በተለይ ምዕራብ አውሮፓውያን የያፌት ልጆች የሆኑት ፈረንጆች ከአውሮፓና ከሰሜን አሜሪካ ይመጣሉ።ኢትዮጵያዊያንን እራሳቸውን መሳሪያ አድርገው ክርስቲያኖችን በኢትዮጵያ ሊያጠፉ ሊያከስሙ የኢትዮጵያንም የተፈጥሮ ሃብት ፈልገው ሊወስዱ ሊበዘብዙ ይመጣሉ በመጨረሻው ቀን ያን ጊዜ ቁጣየን በእነሱ ላይ አደርጋለሁ እነሱንም አጠፋለሁ ይላል እግዚአብሔር ።አሁን እንደ ምናየው የያፌት ልጆች ነጮች በመጨረሻው ቀን ክርስቲያኖችን እና በመልካምድራቸው ውስጥ ያሉት ከብቶችን ፡እህልን ፡ወርቅን ፡ብርን ሁሉ የተፈጥሮ ሀብት ወይም ፈረንጆች Natural Resources የሚሉትን ፈልገው ይመጣሉ።ክርስቲያኖችንም ሊያጠፉ ልክ አሁን ኢትዮጵያን እንዳደረጉት ማለት ነው አፍሪካን ከበቡ መጨረሻ ላይ ኢትዮጵያን ነው ከበው ያስቀሩት ሊያጠፉት የሚፈልጉትም ክርስትናን ነው አማራ በሚል ስም።እስራኤል ማለት መጽሐፍ ቅዱስ ላይ በግልጽ ነው ያስቀመጠው ምንም ጥያቄ የለውም እነማን እንደሆኑ ከእነመልካቸው ከእነዘራቸው ከእነ አሉበት ቦታ እንደገናም ሚወሩት ደግሞ ጎግ የሚባሉት እነማን እንደሆኑ ከእነዘራቸው እስከሚኖሩበት ቦታ በግልጽ አስቀምጠውታል።ስለዚህ አሁን ያለው ጦርነት በጎግ ማጎግ እና በእስራኤል መካከል ነው ማለት ነው።አሁን በኢትዮጵያም የምናየው ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ 1966 ዓ.ም ከውስጥ የውስጥ ኃይሎችን ተጠቅመው የውጭ ኃይሎች ፈረንጆችና አረቦች በተለይ ምዕራብ አውሮፓ አገሮች በውስጥ አቀጣጥለው ክርስትናን የሚያጠፋ ነገር አቀጣጥለው በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከየካቲት 1966 ዓ.ም ጀምሮ ያለው ዘመቻ ሁሉ እስከ አሁን ድረስ ክርስትናን የማጥፋት ዘመቻ ነው በኢትዮጵያ ላይ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን፡ ክርስትናንን የማጥፋት ፡የክርስትና ምሰሶ የሆኑ ነገሮች ሁሉ፡ የክርስትና ምልክቶችን ሁሉ፡ የክርስትና ባህልን ፡የክርስትና ፍቅርን ፡በወንድማማች መካከል ያለ ፍቅርን፡ የማጥፋት ዘመቻ የጥላቻ ዘመን ነው። ከ1966 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ያለው ወንድም ወንድሙን የሚጠላት ወገን ወገኑን የሚጠላበት ሰው በመደብና በመደብ ተከፋፈለ ተብሎ አንድ መደብ በዝባዥ መደብ፡ ተበዝባዥ መደብ ተብሎ ኢትዮጵያዊያን በጠላትነት በዝባዥ ብሔር ፡ተበዝባዥ ብሔር ተብሎ ጎሳና ጎሳ በጠላትነት፡ ሰውና ሰው በጠላትነት ፡ቋንቋው ሁሉ በጠላትነት፡ በጥላቻ ላይ የተመሠረተ ክፉ ትውልድ ነው የመጣው።ይህን የፈጠሩት ምዕራባውያን መጥተው ነው በመጽሐፍ እንደተነገረው ኢትዮጵያዊያንን እራሳቸውን መሳሪያ አድርገው ይጠቀማሉ።