ግራኝ ዐቢይ አሕመድ በድሃው ሕዝብ ገንዘብ ወደ ጠላቶቻችን ዓረብ ሀገራት ሄዶ መንሸራሸሩን መርጧል


ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

[ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፬፥፱፡፲፪]

" እግዚአብሔርም ቃየንን አለው፦ ወንድምህ አቤል ወዴት ነው? እርሱም አለ፦ አላውቅም የወንድሜ ጠባቂው እኔ ነኝን? አለውም፦ ምን አደረግህ? የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል። አሁንም የወንድምህን ደም ከእጅህ ለመቀበል አፍዋን በከፈተች በምድር ላይ አንተ የተረገምህ ነህ። ምድርንም ባረስህ ጊዜ እንግዲህ ኃይልዋን አትሰጥህም፤ በምድርም ላይ ኰብላይና ተቅበዝባዥ ትሆናለህ።"

ፀሎት የሚያደርሱ የተዋሕዶ ልጆች በቤተ ክርስቲያናቸው ውስጥ እየተረሸኑ ባሉበትና ዕልባት ያልተገኘለት የታገቱት አስራ ሰባት ወጣት ሴት ተማሪዎች ጉዳይ ኢትዮጵያውያንን እስትንፋስ እንዲያጡ ባደረገበት በዚህ ጊዜ፤ ይህ ወሮበላ ሰው በድሃው ሕዝብ ገንዘብ ወደ ጠላቶቻችን ዓረብ ሀገራት ሄዶ መንሸራሸሩን መርጧል።  ምን ዓይነት እርጉም ትውልድ ቢሆን ነው ከዚህ ገዳይ ጋር ለመገናኘት ወደ ስታዲየም የሚሄድ?!

ይብላኝ ለልጆቹና ለተከታዮቹ! ለእኛስ እግዚአብሔር አምላካችን ይህን ቅዠታም አፉን ከፍቶ እንዲለፈለፍ እያደረገልን ነው። የንጹሃን ደም እንደ ቃኤል፣ የእናቶች እንባ ገና ብዙ ያስለፈልፉታል።

እስኪ ተመልከቱ፡ ፣ "ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ""የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ"፣ "አባትህንና እናትህን አክብር "፣ "አትግደል" ፣"አትስረቅ"፣ "በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር"፣ "የባልንጀራህን ቤት አትመኝ..." የሚሉትን የአማላካችን ትዕዛዛት ሁሉ አንድባንድ እየካደ፣ እንደሆነ በጄነራል አሳምነው ጉዳይ ብቻ በግልጽ አይተነዋል። ሌላው የሚገርመው ደግሞ ይህ ሀገሩንና የወጣበትን ሕዝብ የካደና መሰቀል የሚገባው ግለሰብ ዛሬም ተከታዮች ሊያገኝ መብቃቱ ነው። ቅሌታም ትውልድ! እነዚህ ተከታዮቹም እነደርሱ እግዚአብሔር አምላክንና ሀገረ ኢትዮጵያን የካዱ ውዳቂዎች መሆናቸውን እየተገነዘብን አይደሉምን? በደንብ እንጂ!


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment