ድንዛዜ እስከ መቼ ?

ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
እህቶቻችን ከጠፉ ዛሬ ልክ ፹፩ (ሰማንያ አንድቀን ሆኗቸዋል።
ክትናንት በስትያ ቅዳሜ በመስቀል አደባባይ ወደ ተካሄድው የቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ድግስ የአዲስ አበባ ወጣቶች ምን ፈልገው፣ ምን አቅደው እንደሄዱና ለገራቸውም ምን በጎ ነገር እንዳመጡም የማውቀው ነገር የለም። ነገር ግን እቶቻችን ከደንቢደሎ መካነ አዕምሮ (ዩኒቨርሲቲ) እልም ብለው በጠፉበት ማግስት፤ ተዋሕዶ የአዲስ አበባ ልጆች በቤተ ክርስቲያናቸው ውስጥ በግፍ በተረሸኑበት ማግስት፤ ጌታችን በተሰቀለበት መስቀል ስም በተሰየመበት ቦታ ላይ ለዳንኪራ እና ጭፈራ በመውጣት የመምህር ምሕረተአብን የማንቂያ ደወል ለማቆምና የገዳይ ግራኝ ዐቢይ አሕመድ አጀንዳ ለማስፈጸም ወጥተው ከሆነ እጅግ በጣም ነው የማዝነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠን የመስቀል ስር ስጦታ የሆነችው ውዷ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም እንደ እናትነቷ አብዝታ ታዝንባቸዋለች።
ይህ ዕለት እናታችን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ከልጇ ቃል ኪዳን የተቀበለችበት ቀን ነው። የእመቤታችን ቃል ኪዳን ለየት ያለ ነው። ለየት የሚለውም በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ነው። የመጀመሪያው እርሷ ምልዕተ ፀጋ በመሆኗና ፍጽምት ርህርህተ ሕሊና ከመሆንዋ የተነሣ ስለ ሰው ልጆች አብዝታ የማለደች እናት እና ክርስቲያኖች ሁሉ ይድኑ ዘንድ ከሌሎቹ በተለየ የለመነች በመሆንዋ ነው። እንኳን እግዚአብሔር ጨካኙ ዳኛ እንኳን አብዝታ ለለመነችው መበለት ያደረገውን እናውቃለንና።(ሉቃ፲፰፡፩-)
ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ወላዲተ አምላክ ለመባል የበቃች ከእርስዋ በቀር ሌላ የሌለ፤ በዚህም መልዕልተ ፍጡራን ትሆን ዘንድ አምላክ ያከበራት በመሆንዋ ልዩ ቃል ኪዳን ይገባላት ዘንድ የተገባት ናት። ለአምላክ እናትነት(ልዩሆና መመረጧን ለሚያምን ሁሉ ልዩ ቃል ኪዳን መቀበሏ ጥያቄ አይሆንበትም። ስለዚህም ልዩ ቃል ኪዳን ተገብቶላታል። ነቢዪ ኢሳይያስ ወይወጽእ እምጽዮን መድኅን ወየዐትት ኃጢአተ እም ያዕቆብ ወዛቲ ይእቲ ኪዳኖሙ እንተ እምኀቤየ ይቤ እግዚአብሔር፦ መድኅን (ክርስቶስከጽዮን ይወጣል (ከእመቤታችን ይወለዳል)፣ ኃጢአትንም ከያዕቆብ (ከእስራኤል ዘነፍስያርቃል፤ ለእስራኤል የማልሁላቸው መሐላ የገባሁላቸው ቃልኪዳንም ይህቺ ናት፤ ሲል እንደተናገረ እግዚአብሔር ልዩ ውልና ስምምነት ከእስራኤል ዘነፍስ ጋር አለው።(ኢሳ.፶፱፡፳-፳፩ከዚህ ውስጥ አንዱና ዋናው ከእመቤታችን ጋር ያደረገው ነው።
ይህ ኪዳን ልዩ ከሆነበት ነገሩ አንዱ የራሱ መታሰቢያ ዕለት ያለው መሆኑ ነው። ዕለቱም ጌታችን በጌቴሰማኒ ተገልጾ ኪዳኑን የገባበት ዕለት ነው፤ ይኸውም የካቲት ፲፮ ቀን ነው። እመቤታችን ከላይ እንደተገለጸው ወደ ጎልጎታ ወደ ጌታ መቃብር እየሄደች አብዝታ ትለምን ነበር። በዚህም ምክንያት መላእክት ወደ ሰማያት አሳርገው ገነትንና ሲዖልን አስጎብኝተዋታል። እርስዋም በሲዖል ያሉ ነፍሳትን አይታ በእጅጉ አዝናላቸዋለች፤ ከዚህም በኋላ ስለ ኃጥአን አብዝታ ስትለምን ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚች ዕለት ተገልጾ ልዩ የምሕረት ቃልኪዳን ስለገባላት ኪዳነ ምሕረት እየተባለች ትከበራለች።
እኛም ከዚህ እጅግ ሊያስተውሉት ከሚገባ ታላቅ መልእክት የምናገኘው ትልቅና ታላቅ ቁም ነገር እግዚአብሔር ከመረጣቸውና ካከበራቸው ጋር እንዴት ቃል ኪዳን እንደሚያደርግ ሲሆን አብዝተው ለጠየቁትና ለተማጸኑት የቅርብ አምላክ እንጂ የሩቅ አምላክ አለመሆኑን ማሳየቱና ጸሎታቸውንና ልመናቸውን ሰምቶ ምላሽ መስጠቱን ነው። ስለሆነም አምላካችን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ኪዳን ከገባላት የመስቀል ስጦታ እናታችን በረከትን ለማግኘት ዘወትር በተሰበረ ልብና በተዋረደ መንፈስ መቅረብ ያስፈልጋል። ነቢዩ ኤርምያስ “አቤቱ የሆነብንን አስብ” ብሎ እንደጮኸው ጩኸት እያንዳንዳችን የምሕረት ቃል ኪዳንን ወደተቀበለች ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንቅረብ። ልዑል እግዚአብሔር ንጉሥ ሰሎሞንን ስለ አባትህ ስለ ዳዊት ስል በትረ ንግሥናህን ከአንተ አልወስድም ብሎ ቃል እንደገባለት እኛም የዘላለም ቃል ኪዳን ስለገባላት ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ሲል እንዲምረን ፍጹም ትህትናን ገንዘብ አድርገን እግዚአብሔር ያከበራቸውን አክብረን መገኘት ይኖርብናል። በዚህ ታላቅ ፆምም በረከትን ለማግኘት ፆማችንን ከግብር ጋር አገናኝተነው ደካሞች የሚረዱበትን፣ ታማሚዎች የሚጠየቁበትን፣ እስረኞች የሚጎበኙበትን፣ የታረዙ የሚለብሱበትን፣ የተራቡ የሚጠግቡበትን፣ የተጠሙ የሚጠጡበትን መንገድ ለማመቻቸት የተዘጋጀን መሆን ይኖርብናል። ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው ብሎ ሐዋርያው ያዕቆብ እንደተናገረ እኛም ፆምንና ምፅዋትን አስማምተን ለበጎ ሥራ የተዘጋጀን እንድንሆን አምላካችን በቸርነቱ ይርዳን፤ እመቤታችን በተገባላት ቃል ኪዳን ትጠብቀን።
ወ ስ ብ ሐ ት ለ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment