ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በተካሄደው የፕሮቴስታንት መሪዎች ስብሰባ ላይ ፓስተር ዶ/ር ወዳጄነህ መሀረነ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል በቃል
''ለሙሴ የተሰጠው የቃልኪዳኑ ታቦት (ታቦተ ጽዮን) ኢትዮጵያ ውስጥ አክሱም ጽዮን ነው ያለው። ይህንን ደግሞ ሁሉም ጥንታውያን የታሪክ ማስረጃዎች የሚመሩት ወደዚህ ነው፣ ብዙ የታሪክ ተመራማሪዎችና የሀይማኖት አባቶችም ያረጋገጡት ይህንኑ ነው። እስከ ቅርብ ጊዜ የተሰሩ ዓለም አቀፍ ጥናቶችም የሚያሳዩትም ይህንን ነው፤ እኔም በጥናቴ ያረጋገጥኩት እንደዛው ። ታቦተ ጽዮን ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ያለው። በሀገራችን የነበሩ የመንግስታት መውደቅ መነሳት ፣ መበልጸግ መጎሳቆልም ከዚሁ ጋር የተያያዘነው ። ቀድሞ ይሄ ታቦት ብዙ ተአምራቶችን ሰርቷል ወደ ሀገራችን ከመጣ በዃላም እንዲሁ። ብዙ ነገስታት ወደ አክሱም ጽዮን በመሄድ በታቦቱ ከብረዋል። ተቀብተዋል። ይህንን ታቦት ያከበሩ ነገስታት ኖረውም አለፈውም እስከዛሬ ተከብረዋል ፥ ያላከበሩት ደግሞ ተዋርደዋል ፤ እና ክቡር ጠ/ሚ እርሶም የዚህች ሀገር መሪ ኖትና ስኬት እንዲኖሮት ከባለቤቶ ጋር ሆነው አክሱም ጽዮን ሄደው ያንን ታቦት ያክብሩ እንዲከበሩ ስል እመክሮታለሁ''
--- ዶ/ ር ወዳጄነህ።
እውነት መስካሪ አያሣጣን። በእርግጥ አቶ ወዳጄነህ ከቤተልሔም ታፈስ ጋር በኤክሶደስ የመስኮተ ትዕይንት መርሓ ግብር ባለፈው ዓመት ቀርበው ፕሮቴስታንቱ ፣ ካቶሊኩና ተዋኅዶን በጋራ እንደሚከተሉ ነግረውናል። ይህ እምነት በምዕራባውያን የተፈለሰፈ እውነተኛዋን ኃይማኖት 'ተዋኅዶ' በማድበስበስ ለመቅበር ያለመ መሆኑ መታወቅ አለበት። እንቅስቃሴውም ኢኩመኒዝም (ecumenism) ይባላል። አቶ ወዳጄነህ እነ 'ዲያቆን ዳንኤል ክብረት' ጭምር በተገኙበት ስብሰባ ይህ እውነት መናገራቸው ግን ያስመሰግናቸዋል።
ሰይጣናዊ መንግስታትና እና የአዕምሮ ባርነት ሰለባ የሆኑ ግለሰቦች ግን እውነት እንዲነገር አይፈልጉም።
የሰይጣናዊ አዕምሮ መቆጣጠሪያ መርሃ ግብር መሠረት የሆነው ዒላማዊ የማህበራዊ ቅኝት መመሪያዎች፦
☞ከብዙዎቹ (ከብቶች) ጋር ሂድ
☞ ከከብቶች ተለይተህ አትቁም
☞ አትከራከር፤ ጀልባውን አታናውጥ
☞ ባለሥልጣንን አትጠይቅ
☞ አብረህ ሂድ፣ ተስማማ ፥ አሊያ ትገለላለህ
☞ ዝም በል እና ተቀላቀል/ ተደመር
☞ መሪዎችህ እና መገናኛ ብዙኃን የሚነግሩህን ነገር ሁሉ እመን
☞ ማን ነህና ነው ነገሮችን የምትጠይቅ?
Blogger Comment
Facebook Comment