ቤተ ክርስቲያን ለምን ዘፈንን አወገዘች???

1. ዘፈን የአጋንንት ሥራ ነው:: አጋንንት ይዘፍናሉና:: ለዚህ ምንም ማስተባበያ አያስፈልገውም:: መጽሐፍ ቅዱስ "በዚያም አጋንንት ይዘፍናሉ" በማለት ስለ አጋንንት
ዘፋኝነት ይናገራል::(ኢሳ.13:21) አትዝፈኑ ማለት የአጋንንትን ሥራ አትሥሩ ማለት መሆኑን እንረዳ:: ይህን በተመለከተ መጽሐፈ መቃብያን ደግሞ እንዲህ ይላል:-
"....እየዘፈኑም ከአጋንንት ጋር ይጫወቱ ነበር::

አጋንንትም ጫወታቸውንና ዘፈናቸውንም ሁሉ ያደንቁላቸው ነበር::" (1ኛ.መቃ.36፥27-28)

በዚህ ስፍራ አገላለጥ ደግሞ ለየት የሚለው አጋንንት ዘፋኞች ብቻ ሳይሆኑ ከዘፈን አድናቂዎች ጐራ መሰለፋቸው ነው::

2. ፍትሐ ነገሥት መንፈሳዊ ሥራን አስመልክቶ ሲናገር እንዲህ ይላል:- "ስለ ተግባረ ዕድ ግን በዓለም ከሚሠሩ ሥራዎች መንፈሳዊ ሕግን ከሚቃወም ሥራ በቀር ሁሉንም ሊሠሩ ይገባል:: ... እንደ ዘፋኝነት፥ እንደ መጥፎ ጫወታ፥
በእግር እንደ ማሸብሸብ(ዳንስና ጭፈራ) ካልሆነ በቀር ነው::" (ፍት.ነገ.መን.አን. 23:820)
ይህ የአበው ቃል ዘፋኝነት በመንፈሳዊ እይታ እንደ ሥራ መቆጠር እንደሌለበት ያስረዳል::

3. ዘፋኝነት "የሥጋ ሥራ" በመሆኑ ኃጢአት ነው::
(ገላ.5:21):: "በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ፤" ተብሏልና:: (ገላ.5:16)::

4. ዘፈን በመንፈሳውያን መጻሕፍት ተወግዟል:: ሐዋርያት በዲድስቅልያ "ኢትኩኑ ዘፈንያነ" ፥ "ዘፋኞች አትሁኑ" ብለዋል:: (ዲድስቅልያ፤ አንቀጽ 7) ቅዱስ ጳውሎስ "በቀን እንደምንሆን በአግባብ እንመላለስ:: በዘፈንና በስካር አይሁን" ብሏል:: (ሮሜ.13፥13) ቅዱስ ጴጥሮስ
ደግሞ "በስካርና በዘፈን የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል::" ይለናል:: (1ኛ.ጴጥ.4:3)::

መጽሐፈ ሐዊ ደግሞ "ከሰይጣን የተገኘ ነውና

ዘፈንንና ዳንስን ከኛ ማራቅ ይገባናል::" ይለናል:: (መጽ.ሐዊ አን. 50):: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ደግሞ ከማዘዝ አልፎ ዘፈንን እንተው ዘንድ "ዘፈንን ትተዉ ዘንድ እማልዳችሗለሁ፤" በማለት ይማጸናል:: (ተግ.ዘዮሐ.አፈ.28) ዘፈንን አንተውም
ላሉ ደግሞ መጽሐፈ ሐዊ "በዘፈን ጸንተው የሚኖሩ ይፈረድባቸዋል" በማለት ሲያስጠነቅቅ እናገኛለን:: (መጽ.ሐዊ.አን. 12)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment