የትግራይ ክልል፤ ዛሬ ለደረሰው የአገር ጥፋት ሁሉ በሥልጣን በነበሩበት ሰዓት የሠሩት ግፍና በደል በመጠኑ ዋጋ እንዲከፍሉ አድርጓቸዋል፡፡

የትግራይ ክልል፤ ዛሬ ለደረሰው የአገር ጥፋት ሁሉ በሥልጣን በነበሩበት ሰዓት የሠሩት ግፍና በደል በመጠኑ ዋጋ እንዲከፍሉ አድርጓቸዋል፡፡ ይህን ደግሞ ደጋግመን ወንጀላቸውንም ነግረናቸዋል ፍርዳቸውንም ቀድመን ገና በሥልጣኑ ላይ እያሉ ነግረናቸዋል በመናቃቸው ዋጋ ከፍለዋል ገናም ይከፍላሉ፡፡ አንድ አራተኛ ጉዳት ተቀብለዋል ገና ሦስት አራተኛ የሆነ ሙሉ ጥፋታቸው እየተከተላቸውና ሊጨርሳቸው እየተጓዘ ይገኛል በምንም ሰውኛ ዘዴ አይቆምም፡፡ ኢትዮጵያዊነት ተዋሕዶ እምነት ሰንደቋ የመላው የሰው ዘር በሙሉ የሚመዘንበት በሚዛኑ ቀሎ ሲገኝ የሚጠረግበት የሚወገድበት ነው፡፡ እነዚህም ኢትዮጵያዊነትን ተዋሕዶን ሰንደቋን ሊያፈርሱ የደከሙ የቻሉትን ያህል ለዲያብሎስ ግዳይ የጣሉ በመሆናቸው በፍጹም ይጠረጋሉ፡፡ በተለይ በአማራው ሕዝብ ላይ ልክ ሂትለር በጀውስ /እስራኤላውያን/ ላይ የሠራውን የዘር ማጥፋት አብዝተውና በከፋ ጭካኔ ፈጽመውታል፡፡ ዛሬም እግዚአብሔር ስለፈረደባቸው ፍርዱ እያሳደዳቸው እየጨረሳቸው ይገኛል፡፡ እጅግ የመረረ የአማራ ጥላቻን በልባቸው በመትከላቸው ሕዝባቸውን ሁሉ ለዚህ ዘረኝነት ሰለባ እንዲሆን አድርገውታል፡፡ ከላዩ ማስወገድ ሲገባው ስላዘላቸው ፈቃዳቸውንም ፈጻሚ በመሆኑ ገና መከራው ባላየነው ባልሰማነው መጠን ይቀጥላል፡፡ ሁለቱም ጋ ያሉት የኦሮሚያው ኦሕዲድም ወያኔም በአስተሳሰብ በስልት በጭካኔ በኢትዮጵያ ጠልነት በዘረፋ በሌብነት በሁሉም ተመሳሳይ ተወራራሽ አስተሳሰብ ያላቸው ናቸው፡፡ ሁለቱም ትእዛዝ የሚቀበሉት ከጌቶቻቸው ከአሜሪካ ከእንግሊዝ ከጀርመን ከፈረንሳይ ከቻይና ከዐረብ ኤሜሬትስ ከሳውዲ ዐረቢያ ከቱርክ ከግብጽ እናም ከሌሎችም ነው፡፡ በሚሰጣቸው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እስከአሁንም በከፋ አጥፊነታቸው ቀጥለዋል፡፡ ሌሎች ክልሎችም እንዲሁ በእነሱ መንፈስ የሚገፉ ሆነው ለኢትዮጵያ ጥፋት እየተባበሩ ይገኛሉ፡፡ ወያኔዎች ለሠሩት ግፍ በደል ኢትዮጵያ ጠልነት ራሳቸውን በኢትዮጵያ ሀብት ንብረትና የሕዝቦቿ ንብረት ዘርፈው ነጥቀው በክልላችን በሚሉት በዘረፋና በሌብነት ገነቡ በተለይ አማራውን ፈጁ አደኸዩ በወልቃይት ብቻ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ሕዝብን አጠፉ ዛሬ በአገራቸው ከወልቃይት ጠገዴ ጠለምት በጥቅሉ ከጎንደር የተጋዙ እስረኞች በአገራቸው አስረው ጉድጓድ ውስጥ ከተው አጥፍተዋል እስከአሁንም በጉድጓዳቸው አስረው የሚያሰቃዩአቸው ጥቂት አይደሉም፡፡ የእነሱ ግለባጭ የሆነው የኦሮሙማው መንግሥት በኢትዮጳያዊነት የሚምለው አንድም ቀን በወያኔ ስላለቁት ስለተሰወሩት ስለተፈጁት-ያነሣው የጠየቀው የለም፡፡ ይህ ወያኔ ተብዬ ድርጅት ያን ሁሉ ግፍ ፈጽሞ ሳይጸጽተው ዛሬም ያ የዘረፋ ወርቃማ ዘመን ትዝ እያለው ያንኑ አውሬነቱን ዳግም ሊያስቀጥል ያልማል፡፡ ዶሮ ብታልም ጥሬዋን እንዲሉ ዛሬም ሁለቱም አውሬዎች ጊዜ የሰጣቸው ቅሎች ድንጋይ ሰባሪዎች ለአንዴና ለዘለዓለሙ በእግዚአብሔር ብርቱ የቁጣ እሳት ይጠፋሉ፡፡ 

ከሁለቱም ኃይሎች ጋር ያልተሰለፈ ያልደገፈ ያልተባበረ ያልተጠቀመ እጅግ ጥቂት ነውና ሂያጁ ከምናስበው በላይ ነው፡፡ ወያኔ በኢትዮጵያም ታሪክ በአፍሪካም የቅርብ ጊዜ ድጋፍ ከአውሮፓ ከአሜሪካ ከእንግሊዝ ብዙ ቢሊዮኖችን በእርዳታ በብድር ያገኝ የነበረ ነው፡፡ የሚደንቀው እንግሊዝ በጀት ደጋፊ የአፋኝ ፖሊስና ደህንነት ደሞዝ ሸፋኝ ነበሩ፡፡ ዛሬም ሥራቸውን አላቋረጡም፡፡ ያ ገንዘብ ደግሞ በወያኔ ባለሟሎች ውጪ ተሻግሮ ዛሬ በድርድር ስም ስውር አጀንዳቸውን እያስቀጠለም ይገኛል፡፡ ሁለቱም በምንም መንገድ የማያመልጡት በፍጹምም ያልታየ ቅጣታቸውን አሁን ያዩታል ይቀበሉታል፡፡ ለአንዴም ለሁሌም ይደመድማቸዋል፡፡ በታሪክም በትዕቢታቸው በጭካኔያቸው በዘረኝነታቸው በዘራፊነታቸው በጨፍጫፊነታቸው እንደምሳሌ ለመጪውም ለሚተርፈውም ትውልድ ምሳሌ ሆነው ይዘከራሉ፡፡ ከእነሱ የሚተርፍ ጥቂት ሰውም ቢኖር እንኳን በሰው ፊት ለመታየት ለመቅረብ እጅግ የሚቸገር ዘወትር ወገኖቹን የሚረግም በሁለመናውም የተጎዳ ይሆናል፡፡

ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት አስር(፲) ገጽ-24 ላይ የተወሰደ
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment