✍️ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
በረኸኛው ቅዱስ ኣባታችን ኣባ ፓይሲዮስ (እ.አ.አ 1924-1994)ቅድስናቸው በሁሉም ግሪኮች ዘንድ የታወቀው፤ ፖለቲከኞች ፣ አገልጋዮች ፣ ዓለማውያን ፣ መነኮሳት ፣ ካህናት ፣ ጳጳሳት በኤጂያን ባሕር ዙሪያ ስለሚሆነው ነገር ሁሉ ከእያንዳንዱ ሰው ጋር ተነጋግረዋል።
የወደፊቷን ግሪክ እጣ ፈንታ ለማየት እስኪበቁ ድረስ አባታችን ቀናትን እና ሌሊቶችን በጸሎት ያሳለፉ ነበር።
ለግሪክ ፣ ለግሪካዊነትና ለቤተ ክርስቲያን ትልቅ፣ ልባዊና ጥልቅ ጭንቀት እንዳላቸው ለሚቀርቧቸው ሁሉ ያወሱ ነበር።
ከአባታችን ትንቢታዊ መልዕክቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦
ቅዱስ ኮስማ እንደተነበዩት ሩሲያውያን ከላይ ጣልቃ ይገባሉ፤ ግሪኮች ቁስጥንጥንያን/ኢስታምቡልን በአምላክ ፈቃድ ያስመልሳሉ።
ቱርክ በአጋሮቿ ትፈራርሳለች፤ ቱርኮች የተቀቀለውን ስንዴ በወገባቸው ዙሪያ አኑረዋል፤ የግሪክ ሠራዊት ወደ ቁስጥንጥንያ/ኢስታምቡል ያመራል
ቱርክ በ፮/6 ማይሎች ርቀቶች(የግሪክን የክልል ውሃ)መቃረቧን በዜና ሲሰሙ ከዚያ ጦርነት ይከተላል፤ መርከቦቿም ይደመሰሳሉ።
ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ፡፡ የቱርክ መጨረሻ መጀመሪያ ይሆናል።
ቁስጥንጥንያ/ኢስታምቡል ለግሪክ ትመለሳለች፤ በሩሲያ እና በቱርክ መካከል ጦርነት ይከሰታል፤ በመጀመሪያ ቱርኮች ያሸንፉ ይመስላቸዋል ነገር ግን ይህ የእነሱ መጥፊያቸው ይሆናል።
ቱርኮች ይጠፋሉ ፡፡ እነሱ ያለ እግዚአብሔር በረከት የተገነባ ህዝብ ስለሆኑ ይደመሰሳሉ።
አንድ ሦስተኛው ቱርኮች ወደ መጡበት የቱርክ ጥልቀት ይመለሳሉ፡፡ አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ክርስቲያን ስለሚሆኑ ይድናሉ ፣ ሦስተኛው ደግሞ በዚህ ጦርነት ይገደላሉ፡፡ ግሪኮች፣ አርመኖችና ኩርዶች ቱርክን ይከፋፈሏታል።
የቀደመው የቱርክ ትውልድ በአዲስ የፖለቲከኞች ትውልድ ይተካል። በእግዚአብሔር ላይ እምነት እና ተስፋ እስካለ ድረስ ብዙ ሰዎች ይደሰታሉ። በእነዚህ ሁሉ ዓመታት ውስጥ የሚሆነው ሁሉ ይህ ነው፡፡ ጊዜው ደርሷል፡፡
እንግሊዞች እና አሜሪካውያን ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ቁስጥንጥንያን ለግሪክ ይሰጧታል፡፡ ቱርኮች ግሪክን ይተናኮላሉ፤ ማዕቀብ ይከተለላል፤ ዘመነ ረሃብ ይመጣል። ግሪኮች ይራባሉ።
ከቱርክ ትንኮሳ በኋላ ሩሲያውያን ወደ ቢስፎረስ ባሕር ይወርዳሉ፣ እኛን ለመርዳት ሳይሆን፣ ሌሎች ፍላጎቶች ስላሏቸው እንጂ።
በሩሲያውያን እና በአውሮፓውያን መካከል ታላቅ ጦርነት ስለሚኖር ብዙ ደም ይፈስሳል፡፡ ግሪክ በዚያ ጦርነት ውስጥ የመሪነት ሚና አለመጫወቷ ትልቅ በረከት ነው። ምክኒያቱም በአውሮፓውያን መካከል በሚደረግ ጦርነት የሚሳተፍ ሁሉ ይጣፋልና ነው።
ቱርኮች ይመቱናል ግን ግሪክ ከፍተኛ ጉዳት አይደርስባትም፤ ቱርኮች በአገራችን ላይ ከፈፀሙት ጥቃቶች ብዙም ሳይቆይ ሩሲያውያን ቱርኮችን ይመቱና ያፈርሷቸዋል፤ ልክ አንድ ወረቀት ተቀዳደደው ይፈራርሳሉ፡፡
ሩሲያ ቱርክ ከወደመች በኋላ እስከ ፋርስ ባሕረ ሰላጤ ድረስ ጦርነቱን ትቀጥላለች፣ ወታደሮቿም ከኢየሩሳሌም ውጭ ይቆማሉ።
ከዚያ የምዕራባውያኑ ኃይሎች ሩሲያውያን ወታደሮቻቸውን ከእነዚህ ቦታዎች እንዲያስወጡ ማሳሰቢያ ይሰጣሉ።
ግን ሩሲያ ኃይሏን አታወጣም ፣ ከዚያ የምእራባዊያን ኃይሎች እነሱን ለማጥቃት ወታደሮችን መሰብሰብ ይጀምራሉ።
የሚፈነዳው ጦርነት ዓለም አቀፋዊ ይሆናል እናም የሩሲያውያንን ኪሳራ ያስከትላል፤ ግዙፍ መተራረድ ይኖራል ፣ ከተሞቹ የፈራረሱ መንደሮች ይሆናሉ።
ግሪክ በዚያ ጦርነት ውስጥ አትሳተፍም፤ የቁስጥንጥንያው ገዢ በእኛ በኩል ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ይሆናል።
የቱርክ መጥፋት ለግሪኮች ትልቅ እርካታ ይሆናል፤ ቁስጥንጥንያ ለግሪኮች ትመለሳለች።
የፀሎት እና ቅዳሴ ሥነ ስርዓት በቅድስት/ ሃጊያ ሶፊያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንደገና ይጀምራል።
በኢትዮጵያ ሃገራችን እየተደረገ ያለው ነገር ሁሉ በመላው የክርስትያን ዓለምም የሚንጸባረቅ ነው። የቅዱስ አባታችን የአባ ዘ-ወንጌል ትንቢቶች ከሃያ ስድስት ዓመት በፊት ከተሰወሩት የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አባት ከአባ ፓይሲዮስ ትንቢቶች ጋር የተዛመዱ ናቸው። በተለይ ቱርክን በተመለከተ። ቱርክ የግሪክም የኢትዮጵያም ቀንደኛ ጠላት ናት፤ አዎ! አባ ፓይሲዮስ እውነታቸውን ነው፤ ልክ እንደ ሶማሊዎቹና ጋሎቹ የነፍስ ዘመዶቻቸው ቱርኮችም ያለ እግዚአብሔር በረከት የተገነባ ህዝብ ስለሆኑ ይደመሰሳሉ።
እስራኤልን በተመለከት አስገራሚ ሁኔታዎችን እያየን ነው፤ እስራኤል በእህት አገር ክርስቲያን አርሜኒያ ላይ የተነሳችውን ቱርክ-መራሽ ሙስሊም አዘርበጃን እየደገፈች ነው፣ የጦር መሣሪያም እያቀበለቻት ነው። በሌላ በኩል እስራኤል ከዓረብ ሃገራት ጋር አንድ በአንድ ግንኙነቷን እየገነባች ነው። "የአብርሃም ስምምነት"፣ "በሰላም ፈንታ ሰላም" ብለውታል። የሰላም ፍርርሙ በእስራኤልና በሁለት የዓረብ አገሮች መካከል በዋሽንግተን በኢትዮጵያ አዲስ ዓመት መግቢያ ላይ በመስከረም 15/2020 ዓ.ም ተካሄደ። እስራኤል፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬት አገሮችና ባሃሬን የሰላም ስምምነት ውል ተፈራረሙ። ቀጣዮቹ ካታር፣ ኦማን፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ሞሮኮ ከሆኑ ይህ “ከብዙዎች ጋር ስምምነት” ይባላል። ስለዚህ ደግሞ ነብዩ ዳንኤል እንዲህ ይለናል፦
”እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል፤ በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ያስቀራል፤ በርኵሰትም ጫፍ ላይ አጥፊው ይመጣል፤ እስከ ተቈረጠውም ፍጻሜ ድረስ መቅሠፍት በአጥፊው ላይ ይፈስሳል” [ትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ ፱፥፳፯]
በሌላ በኩል ዛሬ የወጣ አስገራሚ ዜና የሚከተለውን ይለናል፦
„የቱርክ አመራር ከሶሪያ እስከ ሊቢያ ፣ ከሶማሊያ እስከ ቆጵሮስ ፣ ከኤጂያን ባሕር እስከ ካውካሰስ ድረስ ጠበኛ የሆነ የንጉሠ ነገሥት ባህሪ ቅዠቶች አሉት፡፡”
“Turkey’s leadership has fantasies of imperial behaviour with aggressive behaviour from Syria to Libya, Somalia to Cyprus, from the Aegean to the Caucasus,”
እነዚህን ሁኔታዎች ከአባ ፓይሲዮስ ትንቢቶች ጋር እናገናኛቸው። አባታችን የሚከተሉትን ትንቢቶች ተናግረው ነበር፦
የሶቪዬት ሩሲያ እ.ኤ.አ. ከ 1917 የቦልሼቪክ አብዮት በኋላ ከ 70 ዓመታት በኋላ ትፈርሳለች፡፡ (ትንበያው የተደረገው በ 70 ዎቹ መገባደጃ ላይ - በ 80 ዎቹ መጀመሪያ ላይ ነበር፡፡)
የቱርክ ቆጵሮስ ወረራ በ 1974 ከመከሰቱ ከ 2 ሳምንታት በፊት ራእይ አይተዋል፡፡
ቱርክ በግሪክ ላይ ጥቃት ከሰነዘረች በኋላ በቱርክ በሩሲያ እንደምትደመሰስ አስቀድመው አይተዋል ፡፡ ኔቶ ሩሲያውያንን ይቃወማል ግን ኃይሎቹ ይደመሰሳሉ።
እስራኤል ከተፀነሰች ከ 70 ዓመታት በኋላ ትጠፋለች፡፡ ከህዝባቸው ውስጥ 2/3 የሚሆኑት ክርስቲያን ይሆናሉ፡፡ (አባ ፓይሲዮስ በ 70 ዓመታቸው መሰወራቸው በአጋጣሚ ነውን?)
ቱርክ የኤፍራጥስ ወንዝን ግድብ ከዘጋች በኋላ የአርማጌዶን ጅምር ቅርብ ይሆናል ፡፡
ቱርክ በጥቂቱ ትከፋፈላለች ፡፡ አንድ ቁራጭ ወደ ግሪክ ይሄዳል; አንድ ቁራጭ ወደ አርሜኒያ አንዱ ደግሞ ወደ ኩርዲስታን ይሄዳል፡፡
በኢየሩሳሌም በሞርያ ኮረብታ የሚገኘውና በአሁኑ ጊዜ ዶም ኦቭ ዘ ሮክ የተባለው የእስላም መስጊድ (የጥፋት ርኵሰት) ይፈርሳል/ይወድቃል ፡፡ የሰሎሞን ቤተመቅደስ እንደገና ለመገንባት ዝግጁ በሚሆንበት ጊዜ አርማጌዶን ይቃረባል፡፡
እስራኤል ፍጻሜዋ እንደቀረበ ስትመለከት የቅርብ ጎረቤቶቿን በኑክሌር መሣሪያዎች ታጠቃለች፡፡
Blogger Comment
Facebook Comment