ኢትዮጵያን ክርስትና ክርስትናን ከኢትዮጵያ ለማጥፋትና ክርስቲያኖችን ለማጥፋት በጠላትነት ስሙን ወደ ላይ አድርገው ይህን ነው ጠላታችሁ ምቱት አፍርሱት የሚሉትም አማራ የሚባለውን ነው።አማራ የክርስትና ኮድ Name ነው።ክርስትና እንዳይሉ በኮድ መጠቀም የፈለጉት አማራ ብለው ነው።ክርስትናን ለማጥፈት ኢትዮጵያን ለመበተን ይጠቀሙባቸዋል ይላል።አሁን በመፈጸም ላይ ያለው ይኼ በመጽሐፍ የተጻፈው ነው።ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ የሚለው የአውሮፓ ሰዎች ብዝበዛን ለበዝበዝ ብርንና ወርቅን ለመውሰድ ከብትንና ዕቃን ለመውሰድ እጅግ ብዙ ምርኮን ለማግኜት አውሮፓውያን አንድ ሀሳብ ሁነው ድንበር ጠባቂ ወደ ሌለው ወገን ወደ አፍሪካ ይመጣሉ ኢላማቸውንም ኢትዮጵያ ክርስቲያኖችና በቤተክርስቲያን ላይ ያነጣጥራሉ።የኢትዮጵያ ክርስቲያኖችንና ቤተክርስቲያንን ለማጥቃትም ኢትዮጵያውያንን እራሳቸውን መሳሪያ አድርገው ይጠቀማሉ ነው የሚለው።እስራኤል ማለት ኢትዮጵያ /እስራኤል ዘነፍስ ኢትዮጵያ/ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን መሆኗ ከላይ አይተናል ግን የበለጠ ማረጋገጫ ለሚፈልጉ ሰዎች ደግሞ መዝሙር 88 ላይ እንዲህ ይላል "ከግብፅ የወይን ግንድ አመጣህ አሕዛብን አባረህ እርሷንም ተከልህ በፊቷም ስፍራን አዘጋጀህ ስሮቿንም ተከልህ ምድርንም ሞላች ጥላዋ ተራሮችን ከደነ፣ጫፎቿም እንደ እግዚአብሔር ዝግባ ሆኑ ቅርጫፎቿንም እስከ ባሕር ቡቃያዋንም እስከ ወንዝ ዘረጋች ።አጥሯን ለምን አፈረስህ መንገድ ኃላፊ ሁሉ ይቀጥፋታል የዱር እሪያ አረከሳት፣የአገር አውሬም ተሰማራባት የሰራዊት አምላክ ሆይ እንግዲህ ተመለስ ከሰማይ ተመልከት እይም ይችን የወይን ግንድ ጎብኝ በሰው ልጅ ስለአንተ ያጸናሃውን ቀኝህ የተከላትን አንሳ በእሳት ተቃጥላለች ተነቅላም አለች ከፊትህ ተግሳጽም የተነሳ ይጠፋሉ።ለአንተ ባጸናሃው በሰው ልጅ ላይ በቀኝህ ሰው ላይ እጅህ ትሁን ከአንተም አንራቅ አድነንን ስምህንም እንጠራለን የሰራዊት አምላክ አቤቱ መልሰን ፊትህንም አብራ እኛም እንድናለን ።"ይላል እንግዲህ እንደምናው ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እስራኤል ለመሆኗ ምን ይላል እግዚአብሔር በመዝሙር 88 ላይ ቅዱስ ዳዊት እንደሚለው ከግብጽ የወይን ግንድን አመጣህ እና ተከልካት እሷም አበበች ከግብጽ የወይን ግንድን አመጣህ አሕዛብን አባረህ እርሷንም ተከልህ የሚለው እንግዲህ አንዳንድ ሰዎች አይሁድን ነው ከዚያ አውጥቶ በሲና በረሃ አድርጎ ጁድያን የወረሱ እነሱ ናቸው ስለዚህ ጁዱያን ስለሰፈሩ ነው ይላል ይኼ ግን አይደለም ምክንያቱም ምን ይላል ቀኝህ የተከላትን ይላል ቀኝህ ማለት ክርስቶስ ማለት ነው።