ባዕዳዊው የኢስተር በዓል !

"ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤ የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱያመልኩኛል ተብሎ እንደ ተጻፈ በእውነት ትንቢት ተናገረ።" ማር 7:6_7

ብዙዎቹ የሃይማኖት መሪዎች የስነመለኮት ተማሪዎች የፋሲካ ( Easter ) በአልን ሁል ግዜ እንዲከበር በጥብቅ ያስተምራሉ:: ምክንያቱም የበአሉ መታሰቢያ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤን በማስመልከት ነው ይላሉ:: እውነት ግን የፋሲካ ( Easter ) በአል የጌታ ኢየሱስ የትንሳኤ በአል ነውን?እንደ "ገና" በአል ሁሉ ለ"ፋሲካ" በአልም ለበአሉ የሚደረጉ ሀይማኖታዊ ስርአቶች ያሉ ሲሆን የፋሲካ በአል በዓለም ህዝቦች ዘንድ በልዩ ልዩ የሐይማኖት ስርዓቶች ይከበራል:: ከእነዚህም መካከል በጥንቸል እና በጥንቸል እንቁላል የተመሰለ ቸኮላት እና ብስኩት እንዲሁም በአውሮፓ እና በአሜርካ በተጨማሪም በላቲን አሜርካ በኤሽያ በተለያዩ የባዕድ ሀይማኖት ስርአቶችና ድርጊቶች ሲከበር በተለይ በአውሮጳ ለ5 ተከታታይ ቀናት የሚሆን እንደ ጉድ የሚበላበት : የሚጠጣበት እንዲሁም የሚጨፈርበት በተጨማሪም ጸያፍ የሆነ የዝሙት ሀጢያት እርኩሰት የሚደረግበት ተወዳጅ በአል ነው "ፋሲካ"( Easter ) "ፋሲካ" በአል በቅጽል ስሙ የሚጠራው የ"ጥንቸል ክብረ በአል" ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ይህንን ስም ከምን ጋር እንደሚያገናኘውና በ"ፋሲካ" በአል ስም የሚከበረው በአል ምን እንደሆነ እንዲሁም እውነት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ማስታወሻ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ክብረ በአል ነውን? የሚለውን እውነት በጥልቀት እንቆፍራለን::
የፋሲካ ( Easter ) በአል ከመቼ ጀምሮ ማክበር በውጭ ደ ሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ ( The Encyclopaedia Britannica ) እንደሚነግረን እንደ "ገና" ( Christmas ) በአል ሁሉ የፋሲካ ( Easter ) በአልም ብዙ የጥንት የባዕድ አምልኮ ( pagan survivals ) ስርአት ያለው ክብረ በአል ሲሆን የበልግ የጥንቸል መራቢያ የተመሰለ ታላቅ በአል ነው ፋሲካ ( Easter ) (15th edition, Macropaedia, Vol. 4, p. 605, "Church Year").
"ፋሲካ" ( Easter ) የሚለው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሐዋርያት ስራ ላይ ተጽፎ የሚገኘው ቃል "አይሁድንም ደስ እንዳሰኛቸው አይቶ ጨምሮ ጴጥሮስን ደግሞ ያዘው። የቂጣ በዓልም ወራት ነበረ። በያዘውም ጊዜ ወደ ወኅኒ አገባው ከፋሲካም በኋላ ወደ ሕዝብ ያወጣው ዘንድ አስቦ እያንዳንዱ አራት ወታደሮች ሆነው እንዲጠብቁት ለአራት ጭፍራ ክፍል አሳልፎ ሰጠው። ሐዋ 12: 3_4 የKing James ትርጉም የተሳሳተ የቃል ፍቺ ሰጥቶታል:: ወደ ዋናው ነጥባችን ስንመጣ "ፋሲካ" ( Easter ) የሚለው ቃል ትርጉሙ የተገኘው ከግሪክ pascha ከሚለው ቃል ሲሆን ትርጉሙም ፓሶቨር (Passover) ማለት ሲሆን ፓሶቨር (Passover) ቀጥተኛ ትርጉሙም እስራኤላውያን ከግብጽ ምድር የወጡበትን እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር በየአመቱ ማርች ወይም አፕሪል ወር ላይ የሚያከብሩት ታላቅ በአል ነው:: መጽሐፍ ቅዱስ ኪንግ ጀምስ ትርጉም ግን የተሳሳተ ትርጉም በመስጠት የአይሁድን (Passover) ከግብጽ ባርነት ነጻ የወጡበትን በአል በ"ፋሲካ" ( Easter ) በሚለው ቃል እና ሀይማኖታዊ ስርአት ቀይሮታል ይላሉ ይህንን ጥናት የዘገበው ድረ ገጽ:: እንደ ድረገጹ ገለጻ መሰረት አማርኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉምን ጨምሮ በአለም ላይ ያሉ ብዛት ያላቸው በተለያዩ የአለም ህዝቦች ቋንቋ ተተርጉመው የተሰራጩት መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ቅጂው የተካሔደው ከኪንግ ጀምስ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ላይ ነው ይለናል ጥናቱ ስለሆነም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሁለት በአሎች ጎን ለጎን ተጽፈው በግልጽ ይገኛሉ አንደኛው የቂጣ በአል (Passover) በአል እስራኤላውያን ከግብጽ ምድር የወጡበት ክብረ በአል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የ"ፋሲካ" ( Easter ) በአል ነው:: "ለደቀ መዛሙርቱ። ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካ እንዲሆን ታውቃላችሁ፥ የሰው ልጅም ሊሰቀል አልፎ ይሰጣል አለ።" ማቴ 26:2
"በቂጣው በዓል በመጀመሪያ ቀን ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ ቀርበው። ፋሲካን ትበላ ዘንድ ወዴት ልናሰናዳልህ ትወዳለህ አሉት። እርሱም። ወደ ከተማ ከእገሌ ዘንድ ሄዳችሁ። መምህር። ጊዜዬ ቀርቦአል፤ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ከአንተ ዘንድ ፋሲካን አደርጋለሁ ይላል በሉት አለ። ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ ፋሲካንም አሰናዱ።" ማቴ 26:17_19
"ፋሲካን በሚያርዱበት በቂጣ በዓል መጀመሪያ ቀን ደቀ መዛሙርቱ። ፋሲካን ትበላ ዘንድ ወዴት ሄደን ልናሰናዳ ትወዳለህ? አሉት።" ማር 14:12
"እንግዲህ ያለ እርሾ እንዳላችሁ አዲሱን ሊጥ ትሆኑ ዘንድ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ። ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና፤ ስለዚህ በቅንነትና በእውነት ቂጣ በዓልን እናድርግ እንጂ በአሮጌ እርሾ በክፋትና በግፍ እርሾም አይደለም።" 1 ቆሮ 5:7_8
እንደ Vine's Complete Expository መዝገበ ቃላት መሰረት የብሉይ እና የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ስለ "ፋሲካ" ( Easter ) ተብሎ በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው ቃል ስህተት ነው "Pascha" የቃል ትርጉሙ ከላይ እንደተገለጸው የቂጣ በአል (Passover) በአል እስራኤላውያን ከግብጽ ምድር የወጡበት ክብረ በአል ሲሆን ይህንን የቂጣ በአል የፋሲካ በአል እንዳልሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሐዋርያት ስራ ላይ በግልጽ ተጽፎ ይገኛል:: "አይሁድንም ደስ እንዳሰኛቸው አይቶ ጨምሮ ጴጥሮስን ደግሞ ያዘው። የቂጣ በዓልም ወራት ነበረ። በያዘውም ጊዜ ወደ ወኅኒ አገባው ከፋሲካም በኋላ ወደ ሕዝብ ያወጣው ዘንድ አስቦ እያንዳንዱ አራት ወታደሮች ሆነው እንዲጠብቁት ለአራት ጭፍራ ክፍል አሳልፎ ሰጠው። ሐዋ 12: 3_4
የ"ፋሲካ" ( Easter ) የተጀመረው በክርስቲያኖች አይደለም! ነገር ግን የ"ፋሲካ" ( Easter ) ቃሉ የመጣው "አሽታርት"Astarte ከሚለው የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙም "የልጆች አማልክት" (Chaldean goddess ) ወይም "የሰማይ ንግስት" ( the queen of heaven) ማለት ነው:: "Pascha" የቂጣ በአል (Passover) የክርስትያን በአል ሲሆን የክርስቶስ ሐዋርያቶችም በአዲስ ኪዳን ስርአት በአሉን ቀጥለውት ያከብሩታል:: የ"ፋሲካ" ( Easter ) ወይም "አሽታርት"Astarte የተጀመረው በአውሮፓውያን ሲሆን የባእድ አምልኮ ክብረ በአል ነው:: ልክ እንደ "ገና" ( Christmas ) በአል ሁሉ የፋሲካ ( Easter ) በአልን የክርስትያን በአል ለማስመሰል ከቂጣ በአል (Passover) እስራኤላውያን ከግብጽ ምድር የወጡበት ክብረ በአል ጋር አቆራኝተውት ያሳስቱበታል:: (1985, p. 192, "Easter").
"ፋሲካ" ( Easter ) አመጣጥ የጥንት ታሪክ
botticelli__birth_of_venus
"ፋሲካ" ( Easter ) በአል አከባበር የተጀመረው ትክክለኛው አመተ ምህረት ባይታወቅም ከኢየሱስ ክርስቶስ ውልደት በፊት እንዲሁም ኢየሱስ ክርስቶስ ምድር ላይ በነበረበት ዘመንም ሁሉ "ፋሲካ" ( Easter ) ይከበር እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ይናገራል:: የተለያዩ የ"ፋሲካ" ( Easter ) የበልግ ወር ክብረ በአል ማክበር በጥንት ግዜ በደንብ ይታወቅ የነበረ ሲሆን "አሽታርት"Astarte ወይም "ፋሲካ" ( Easter ) የሚለው ቃል የሚወክለው "የበልግ ወራት ሴት የዝሙት አማልክት" (the goddess of spring and fertility ) የሚለውን ሲሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲህ ተጽፎ ይገኛል::
"በኢየሩሳሌምም ፊት ለፊት በርኵሰት ተራራ ቀኝ የነበሩትን፥ የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን ለሲዶናውያን ርኵሰት ለአስታሮት ለሞዓብም ርኵሰት ለካሞሽ ለአሞንም ልጆች ርኵሰት ለሚልኮም ያሠራቸውን መስገጃዎች ንጉሡ ርኩስ አደረገ።" 1 ሳሙ 23:13
በተጨማሪም እንደ ቪነስ ወይም "አሽታርት"Astarte ወይም "ፋሲካ" ( Easter ) ተመስላ የምትመለከዋ የሴት ጣኦት "ሰመራሚስ" ወይም አይ ኤስ አይ ኤስ (ISIS) ወይንም "የሰማይዋ ንግስት" "the Queen of Heaven," ስትሆን እግዚያብሔር እስራኤላውያን እንዳያመልኳት አዟቸው እና አስጠንቅቆዋቸው ነበረ መጽሐፍ ቅዱስም እንደዚህ ይላል::
"ያስቈጡኝ ዘንድ፥ ለሰማይ ንግሥት እንጐቻ እንዲያደርጉ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥ ቍርባን እንዲያፈስሱ ልጆች እንጨት ይሰበስባሉ፥ አባቶችም እሳት ያነድዳሉ፥ ሴቶችም ዱቄት ይለውሳሉ።" ኤር 7:18
astarte_03
diana-of-ephesus-statue-modern2-SS-MDE

"ኤርምያስም ለሕዝቡ ሁሉ ለሴቶቹም ሁሉ እንዲህ አለ። በግብጽ ምድር የምትኖሩ ይሁዳ ሁሉ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እናንተና ሚስቶቻችሁ በአፋችሁ። ለሰማይ ንግሥት እናጥን ዘንድ የመጠጥንም ቍርባን እናፈስስላት ዘንድ የተሳልነውን ስእለታችንን በእርግጥ እንፈጽማለን አላችሁ በእጃችሁም አደረጋችሁት፤ እንግዲህ ስእለታችሁን አጽኑ ስእለታችሁንም ፈጽሙ። እናንተ በግብጽ ምድር የምትኖሩ ይሁዳ ሁሉ፥ ስለዚህ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ በግብጽ ምድር ሁሉ በሚኖር በይሁዳ ሰው ሁሉ አፍ ስሜ ከእንግዲህ ወዲህ። ሕያው እግዚአብሔርን! ተብሎ እንዳይጠራ፥ እነሆ፥ በታላቅ ስሜ ምያለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። እነሆ፥ ለመልካም ሳይሆን ለክፋት እተጋባቸዋለሁ፤ በግብጽም ምድር ያሉት የይሁዳ ሰዎች ሁሉ እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍና በራብ ያልቃሉ። ከሰይፍም የሚያመልጡ ጥቂት ሰዎች ሆነው ከግብጽ ምድር ወደ ይሁዳ ምድር ይመለሳሉ፤ ሊቀመጡም ወደ ግብጽ ምድር የገቡት የይሁዳ ቅሬታ ሁሉ ከእኔ ወይም ከእነርሱ የማናችን ቃል እንዲጸና ያውቃሉ።" ኤር44:24_28
ፕሮፌሰር ፍራንሲስ ዊዘር የተባሉ የቦስተን ኮሌጅ ፊሎሶፈር እንዲህ ይላሉ:: እውነቱን ለማቅረብ ካስፈለገ "ፋሲካ" ( Easter ) እንቁላል ክብረ በአል መሰረት ያደረገው ባህላዊ የሴት የመራቢያ (ዝሙት) ወቅት ነው ብለው ያምናሉ:: በተጨማሪም "ፋሲካ" ( Easter ) የጀመሩት ኢንዶ-ኢሮፓውያን ሲሆኑ በዚህ ወቅት በአሉን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ባህላዊ ውድድሮች ይደረጋሉ:: በተጨማሪም በዚህ "ፋሲካ" ( Easter ) በበልግ ወቅት ልጆች በብዛት ይወለዳሉ እንዲሁም ማንኛውም ምርትም ሆነ ሀብት ተትረፍርፎ ይገኛል ብለው ያምናሉ:: በ"ፋሲካ" ( Easter ) በጥንቸል የተመሰለው ዋና ምክንያቱ ጥንቸል ከየትኛውም እንሰሳ ለመራባት በጣም ፈጣን እንሰሳ ናት ይሉናል ፕሮፌሰሩ ( Handbook of Christian Feasts and Customs, 1958 pp. 233, 236) "Fertility Symbols: Beneath the Dignity of God" on page 22).
የመራባት (ዝሙት) ሀይማኖታዊ ክብረ በአል ከክርስትያን ሀይማኖት ጋር አቆራኝቶ ክብረ በአልን ማክበር የቅርብ ግዜ ታሪክ ነው:: አዳም እና ሔዋን ከገነት እግዚያብሔር ካስወጣቸው ቡኋላ (ዘፍ 3) ሰብአዊነት ሌላ መልክ ይዞ ኖሯል:: የተፈጥሮ ሀይል እና ወቅቶች እንደመጀመሪያው እንደ እግዚያብሔር ሀሳብ እና እቅድ ሊሆኑ አልቻሉም:: ስለሆነም ጣኦታት (goddesses) እና የጥንቆላና : የመተት እና እንደ አስማት የመሳሰሉት የባእድ አምልኮ የተለየ ሀይል ያላቸው ጣኦታት ይመለካሉ ይፈራሉም:: የሰው ልጅ የእራሱን አምላክ ፈጠረ፣ስለዚህ እግዚያብሔር ከሰራው ስራ ጋር ግጭት እና ያለመስማማት ተፈጠረ:: ለዚህም ደግሞ የዝሙት ጣኦትን የሰው ልጅ ማምለክ ጀመረ::
aphrodite_by_lilok_lilok-d28qzxl
"ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ። በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ። አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም፤ በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤ ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና።" ዘፀ 20:3_6
"እኔ የእግዚአብሔርን ቃል እነግራችሁ ዘንድ በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔርና በእናንተ መካከል ቆሜ ነበር፤ እናንተ በእሳቱ ምክንያት ፈርታችኋልና፥ ወደ ተራራውም አልወጣችሁምና። እርሱም አለ። ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ። ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ። በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፤ በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤ ለሚወድዱኝ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኛና አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም።" ዘዳ 5:5_10
የባእድ አምልኮ ማህበረሰብ የሚያመልኮቸውን ጣኦታት በሀውልት እና በስእል መልክ ሰርተዋቸው ያመልኳቸዋል:: አብዛኞቹ የባእድ አምልኮዎች የሚወከሉት በእንሰሳ እና በሰው ልጅ ተመስለው ነው:: አንዳንድ ግዜ ጣኦታቶች በሚታዩ የተፈጥሮ ሀይሎች ተመስለው ይመለካሉ:: ለምሳሌ በፀሐይ፣በጨረቃ እና በኮከብ እንዲሁም በተፈጥሮ ሀይል ማለትም በባህር፣በዝናብ አሊያም በህይወት ሀይል ማለትም በሞት እና በእውነት ተመስለው ይመለካሉ::
"በግዜ ውስጥ ብዙ የተፈጥሮ ሀይል ኡደት እንደሚያድግ የሚታመን አስተምሮ አለ:: የተወሰኑት የስልጣኔ እና የባህል የራሳቸው አስተምህሮ የአወቃቀር ህግ አላቸው:: ነገር ግን የሁሉም የአወቃቀር ህጋቸው አንድ አይነት ነው:: የአምላክ ስሞች የተለያዩ ናቸው:: ነገር ግን እነዚህ የተለያዩ አምላኮች አሰራራቸው እና ድርጊታቸው አንድ አይነት ነው:: በጣም የታወቀ አስፈላጊ የጥንት ታሪክ አቋርጦ የሚያልፈው መስመር ባህልን ሲሆን ይህ መስመር የመራባት ኡደት ነው:: በብዙ የባእድ (pagan ) የባህል አምልኮ ውስጥ በየአመቱ በቀዝቃዛው የክረምት ወራት የአምላክ መራቢያ ይሞታል ተብሎ ይታመናል:: ነገር ግን ይህ በክረምቱ የሞተው የአምላክ መራቢያ ክረምቱ ከወጣ ቡኋላ ዳግም በበልግ ወር እንደገና መራባት (ዝሙት) ይጀምራል ተብሎም ይታመናል:: በሁለቱም መካከል ያለው ልዩነት የባህል ሲሆን ነገር ግን ዋናው ሀሳባቸው ግን አንድ አይነት ነው::" ( Nelson's New Illustrated Bible Dictionary, 1995, "Gods, Pagan," p. 508).
20130603nw863
በባእድ (pagan ) አምልኮ አስተምሮ ፀሐይ የምትወክለው ህይወትን ነው:: በጨለማው የክረምት ወቅት ፀሐይ ለተወሰነ ግዜ ትሞታለች:: በአመቱ በጣም አጭሩ የብርሀን ወቅት ግዜ ( የጥንት የባእድ አምልኮ ታሪክ መሰረት የ"ገና" Christmas በአል ቀን እንደሚከበረው "ዩል" ተወለደ ወይንም ንጉስ ናምሩድ የተወለደበት ቀን ነው ዲሴምበር 25 እንደሚባለው "ፋሲካ" Easter በበልግ ወቅት ልጆች በብዛት ይወለዳሉ ) የሚል አስተምህሮ ነው "ፋሲካ" ( Easter ) ማለትም እንደገና ፀሐይ ዳግም ስትወለድ ( ክረምቱ አብቅቶ የበልግ ወቅት ሲመጣ) የሰው ልጅም ሆነ የፍጥረታት የመራቢያ ወር ሀይማኖታዊ ክብረ በአል ነው:: ስለዚህም ሁል ግዜ "ፋሲካ" Easter ክብረ-በአል በመላው አለም በየአመቱ ይከበራል ::
celebrate-easter-world-easter-egg
በተጨማሪም "ጥንቸል" እና "እንቁላል" ሌላይኛው ተወዳጅ "ፋሲካ" Easter በአል ምግብ የተጀመረው በመጀመሪያዎቹ ክርስትያኖች ነው:: "በተጨማሪም በአውሮፓ እና በአሜርካ የአሳማ ስጋ በ"ፋሲካ" Easter ወቅት ተወዳጅ ምግብ ነው:: ምክንያቱም አሳማ በጥንት የአውሮፓውያን የመጀመሪያዎቹ ክርስትያኖች ባህል መሰረት የእድል መገለጫ ተደርጎ ይወሰዳል:: (The Encyclopedia of Religion, 1987, p. 558, "Easter").
ጥንታዊ የ "ዝሙት" ሀይማኖታዊ የአምልኮ ባህል
ጥንታዊ የመራባት (ዝሙት) ሀይማኖታዊ የአምልኮ ባህል ለአብዛኛው ማህብረተሰብ እንግዳ እና ሞራለ-ቢስ የሆነ በግልጽ የአደባባይ የዝሙት እርኩሰት ይደረጋል:: እንደ የዝሙት እርኩሰት ያሉ ጸያፍ ድርጊቶች ታሪክ በግልጽ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች እና በተለያዩ ስሞች እየተጠራ በጣም ለብዙ ግዜ ተጽፎ ይገኛል::
Pagan_god_Astarte
የባቢሎናውያን እና የአሴራውያን የመራባት (ዝሙት) አማልክት "ኢሽታር" Ishtar ወይም ( Easter ) "ፋሲካ" በመባል ትታወቃለች:: ስሙንም የተገኘው "እስታሮት" እና "አሽታሮታ" እና በጣም እንደነሱ የሚመስሉ "አንግሎ-ሳአክሰን ኢኦስተር" ወይም "ጀርመኒክ ኦስታራ" ከሚባሉ የበልግ ወር አማልክቶች ነው:: "ኢሽታር"( Easter ) የተባለው ቃል የተገኘው ከጸሐይ መውጫ የምስራቅ (east) አቅጣጫ ማለት ነው:: ሀሰተኛው ክርስቶስ የሚገለጠው ከጸሐይ መውጫ በስተምስራቅ (east)አቅጣጫ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በግልጽ ተጽፎ ይገኛል:: "ስድስተኛውም ጽዋውን በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከፀሐይም መውጫ ለሚመጡ ነገሥታት መንገድ እንዲሰናዳላቸው ውኃው ደረቀ።" ራዕ 16:12
"ኢሽታር" Ishtar ወይም ( Easter ) "ፋሲካ" የምትወክለው የ "ምድር እናት" የተፈጥሮ የመራባት (ዝሙት) ኡደት በምድር ላይ የሚለውን ነው:: ብዙ ጥንታዊያን ታሪኮች ያደጉት በሴት የመራባት (ዝሙት) አማልክት ነው:: እርሷ የፍቅር አማልክት ናት በተጨማሪም የሴተኛ አዳሪነት በአለም ላይ የተስፋፋው እና የመራባት (ዝሙት) አምልኮ የተስፋፋው በ"ኢሽታር" Ishtarወይም ( Easter ) "ፋሲካ" ስም ነው::
"ኢሽታር" Ishtar ወይም ( Easter ) "ፋሲካ" ቤተ መቅደስ ብዙ ቄሶች ወይም ከእርሷ ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያላቸው ሴተኛ አዳሪዎች አሉዋት:: እርሷ የምትመሰለውም በመራባት (ዝሙት) ሀይማኖት የምድርን የተፈጥሮ ኡደት መጠበቅ ነው::
"ኢሽታር" Ishtar ወይም ( Easter ) "ፋሲካ" ቀድሞ የምትታወቅበት "ፎኔሽያን አስታሮት" ፣ "የሴማቲክ አሽተሮታ" እና "ሰመሪያን ኢናና" በሚሉ የቀድሞ መጠሪያዎቿ ትታወቃለች:: በተጨማሪም በግብጽ አይ ኤስ አይ ኤስ (Isis) ፣ በግሪክ አፍሮዳይት እንዲሁም በሮም ቪነስ በመባል በሌሎች ስሞቿ ትታወቃለች::
litha_color_by_jess_foxx_quinn-d7dpwr3
""ኢሽታር" Ishtar ወይም ( Easter ) ፋሲካ "ታሙዝ" ከሚባል ወጣት አማልክት ጋር አንድ ላይ በመሆን ትመለካለች:: "ወደ ሰሜንም ወደሚመለከተው ወደ እግዚአብሔር ቤት በር መግቢያ አመጣኝ፤ እነሆም፥ ሴቶች ለተሙዝ እያለቀሱ በዚያ ተቀምጠው ነበር።እርሱም። የሰው ልጅ ሆይ፥ ይህን አይተሃልን? ደግሞ ተመልሰህ ከዚህ የበለጠ ርኵሰት ታያለህ አለኝ።" ሕዝ 8:14_15 መታወቅ ያለባቸው በዚህ በትንቢተ ሕዝቃኤል ቃል ሁለቱም መለኮቶች ሞተዋል:: በባቢሎናውያን አስተምህሮ "ታሙዝ" አመቱን ሙሉ ይሞትና በየአመቱ ደግሞ እንደገና ይወለዳል:: ይህ የሚወክለው የአመቱን የወቅቶች መፈራረቅ እና የሰብል የሚሰበሰብበትን ወቅቶች አምሳያ ነው "ታሙዝ" ይህ የባእድ አምልኮ እምነት የሚታወቀው የባእድ አማልክት የሆነው "ቤል" እና "አናት" አንድ ላይ በመሆን ነው:: ( Nelson's New Illustrated Bible Dictionary, "Gods, Pagan," p. 509)
ሁል ግዜ በመጽሐፍ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን መጽሀፍ ውስጥ እግዚያብሔር የራሱን ህዝብ የውሸት አምላክ የሆኑትን አማልክቶች ሲከተሉ ብዙ ግዜ በቁጣ ቃል ሲናገራቸው እናነባለን::
"እግዚአብሔርንም ትተው በኣልንና አስታሮትን አመለኩ። የእግዚአብሔርም ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፥ ወደ ማረኩአቸውም ማራኪዎች እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ በዙሪያቸውም ባሉት በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፥ ጠላቶቻቸውንም ከዚያ ወዲያ ሊቋቋሙ አልቻሉም።" መሳ 2:13_14
"የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ በኣሊምንና አስታሮትን የሶርያንም አማልክት፥ የሲዶናንም አማልክት፥ የሞዓብንም አማልክት፥ የአሞንንም ልጆች አማልክት፥ የፍልስጥኤማውያንንም አማልክት አመለኩ፤ እግዚአብሔርንም ተዉ፥ አላመለኩትምም። የእግዚአብሔርም ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፥ በፍልስጥኤማውያንና በአሞን ልጆች እጅ አሳልፎ ሰጣቸው።" መሳ 10:6_7
"ሰሎሞንም የሲዶናውያንን አምላክ አስታሮትን፥ የአሞናውያንንም ርኵሰት ሚልኮምን፥ ተከተለ። ሰሎሞንም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገርን አደረገ፥ እንደ አባቱም እንደ ዳዊት እግዚአብሔርን በመከተል ፍጹም አልሆነም። በዚያን ጊዜም ሰሎሞን ለሞዓብ ርኵሰት ለካሞሽ፥ ለአሞንም ልጆች ርኵሰት ለሞሎክ በኢየሩሳሌም ፊት ለፊት ባለው ተራራ ላይ መስገጃ ሠራ። ለአማልክቶቻቸው ዕጣን ለሚያጥኑ መሥዋዕትም ለሚሠዉ ለእንግዶች ሚስቶቹ ሁሉ እንዲሁ አደረገ። ሁለት ጊዜም ከተገለጠለት፥ ሌሎችንም አማልክት እንዳይከተል ካዘዘው ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ልቡን አርቆአልና፥ እግዚአብሔርም ያዘዘውን ነገር አልጠበቀምና እግዚአብሔር ሰሎሞንን ተቈጣ። እግዚአብሔርም ሰሎሞንን አለው። ይህን ሠርተሃልና፥ ያዘዝሁህንም ቃል ኪዳኔንና ሥርዓቴን አልጠበቅህምና መንግሥትህን ከአንተ ቀዳድጄ ለባሪያህ እሰጠዋለሁ።" 1 ነገ 11:5_11
"ወደ ሰሜንም ወደሚመለከተው ወደ እግዚአብሔር ቤት በር መግቢያ አመጣኝ፤ እነሆም፥ ሴቶች ለተሙዝ እያለቀሱ በዚያ ተቀምጠው ነበር። እርሱም። የሰው ልጅ ሆይ፥ ይህን አይተሃልን? ደግሞ ተመልሰህ ከዚህ የበለጠ ርኵሰት ታያለህ አለኝ። ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ውስጠኛው አደባባይ አመጣኝ፥ እነሆም፥ በእግዚአብሔር መቅደስ መግቢያ ፊት በወለሉና በመሠዊያው መካከል ሀያ አምስት የሚያህሉ ሰዎች ነበሩ ጀርባቸውም ወደ እግዚአብሔር መቅደስ ፊታቸውም ወደ ምሥራቅ ነበረ፤ እነርሱም ወደ ምሥራቅ ለፀሐይ ይሰግዱ ነበር። እርሱም። የሰው ልጅ ሆይ፥ ይህን አይተሃልን? በዚህ የሚያደርጉትን ይህን ርኵሰት ያደርጉ ዘንድ ለይሁዳ ቤት ጥቂት ነገር ነውን? ምድሪቱን በግፍ ሞልተዋታል ያስቈጡኝም ዘንድ ተመልሰዋል፤ እነሆም፥ ቅርንጫፉን ወደ አፍንጫው አቅርበዋል። ስለዚህ እኔ ደግሞ በመዓት እሠራለሁ፤ ዓይኔ አይራራም እኔም አላዝንም፤ ወደ ጆሮዬም በታላቅ ድምፅ ቢጮኹ አልሰማቸውም አለኝ።" ሕዝ 8:14_18
ማጠቃለያ
በ"ገና" ( Christmas ) በአል ወቅት የሚመለከው እና ታላቅ ሀይማኖታዊ ክብረበአል የሚደረገው ለፀሐዩ ንጉስ ለናምሩድ የውልደት ልደት ሲሆን እንዲሁ ሁሉ የፋሲካ ( Easter ) በአልም ምክንያት ሆኖ የምትመለከውና በአሉ የሚከበርላት የናምሩድ ሚስት እና እናት የሆነችው ሰመራሚስ ወይንም "ኢሽታር" Ishtar ወይም ( Easter ) "ፋሲካ" ቀድሞ የምትታወቅበት "ፎኔሽያን አስታሮት" ፣ "የሴማቲክ አሽተሮታ" እና "ሰመሪያን ኢናና" በሚሉ የቀድሞ መጠሪያዎቿ ትታወቃለች:: በተጨማሪም በግብጽ አይ ኤስ አይ ኤስ (Isis) ፣ በግሪክ አፍሮዳይት እንዲሁም በሮም ቪነስ በመባል በሌሎች ስሞቿ ትታወቃለች:: በተጨማሪም "ኢሽታር" Ishtar ወይም ( Easter ) "ፋሲካ" በመጨረሻው ዘመን የምትገለጠዋ ሴሰኛዋ ታላቂቱ ጋለሞታ የምድር እርኩሰት ይህችው "ኢሽታር" Ishtar ወይም ( Easter ) "ፋሲካ" ናት ይሉናል የመጽሐፍ ቅዱስ አጥኚዎች ስለሆነም ትክክለኛው በመጽሐፍ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን እንዲሁም በአዲስ ኪዳን የሚከበረው በአል የቂጣ በአል ወይም (Passover) እስራኤላውያን ከግብጽ ምድር የወጡበት ክብረ በአል ብቻ ነው:: እንጂ የፋሲካ ( Easter ) በአል እውነተኛ ክርስትያኖች እንዲያከብሩት የእግዚያብሔር ቃል አያዝም:: ቢሆንም አንዳንድ ሀይማኖቶች እኛ የምናከብረው የፋሲካ ( Easter ) በአልን ሳይሆን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በአልን ነው ብለው እራሳቸውን ያታልላሉ:: ምክንያቱም እውነተኛ ክርስትያን የክርስቶስን ትንሳኤ አምኖ ህይወት ሆኖት ይኖርበታል እንጂ ምክንያት አድርጎ ፊንጢጣው እስኪገለበጥ አይበላበትም ፣ ጢምቢራው እስኪዞር አይጠጣበትም ፣ ጨርቁን እስኪጥል በዘፈን አይጨፍርበትም በተጨማሪም አስጸያፊና ልቅ የሆነ የዝሙት መዝናናት ውስጥ አይኖርበትም በተጨማሪም የትንሳኤም ሆነ የገና ልደትን ክርስትያን እንዲያከብር የእግዚያብሔር ቃል አያዝም!
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment