ከሰኔ ፲ - ፲፪ በ'መድኃኒዓለምና በድንግል ማርያም ማኅበር' በእኅታችን እኅተ ማርያም መሪነት ለ፫ ቀናት የቆየ ፀረ ግብረሰዶማዊነት ተቃውሞ በሠላማዊ መንገድ ተካሂዷል። በግንባር ላይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቀለማት የሆኑት አረንጓዴ ፣ ብጫ እና ቀይ ቀለማት ያሉት ጨርቅ በማሰር ነበር የተካሄደው።
ባለፈው ጊዜ ሰባኪው ዴቪድ ሊንን አስሮት የነበረው ግብረ-ሰዶማዊ ፖሊስ (መለዮው ላይ የግብረ-ሰዶማውያንን አርማ ለጥፏል)አሁን ደግሞ ዶሬላቭ በተባለው ሰባኪ ላይ ዘመተ።
ሰባኪው፡ "ግብረ-ሰዶማውያን ልጅ መውለድ አይችሉም፤ የቤተሰብንን እና ማሕበረሰብን አስፈላጊነት ያጠፋሉ፤ ስለዚህ ግብረሰዶማዊነት የሙታን አምልኮ ነው፣ የመግደያ መሣሪያ ነው" ማለት ሲጀምር ሰዶማውያኑ ፖሊሶች ተጠራርተው መጡበት።
የሚገርመው ደግሞ፡ ይህ ግብረ-ሰዶማዊ፡ “እኔም እንዳንተ ሰባኪ ነበርኩ፡ ከአንተ የተሻለ ዕውቀት አለኝ፤ ክርስቶስ እንዲህ እየጮኸ አይሰብክም ነበር፤ የማጉያውን ድምጽ ቀንስ፤ አሊያ ክስ እንመሰርትብሃለን“ እያለ በጥቁሩ ሰባኪ ላይ ሲሳለቅበት መስማቱ ነው። ባካባቢው የነበሩ አጋንንት ሲፈነድቁና ሲያጨበጭቡ ይሰማሉ።
በእኅተ ማርያም እኅቶች ላይ በሀገራችን ያሳዩትም ትንኮላ ሌላ ማስረጃ ነው።
እነድዚህ ዓይነት ነገር ከአሥር ዓመታት በፊት የማይታሰብ ነበር፤ አሁን ግን በድፍረት ብቅብቅ እያሉ ነው፤ አጋንንት ተለቅቀዋልና፤ ግድየለም ይታዩን፣ ጊዚያቸው አጭር ነው!
Blogger Comment
Facebook Comment