የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢትዮጵያ ወይስ ...?

ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ


የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ወደ ቻይና የሚያደርገውን በረራ አለማቋረጡን ይገርማል ። ሌሎች አየር መንገዶች ሁሉ ወደ ቻይና የሚያደርጓቸውን በረራዎች ሁሉ አቁመዋል። ከአፍሪቃ እንኳ አምስት አየር መንገዶች ወደ ቻይና የሚያደርጉትን በረራ አቋርጠዋል።

የኬንያ፣ የሩዋንዳ፣ የማዳጋስካር፣ የሞሪሸስ እና የሞሮኮ አየር መንገዶች ወደ ቻይናና ከቻይና ያደርጓቸው የነበሩትን ሁሉንም ጉዞዎች ለጊዜው ማቆማቸውን አስታወቀዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ብቻ ይበርራል ማለት ነው።

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሓኖምን የዓለም ጤና ድርጅት ሃላፊ አድርገው ሾሟቸው፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድን የበረራ አድማስ በማስፋት በአፍሪቃ ትልቁ አየር መንገድ እንዲሆን ፈቀዱለት...ነጠብጣቦቹን እናገናኝ።

ከሁለት ዓመታት በፊት የሚከተለውን ጽሑፍ አቅርቤ ነበር፦

"በጥቁር ሕዝቦች ላይ ያነጣጠረው ‘ኢቦላ’ እንደገና አገርሽቷል | ዶ/ር ቴዎድሮስን ያለምክኒያት መርጠዋቸዋልን?”

...በሌላ በኩል፡ አውሮፕላኖች እንደ ኢቦላ የመሳሰሉ ቫይረሶችን በፈጠነ መልክ ለማሰራጨት አስተዋጽኦ ያበረክታሉ የሚለውን መረጃ ሳነብ፡ የታየኝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው። ሁሌ የምጠይቀው፡ ከጥንት ጀምሮ፣ በማንኛውም የኢትዮጵያ መንግስታዊ መስተዳደር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያለምንም ተንኮልና መሰናክል እንዲያድግና እንዲስፋፋ መደረጉ ከምን የመጣ ይሆን? የሚለው ጥያቄ ነው።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment