ዐቢይ አሕመድ እንደ በለዓም

ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ – “ና፥ ያዕቆብን ርገምልኝ፤ ና፥ እስራኤልን ተጣላልኝ” ብሎ በለዓምን ከምሥራቅ ተራሮች አስጠራው።
ባላቅ በአንድ ወቅት የሞዐብ ንጉስ የነበረ ሲሆን፤ በለዓም ግን ከሞዐብ ትንሽ ራቅ ያለ ሥፍራ ላይ ተቀምጦ በረጋሚነት የሚተዳደር ሰው ነበር፡፡ እስራኤላውያን ከግብጽ ወጥተው ወደ ከነአን ጉዞ መጀመራቸውን ተከትሎ በምድሩ እንዳያልፉ፡ በተለይም ከሰማው ዝናቸው አንጻር ሰግቶ በለዓምን አስመጥቶ በሙዋርት ሊያስረግማቸውና መንገድ ሊያስቀራቸው ሽቶ ነበር፡፡ በዚህ መልክ ነው እንግዲህ በለዓምን የሚያግባቡ ተለቅ ተለቅ ያሉ ሰዎች ተልከው ከቀናት በኋላ ተክተልትለው አብረው የደረሱት፡፡ ቢሆንም እቅዳቸው ሳይሰምር ቀረ፡፡ ለሦስት እና ለአራት ጊዜ ፈጽሞ መባረክ ብቻ እንጂ መርገም ከቶ አልተቻለም ነበረና፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር በስውር ለሕዝቡ እየተሟገተ ነበር፡፡ ምንም እንኳ በዘኁልቁ መጽሐፍ ላይ ሁለቱ ሰዎች በዚህ መልክ እንደተለያዩ ቢገልጽም፤ አዲስ ኪዳንን ጨምሮ በሌሎች ስፍራዎች ላይ በለዓም የሰራው ተንኮል ቁልጭ ብሎ ወጥቷል፡፡
በለዓም ሁለት መልክ ያለው፣ ሁለት ምላስ ያለው፣ ከባድ ሰው ነበር፡፡ ፊት ለፊት እስራኤልን ይመርቃል፣ ያደንቃል ፣ እግዚአብሔር በመካከላቸው ያለ ታላቅ ሕዝብ መሆኑን ይናገራል፣ ከአንበሳ ደቦል ጋር ያመሳስላቸዋል፣ ሞታቸውን እንኳ እኔ ልሙት ብሎ እስኪመኝ ደርሶ ይታያል/ዘኁ.2310……../፤ ዞር ብሎ ደግሞ የሚጠፉበትን፣ ተሰነካክለው የሚወድቁበትን ጉድጓዳቸውን ይቆፍራል፡፡ ያወቀውን ድካማቸውን አጋልጦ ሰጠድካማቸውን ፈጽመው እንዲወድቁበት ተጠቀመበት፤ ከፊት ጥሩ ስለሚናገር ማንም እርሱን ጠላት ነው ብሎ ሊፈርጀው አይደፍርም ከጀርባ ግን ሐሜት አለእየሳቀ የሚገድል ቀን ጠብቆ አሳልፎ የሚሠጥ ከባድ ሰው ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት መተት ያላጠፋው ሕዝብ፣ ሙዋርት ያልገደለው ሕዝብ፣ ከቶ እርግማን ሊሰራበት ያልቻለ፣ ሊረገምም ያለተቻለ የእግዚአብሔር ሕዝብ በድካሙ ምክንያት መንገድ ቀረ‹በአንድ ቀን ብቻ ሃያ አራት ሺህ ሰዎች ሞቱይለናል ዘኁ.25.9/፡፡
በለዓምም ከተራራ ላይ ሆኖ ሕዝቡን እያዬ፦“ …በአምቦች ራስ ላይ ሆኜ አየዋለሁ፥ በኮረብቶችም ላይ ሆኜ እመለከተዋለሁ፤ እነሆ፥ ብቻውን የሚቀመጥ ሕዝብ ነው፥ …ይህ ሕዝብ እንደ እንስት አንበሳ ይቆማል፥ እንደ አንበሳም ይነሣል…..” እያለ ባርኮቱን ቀጠለ።
ይህኔ ንጉሡ ተበሳጭቶ በለዓምን፦ “ይህን ሕዝብ እንድትረግምልኝ አስመጣሁህ፤ አንተ ግን ሦስት ጊዜ ባረካቸው፤ ምንድነው እየሠራህ ያለኸው?” ሲለው በለዓምም እንደሚከተለው መለሰለት፦” እግዚአብሔር ያልረገመውን እንዴት እረግማለሁአንተ እንድረግማቸው አስጠራኸኝ፤ ጥሪህን አክብሬ ያልከኝን ላደርግ መጣሁ፤እግዚአብሔር ግን የምርቃትን ቃል በአፌ አኖረ።”