በየትኛው ቦታ ሲጻፍ በእግዚአብሔር በቀኙ በኩል ያለው ክርስቶስ ነው የእግዚአብሔር ቀኙ ክርስቶስ ነው በየትኛውም ቦታ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያሉ ስንኞች በሙሉ ቀኝ የሚለው ክርስቶስን ነው።ክርስቶስ ደግሞ አይሁድን አይደለም ክርስቶስ የተከለው ቤተክርስቲያንን ነው።ከግብፅ መጣ የተተከለች ቤተክርስቲያን አሁንም ያለች ዙሪያዋ አጥራ የተፈረሰባት ኢትዮጵያ ብቻ ናት።ሌላ ቤተክርስቲያን የለም።ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ብቻ ናት ከግብጽ መጣ የተተከለች መጽሐፍ ደጋግሞ የሚያወራላት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብቻ ናት።እንግዲህ ኢትዮጵያ እነዚህ ከላይ ያየናቸው ኃይሎች እየሸራረፉ እያሳነሱአት ህዝቦቿንም እየበታተኑ መጡና መጨረሻ ላይ ያተኮሩት መሐል ቦታ ሁሉም አጥረው አጥሯን ሁሉ አጥረው አጥረው አጥሯን አሳንሰው የባህር በሮቿንም ዘግተው ሕዝቦቿንም በታትነው አሁን ያተኮሩት መሐል ላይ የሚኖር ክርስቲያንን ነው እሱም የኮድ ስም አላቸው አማራ የሚል የኮድ ስም ነው የሰጡት። አሁን ምን ይላል መጽሐፍ ቅዱስ ትንቢተ ዳንኤል 12:7 "ከወንዙም፡ውሃ፡በላይ፡የነበረው፡በፍታም፡የለበሰው፡ሰው፡ቀኝና፡ግራ፡እጁን፡ወደ፡ሰማይ፡አንሥቶ፦ለዘመንና፡ለዘመናት፡ለዘመንም፡እኩሌታ፡ነው፤የተቀደሰውም፡ሕዝብ፡ኀይል፡መበተን፡በተጨረሰ፡
ጊዜ፡ይህ፡ዅሉ፡ይፈጸማል፡ብሎ፡ለዘለዓለም፡ሕያው፡ኾኖ፡በሚኖረው፡ሲምል፡ሰማኹ።"አለ ነብዩ ዳንኤል እነዚህ የቅዱሳን ኃይል ተበትኖ በተጨረሰ ጊዜ ያን ጊዜ መጨረሻ ይሆናል እግዚአብሔር በጠላቶቹ ላይ ይነሳል ማለት ነው እነዚህ መጥተው በሚወሩ ኢትዮጵያን በሚያሳንሱ ውስጧን በሚበጠብጡ ክርስትናን ማጥፋት በሚፈልጉ የተፈጥሮ ሀብቷን በሚሹ ላይ ይነሳል ያጠፋቸውማል ነው የሚለው ዳንኤል።እንግዲህ ቀደም ሲል እንደ አየነው የአሜሪካ ፓሊሲ ኢትዮጵያን ማፈራረስ ስለሆነ አሜሪካ በስልጣን ላይ ያስቀመጠቻቸውን ታዛዦቿን ኢትዮጵያን በቋንቋ ከፋፍለው እንዲገዙ ያደረገችበት ዋናው ምክንያት ሌላ ኃይል ሳያስፈልግ ኢትዮያዊያን በቋንቋ ተለያይተው እንዲበታተኑ ማድረግ ነበረ።ይህ መበታተን እንዲመጣ በቋንቋ የማይግባባ አንድ ትውልድ እስኪያሌፍ አሜሪካኖች በኢትዮጵያ ላይ ስልጣን ላይ ያስቀመጡትን ታዛዣቸውን ሲደጉሙትና ሲጠብቁት ኑረዋል አሁን በኦሮሞዎች አካባቢ የሚታየው ፀረ ኢትዮጵያዊ ቋንቋን እንቅስቃሴ የአሜሪካ ደባ ውጤት ነው።ስለዚህ አሜሪካ ቀንበሯን በኢትዮጵያ ላይ እጅግ ስለአከበደች የኢትዮጵያን ኃይልም በመሪነት ስለበተነች በመጽሐፍ እንደተጻፈው መጀመሪያ እሷ ትወድቃለች።አሜሪካ በልቧ በኢትዮጵያ ላይ የነበረኝ እቅድ አሟላሁ ያለች እለት ትወድቃለች። እስከ አሁን ያየነው ትንቢት የተነገረው የዛሬ 2600 እና የዛሬ 3000 ዓመት ነው ያን ጊዜ ብረት አልተጠፈጠፈም መስታወት አልተሰራም መንገድ አልተነጠፈም መኪና አይሽከረከርም ነበር የስልክ መስመር አልተዘረጋም መድፍ አልተተኮሰም በአየር ላይ ጉዞም አልታለመም እንግዲህ በዚያ ጊዜ ነው ከተማ ሚባለው ትንሽ መንደር በነበረ ጊዜ ሰው በቀን 7 ኪ.ሜ እንኳን ተጉዞ መድረስ የማይችልበት ነበር። እንግዲህ በዚያ ጊዜ ነው በመጨረሻው ጊዜ ከምዕራብ የያፌት ልጆች የሚሆኑ ፈረንጆች ከምዕራብ ይመጡና አጥር ወደ ሌለው ወደ ማይጠበቀው በመሳሪያ: በጦር ኃይል: ወደ ማይጠበቀው ወደ አፍሪካ ይመጣሉ።አፍሪካንም በቅኝ ግዛት ይይዛሉ ፈልገው የሚመጡትም ጥሬ ሀብትን ነው ከብትን ነው እህልን አዝመራን ብርን ወርቅን በከርሰ ምድር ውስጥ የሚገኝ ንጥረ ነገርን በከርሰ ምድር ውስጥ የሚገኝ ሀብትን ፈልገው ነው ሚመጡት ይላል በዘመኑ አነጋገር Natural Resource ፈልገው ነው ሚመጡት ይላል የዛሬ 2600 ዓመት ነው ይሄ የተነገረው።ያን ጊዜ የያፌት ልጆች ምን ነበሩ የያፌት ልጆች ምንም አልነበራቸውም ያን ጊዜ ዘላኖች ነበሩ በመንገድ የሚኖሩ እንደውም አሳ እንኳን አጥምደው መብላት እንኳ የማይችሉ ነበሩ እነሱ ግን በመጨረሻ ዘመን በሳይንስና በእደ ጥበብ ይራቀቃሉ ዓለምን ይቆጣጠራሉ ።በሳይንስና በዕደ ጥበብ ከመራቀቃቸው የተነሳ ዓለምን ይበክሏታል የሳይንስ ውጤቶች በሆኑ ነገሮች ዓለም ትበረዛለች በዘመኑ አነጋገር polluted ትሆናለች ብለው የተናገሩት የዛሬ 2600 ዓመት ነው።እንግዲህ ሰው ይህን እያየ አይ እግዚአብሔር የለም እግዚአብሔርን መቼ አየሁትና መቼ ጨበጥኩትና መቼ ሰማሁትና መቼ ባይኔ በብሌኑ አየሁትና ማለት ሞኝነት ነው ሞኝ አትሁኑ ። ሞኝ ነው እግዚአብሔር የለም የሚለው ምክንያቱም እንኳን የዛሬ 2600 ዓመት አሁን የሚሆነውን ነገር መንገር ይቅርና ከአንድ ሰዓት በኋላ ሰው ምን እንደሚሆን አያውቅም።የዘመኑ የተራቀቀው የአየር ትንበያ ነገ ይዝነብ አይዝነብ አያውቅም ግምት ነው ሚሰጠው እና ደግሞ ምዕራባውያን ይሄ ተጠራጣሪ ሁኑ ብለው የሚያስተምሩት ትምህርት Sceptical ሁኑ የሚሉት የእነሱ ፍልስፍና ነው የተነገረው ትንቢት በእነሱ ላይ ስለሆነ እኛ ያን ትንቢት እንዳናምን ነው Sceptical ሁኑ ወይም ተጠራጣሪ ሁኑ ብለው የሚያስተምሩ በፍልስፍናቸው ውስጥ በሳይንስአቸው ውስጥ sceptical መሆን ነው ትልቁ ነገር ብለው የሚያስተምሩ በእነሱ ላይ የተነገረውን እንዳናውቅ እንዳንቀበል ነው የእነሱ ተገዢ እንድንሆን ነው።ኢትዮጵያዊ በተለይ ይህን ማወቅ አለበት ስለዚህ አለማመን ሞኝነት ነው ከእግዚአብሔር መንገድ የወጣችሁ ወደ እግዚአብሔር መንገድ ተመለሱ ለማለት ነው ።

Blogger Comment
Facebook Comment