የንስሐ ፀሎት



አቤቱ ፈጣሪዬ ሆይ አዳምን ከሲኦል ኖህን ከውሃ ጥፋት ይስሃቅን ከመታረድ እስራኤልን ከፈርኦን ዳዊትን ከሳኦል ኤልያስን ከኤልዛቤል መርዶክዮስን ከሀማ ሰለስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ያዳንክ አምላክ ሆይ እኔንም ባሪያህን ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ አድነኝ በዚህ አለም ስኖር ከረሃብ ከጥማት ከመሠደድ ከመንገላታት በሀይለኞችና በጨካኞች እጅ ከመውደቅ አድነኝ ለንስሐ ሞት አብቃኝ የሗላ ቤቴን አሳምርልኝ ከዳግም ሞት አድነኝ አሜን ፡፡

አቤቱ አምላኬ ሆይ ኢዮብን ከቁስል አላዛርን ከመቃብር ሕዝቅያስን ከሰናክሬም ዮናስን ከአሳ ነባሪ ምናሴን ከብረት ቀፎ ሙሴን ከዳታንና ከአቤሮን አሮንን ከደቂቀ ቆሬ ያዳንክ አምላክ ሆይ እኔንም ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ አድነኝ ፡፡

አቤቱ ጌታዬ ሆይ ዳንኤልን ከአፈ አናብስት ሶስናን ከእደ ረበናት ሎጥን ከሰዶምና ከገሞራ ዲቦራን ከሲሳራ ያእቆብን ከወንድሞቹ ሶምሶምን ከእርግውና ወደ ውርዝውና የመለስክ የበለአምን አህያ ያናገርክ ቶማስን ብልጣሶንን ያእቆብን ከቱርክ ያዳንክ እኔንም ባሪያህን ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ ሰውረኝ በንፅህና ሆኜ ቅዱስ ስጋህን እና ክቡር ደምህን እየተቀበልኩ ለመኖር ፍቀድልኝ ከዚህ አለም እሾህና አሜከላ አድነኝ አቤቱ ፈጣሪዬ ሆይ ሰማእቱ ጊዮርጊስን ከሰባ ነገስት ጦቢትን ከአይን ህመም ብሩክታዊትን ከአፈ ደራጎን እግዚሃርያን ከመቶሎሚ የአትናስያን ሞት ወደ ህይወት የመለስክ በላኤሰብን የማርክ አክሊለ ሶክን ያጠለቅክ በቅድመ አይሁድ እስራትና ግርፋትን ለቤዛ አለም የተቀበልክ በጾረ መስቀል በፍኖት አምስት ጊዜ የወደቅህ በፊትህም በሗላህም መራቀ አይሁድን የተቀበልክ በቀራንዮ በእለተ አርብ ደምህን ያፈሰስክ ስጋህን የቆረስክ ህማማተ መስቀልን የተቀበልክ የእውሩን አይን ያበራህ ለምፃሙን ያነጻህ ጎባጣን ያቀናህ ዲዳን ያናገረክ አንካሳን የፈታህ ባህርን ያናወፅክ ነፍስን የገሰፅክ ፴፰ አመት በአልጋ ቁራኛ የነበረውን መጻጉን ያዳንክ ያመኑብህን የማትጥል ሰማይና ምድርን በቃልህ ያቆምክ መአልቱን በሌሊት በጋውን በክረምት የምታፈራርቅ አካልህ የማይዳሰስ ቃልህ የመይገሸፅ መንግሥትህ አይሻር ከተሾምክ ያልተሻርክ የማትሻር ከተወለድክ የማታረጅ ያላረጀህ ከአለም በፊት የተገኘህ አለምን አሳልፈህ ለዘለአለም የምትኖር አልፋ ኦሜጋ ኤልሻዳይ አዶናይ ፀባኦት ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከክፋት ወደ በጎነት መልሰኝ ሀይል መዊእ ለዳዊት የሠጠህ ለእኔም ስጠኝ ዕድሜ ለማቱሳላ ፅድቅ ለቅዱስ ላሊበላ የሰጠህ ለእኔም እድሜ ለንስሐ ጽድቅ ለፍስሀ ስጠኝ መልአከ ጠባቂዬን አበርታልኝ ከሰው ከእግዚአብሔር የሚያስማማ ምግባር ስጠኝ በተወለድኩበት ሀገር ክፉ ነገር አታሳየኝ የመላእክት የሰማእታት የፃድቃን የነቢያትን የሐዋርያትን የምእመናንን የደብርን የገዳማትን የአእሩግን የህፃናትን የንጉስን የመሰተጋድልን ልመና ፀሎት የተቀበልክ አምላክ የእኔንም ልመና ፀሎት ስማኝ ተቀበለኝ መሐረኒ እመከራ ስጋ ወነፍስ እመከራ ዝንቱ አለም ሊተ ለገብርከ __________ወኩሎሙ ሰብአ ዓለም ለዓለም አሜን፡፡


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment