ሱዳን ከህገ-ወጡ የፋሺስት ቄሮ አገዛዝ ጋር በኢትዮጵያ ላይ እያሤረች ንው!

✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

አሸባሪው ዳግማዊ ግራኝ አሕመድ ዓሊ ከግብጽ፣ ሱዳን እና ቱርክ ጋር በመደመር የግራኝ አሕመድ ቀዳማዊን ህልም ዕውን ለማድረግ በመወራጨት ላይ ነው። 

ሙስሊሙን "ጄነራል" ሳሞራ ዩኑሱን ከዓመት በፊት ወደ ሱዳን በመላክ የጦር ሰራዊት ችግኙን እንዲተክል ካደረገ በኋላ በቅርቡ በአማካሪነት ወደ አዲስ አበባ አምጥቶታል። ልብ ብለናል? ሳሞራ ዩኑስ ወደ አዲስ አበባ በገባበት ዕለት "ከግራኝ ዐቢይ አሕመድ አፈነገጠች" በሚል የማታለያ እቃ-እቃ ጨዋታ ሌላዋ መሐመዳዊት ኬሪያ ኢብራሂም ሳሞራ ዩኑስን በመተካት ወደ መቐለ እንድትሄድ ተደረገች። ሁሉም ታስቦበት በቅደም ተከተለ የተሠራ ነው!

ኢትዮጵያን ለማጥፋት በህወሓትና ብልጽጋና ዙሪያ ከግራኝ አሕመድ ቀዳማዊ እርዝራዦችና ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር እነማን እየተባበሩ እንደሆኑ በሚገባ እንመዝግበው። ሁሉም ነገር ድራማ ነው! ሁሉም እርስበርስ ተፃራሪዎች በመምሰልና በመወቃቀስ እየተናበበቡ ለአንድ ዓላማ የሚሰሩ የ666 ወኪሎች ናቸው። ዓላማቸውም ኢትዮጵያና ተዋሕዶ ሃይማኖቷን ማጥፋት ነው።

ጎርፉ ማስጠንቀቂያ ሊሆናቸው በተገባ ነበር። በህገ-ወጦቹ አፋር፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብና ሶማሊያ ክልሎች እስካሁት ታይቶ የማይታወቅ የጎርፍ አደጋ ገጥሟቸዋል።

አፋር በተባለው ክልል የገዳይ ዐቢይ ሠራዊት የመስቀል በዓልን ለማክበር ለደመራ የሚሆን እንጨት ቆርጠው ሲያዘጋጁ የነበሩ ሦስት ወጣቶችን ገድሎ ዘጠኙን ደግሞ አቁስሏቸዋል።

እንግዲህ እንደምናየው ዳግማዊ ግራኝ አሕመድ ደመራና መስከረም ፴ ከመድረሳቸው በፊት ብዙ ፀረ-ኢትዮጵያ የሆኑ እርምጃዎችን ለመውሰድ በመጣደፍ ላይ ነው። "ችግኝ ስለተከልኩ ነው ዝናብ የበዛው!" እያለን ነው ጨቅላው ጂኒ።

እኛ ግን ክቡር መስቀሉን ተሸክመን ለደመራው እንዘጋጅ!


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment