“ኦሮሞ ነን” የሚሉት ብልሹ ልሂቃን እጅግ በጣም አሳፋሪና በዝምታ የማይታለፍ ምሑራዊ ቀውስ ውስጥ መግባታቸው መታወቅ አለበት፤ አካሄዳቸው ልክ እንደ ጣልያን ፋሺስቶች፣ እንደ ጀርመን ናዚዎች፣ እንደ ሩዋንዳ ሁቱ እና ሰሜን ሱዳን እብዶች መሆኑን እያየን ነውና እንደ እስካሁኑ ሳንለሳለስ ቆንጠንጥ ብለን ልንዋጋቸው ይገባል። እስኪ እናስበው፤ ከአንድ ቢሊየን በላይ ቁጥር ላላቸው “ጥቁር” ሕዝቦች ኩራት የሚሆነውን ኢትዮጵያኛ ጽሑፍን፣ ባሕልንና ሃይማኖትን ለመዋጋት የኢትዮጵያን ጡት ለዘመናት ጠብተው ያደጉት ውርንጭሎች ደፋ ቀና ሲሉ።
ኢትዮጵያ ከሰማንያ በላይ ቋንቋዎች የሚነገሩባት ሀገር ነች። የእነዚህ ሁሉ ቋንቋዎች ተናጋሪዎች መብታቸው ተጠብቆ ቋንቋቸውን ያለምንም ገደብ እንዲናገሩ ያው እስከ ዛሬ ድረስ እንዲናገሩ የከለከላቸው የሰሜን መንግስት ወይም ሥርዓት የለም። ይህን መሰሉ መብት–ለጋሽነት፣ ዜጎች የማንነታቸው መገለጫ የሆኑትን ቋንቋዎችና ባሕሎች ጠብቀው እንዲኖሩ የሚያስችላቸው መብት በምዕራቡም ሆነ በአረብ ቱርክ ዓለም የለም፤ እነዚህ ሀገራት የአናሳ ብሔር ቋንቋዎችንና ባሕሎችን ባጭር ጊዜ ውስጥ ሊያጠፉ ችለዋል። በአሜሪካ ቀይ–ህንዳውያን ቋንቋዎቻቸውን አጥተዋል። አብዛኞቹ ነጭ አሜሪካውያን የጀርመን ዝርያ ያላቸው ሲሆኑ ጀርመንኛ ቋንቋቸውንም በእንግሊዝኛ እንዲተኩ ተገድደዋል። በቱርክ ሁሉም ነዋሪ ከቱርክኛ በቀር ሌላ ቋንቋ እንዳይነገር ተደርጓል፤ ሠላሳ ሚሊየን የሚጠጉ የቱርክ ኩርዶች እንኳን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ቋንቋቸውን መንገድ ላይ እንዳይናገሩ፣ በትምህርት ቤትና መንግስት ተቋማት እንዳይናገሩ ተደርገው ነበር። በአረቡ ዓለም ደግሞ ከአረብኛ ቋንቋ በቀር ሌሎች ብዙ የአገራቱ ቋንቋዎች ሙልጭ ብለው እንዲጠፉ ተደርገዋል።
በኢትዮጵያ ሃገራችን ግን በከፍተኛ ደረጃ ብቸኛ ጥቃት የደረሰበት ቋንቋ የኢትዮጵያ የሆነው የግዕዝ ቋንቋ ነው። በውጭ ሃገራት ተጽዕኖ እና በኢትዮጵያውያኑ ደካማነት ላለፉት መቶ ዓመታት በግዕዝ ቋንቋ ላይ አሳፋሪና ቅሌታማ የሆነ ጦርነት ተካሂዷል። ለምን? ተብሎ ቢጠየቅ፤ ግዕዝ የሰው ልጅ የመጀመሪያ ቋንቋ ስለሆነ እንዲሁም በመንፈሳዊ ኃይሉ ከማንኛውም የዓለማችን ቋንቋ (ከትግርኛ እና አማርኛ ሳይቀር)በጣም የላቀና ኃብታም የሆነ ድንቅ ቋንቋ በመሆኑ ነው። ቀናተኛው ዲያብሎስ የግዕዝን ቋንቋ አጥፍቶ ደካማ በሆኑ የራሱ ቋንቋዎች ለመተከታት ፍላጎት ስላለው ነው።
“የአዲሲቷ ኢትዮጵያ መሪዎች ነን” እያሉ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ላይ የሚያላግጡ ግብዞች ሆኑ እርሷን ለማጥፋት የተሰለፉ የተለያዩ ቡድኖችና ድርጅቶች እንዲሁም መንግሥታትና ተቋማት እንዲሁም ግለሰቦች ዛሬ ነገ ሳይሉ በእዉነተኛ ንስሐ ለእግዚአብሔር እጃቸዉን ቢሰጡና ወደማንነታቸዉ ወይንም ወደ ኢትዮጵያዊነታቸዉ ቢመለሱ ነው የሚበጃቸዉ።
ኢትዮጵያ: ሀገረ እግዚአብሔር መሆንዋ የሚያውቁት: ዲያብሎስ እና ጭፍሮቹ ርትዕት ተዋሕዶ ኃይማኖትና ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያን ለማጥፋት እስከ ጫፍ ድረስ ቢለፉም አይሣካላቸውም። ምንም የማያውቀው የዋሁ ኢትዮጵያዊ ይዘውት የሚጠፉ ናቸው።
Blogger Comment
Facebook Comment