እኛስ ከዚህ ምን እንማራለንእየሳቁ የሚገድሉ፣ ፊት ለፊት ጥሩ ነገር ያወሩና ከጀርባ ጉድጓድ የሚቆፍሩ …በተለይ እግዚአብሔር ቤት ውስጥ በርካቶች እንዳሉ ሲሰማ አያምም ወይዞረው የሚያሙ፣ ድካሙን እንዲያስተካክል ለወንድማቸው ከመናገር ይልቅ ለሌላው /ለገዳይአሳልፈው የሚሰጡ፣ በለዓም ለደሞዝ ተታሎ ይህን እንዳደረገ ተጠቅሷል፡፡ እንዲህ ባለ ምድራዊ ጥቅማ ጥቅም የሚታለሉ፣ እውነትን የሚሸቃቅጡ፣ ለሆዳቸው ያደሩ፣ እውነትን መጋፈጥ አንድ ቀን እንኳ የተሳናቸው፣ ዘላለማዊውን ነገር የረሱትን ይመስላል፡፡
ትንሽ ከፊት ሲሆን ሀገር ያሳንሳል
ታላቋን ኢትዮጵያን በመግዛት ላይ ያሉት በለዓማውያን ጠላቶቿም፡ ሕዝባችን እንደ እንስቲቱ አንበሳ ጋደም ሲል፤ የተኛና ያንቀላፋ እየመሰላቸው በግፍ ላይ ግፍ፣ በበደል ላይ በደል ሲፈጽሙበት በተደጋጋሚ ይስተዋላሉ። ከዚያም አልፈው “ተቆጣጥርነዋል፣ እንዳሰኘን መንዳት እንችላለን፣ ከእንግዲህ ጠራርገን በልተነዋል፤ ሀገራዊ (ኢትዮጵያዊ ስሜቱንጨርሰን አጥፍተነዋል።” ብለው የደመደሙባቸው አጋጣሚዎችም ጥቂት አይደሉም። ይሁንና የተስፋ ክር የሰለሰለበትና ሁሉ ነገር ያለቀለት በሚመስልበት ሰዓት ይህ እንደ እንስቲቱ አንበሳ ጋደም ያለው ሕዝብ ድንገት አፈፍ ብሎ “ኢትዮጵያ!” በማለት እየተነሳ ሲያስደነግጣቸው ይታያል።
“…ከፊት ጥሩ ስለሚናገር ማንም እርሱን ጠላት ነው ብሎ ሊፈርጀው አይደፍርም ከጀርባ ግን ሐሜት አለእየሳቀ የሚገድል ቀን ጠብቆ አሳልፎ የሚሠጥ ከባድ ሰው ነበር”
„ “….ሰዎች ጥቅም ወዳድ ናቸውና በጥቅም ሂድባቸውየሚፈልጉትን እያሳየህ ወደምትፈልገው ስፍራ ውሰድ እና ጣላቸው… ከዚያም በሬ ሆይሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ… ብለህ ተርትባቸው” ብሎን የለ በለዓም ዐቢይ አሕመድ አሊ
ባላቅ (ባራክ ሁሴን ኦባማ፥ በለዓም (ዐቢይ አሕመድ አሊ)
ሁለቱም የኖቤል ሰላም ሽልማት ተሸላሚዎች ናቸው፤ ሁለቱም ሙስሊሞች ናቸው፣ ሁለቱም ግብረሰዶማውያን ናቸው፣ ሁለቱም ለወርቅ እና ለጥቅም የሚኖሩ አታላዮች ናቸው፣ ሁለቱም እየሳቁ የሚገድሉ ቀን ጠብቀው አሳልፈው የሚሰጡ ከሃዲዎች ናቸው፣ ሁለቱም እንደ ጠዋት ጤዛ (Snowflakes) የሚርግፉ ናቸው።
ኢትዮጵያዊነት በነበለዓም እርግማንና ሟርት አይጠፋም! በሁለቱም ላይ እሳት ይወረድባቸዋል!!!
[የይሁዳ መልእክት ምዕራፍ ፩፥፲፩]
ወዮላቸው፥ በቃየል መንገድ ሄደዋልና ስለ ደመወዝም ለበለዓም ስሕተት ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል በቆሬም መቃወም ጠፍተዋል።”
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment