ከፀሓይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም! — በሀገር–ወዳድ ኢትዮጵያውያን ላይ ዘመቻው ጀምሯል፦

ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ሀገራችንን እየመሯት ያሉት የተዋሕዶ ኢትዮጵያ ጠላቶች መሆናቸውን መቶ በመቶ መናገር እደፍራለሁ። አዎ! እነግራኝ ዐቢይ አሕመድ፣ ለማ መገርሳ፣ ደመቀ መኮንን ወዘተ ሁሉም የተዋሕዶ ኢትዮጵያ ጠላቶች ናቸው። ብሔራዊ ማንነትን በየሀገራቱ ለማጥፋት በመላው ዓለም በመታየት ላይ ያለው ሉላዊው እንቅስቃሴ በተለይ በጥንታዊቷ ቤተክርስቲያን ላይ ነው በጠላትነት ያነጣጠረው። በሶሪያ እና ኢራቅ የተካሄደው ዘመቻ በጥንታዊቷ ቤተክርስቲያን ላይ ነበር፤ ከሞላ ጎደል ክርስቲያኖችን በእነዚህ ሀገራት ለማጥፋት ተችሉቸዋል። አሁን ትኩረታቸው በኢትዮጵያ ላይ ነው። ያስቀመጧቸው መሪዎች የሰጧቸውን የቤት ሥራ አንድ ባንድ በመሥራት ላይ ናቸው። ላለፉት ሃምሳ አመታት ፀረ–ኢትዮጵያ የሆኑትን ኃይሎች በተለይ “ኦሮሞ” የተባሉትን የኢትዮጵያ ጠላቶች በማደራጀት ላይ ነበሩ፤ ነገሮች በአንዴ አልመጡም፤ ቀስበቀስ ነው። ደርግና ኤሕአፓ እርስበርስ ተቃራኒዎች በመመሰል የኢትዮጵያን ጥንካሬና አንድነት የሚጠብቁትን ጄነራሎች፣ ሚንስትሮች፣ ዳኞችና መምህራን ባሰቃቂ መልክ እረሸኑ፣ ተተኪውን ኢትዮጵያዊ ትውልድ ለማድከም በብዙ ሚሊየን የሚቆጠሩ የተዋሕዶ ወጣቶችን ገደሉ፤ በዚህም ኢትዮጵያን አዳከሟት፣ አዋረዷት፥ ኢትዪጵያዊነትን አረከሱት። ወገኖቼ፤ ታሪክ እየተደገመች ነው፤ አሁን እነ አብይ አህመድ እያካሄዱት ያለው የምንጠራ ዘመቻ በደርግ ጊዜ ኢትዮጵያን ለማድከም ከሚካሄደው ዘመቻ ጋር በጣም የሚመሳሰል ነው። ብዙ ልምድ ያላቸውን አገር–ወዳድ ጄነራሎችና የጦር መሪዎች ደርግ ሲረሽናቸው፤ የሶማሊያ እስላማዊ ሠራዊት አጋጣሚውን በመጠቀም ወደ ኢትዮጵያ ሰተት ብሎ እንደገባው፤ አሁንም እነ ዶ/ር አህመድ ልምዱ ያላቸውን እና የሃገር ፍቅር ያላቸውን የጦር መሪዎች በመግደል ላይ ይገኛል። 

“የጎረቤት ሃገራት እርዳታ ሊያደርጉልን ዝግጁ ነበሩ” ማለቱ የግብጽ፣ ሱዳን እና ሶማሊያ እስላማዊ ሠራዊቶች ወደ ኢትዮጵያ ሰተት ብለው እንዲገቡ ልፈቅድላቸው ነው” ማለቱ ነው። ግብጽ የሕዳሴው ግድብ የሚገኝበትን እና ሆን ተብሎ ለዚህ ወቅት የተከፈለውን “ቤኒሻንጉል–ጉሙዝ” የተባለውን ክልል ለመቆጣጠር በመዘጋጀት ላይ ናቸው፤ በዚህ ክልል እና በሱዳን የተፈጠረው ህውከት ከዚህ ጋር የተያያዘ ነው። የእነዚህ የኢትዮጵያ ጠላቶች ሤራ የመጨረሻው ደረጃ ላይ ደርሷል፤ ኢትዮጵያን ለመበታተን አይቻላቸውም፤ ነገር ግን ብዙ ጥፋቶችን ያጠፋሉ፤ ለዚህም በተለይ ያልነቁና በደፈናው ሁሉንም አቅፈው አንድ ለመሆን የሚመኙት ሞኝ ኢትዮጵያውያን ተጠያቂዎች ናቸው። ከማን ጋር፣ ምንን ይዘን፣ በማን ሥር ነው አንድ የምንሆነው? ይህ ድብልቅልቅ ሁኔታ ከዚህ ቀደም ስንሄድበት በነበረው የኑሮ ጎዳና እንዳንጓዝ ጥሩ እድል ሰጥቶናል፤ ማን የኢትዮጵያ ጠላት እንደሆነ ለማየት አጋጣሚውን ፈጥሮልናል፣ አዝማቹ ጠላት በሞተ ሥጋ የማያርፍ ዲያብሎስ እንደሆነ በብሩህ ልቡና እንድናውቅ ረድቶናል፡፡ በመልካም እርሻ /ማሳ/ የተዘራው ንጹሕ ስንዴና ጠላት ጨለማ ለብሶ በስንዴው ማሳ ላይ የበተነው እንክርዳድ እስከ መኸር ጊዜ ዐብረው እንደሚኖሩ ጌታችን ራሱ ባለቤቱ በቅዱስ ወንጌል አስተምሮናል [ማቴ. ፩፫፥፳፬፡ ፴፩]ይህ የማይሻር ቃል ስለሆነ ሌላ ምን ይባላል? አባቶቻችን ባቆዩልን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ላይ ዛሬም ግልጽ የሆነ ጦርነት ተከፍቶባታል። ይህች ሃይማኖት ጥንታዊት፣ የቀናችና የጠራች ስለሆነች ተካታዮቿን የምታኮራ እንጂ የምታሳፍር አይደለችም፡፡ በሰዎች የግል ድካም እንጻርም አትመዘንም፡፡ ለመከራም አትበገርም፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን እስከ ዛሬ ድረስ በእምነቷ፣ በጾሟና በጸሎቷ የማያቋርጥ የገቢረ-ተአምራት ወመንክራት፣ ኀይላትም ሥራ ስትሠራ የምትገኝ ለተከታዮቿ ተስፋ ሆና የምትኖር እውነተኛ ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ርግጥ ነው፤ በቅን ልቡናና በትሑት ሰብእና ለተቀበለው ሸክሟ ቀላል ቀንበሯ ልዝብ ነው፡፡ ዳሩ ግን በገድል የተቀመመ ሕጓ፣ ባህሏና ሥርዐቷ ጥብቅ ስለሆነ የሕግና የሥርዐት ቀንበር ላለመደ ስስ ጫንቃ አይመችም፡፡ መንገዱ ቀጭን፣ በሯ ጠባብ ነው፡፡ 

የእግዚአብሔርም መንግሥት የምትወርሰው በመከራ መስቀልና ብዙ ትዕግሥት፣ በዚሁ ቀጭን መንገድ ተጉዞና በጠባቡ በር ዐልፎ ስለሆነ በቀና ሃይማኖት ጸንቶ፣ በጾም በጸሎት ተወስኖ ሕይወቱን = አኗኗሩን በሥነ ምግባር፣ ገዝቶ በአበው፣ መንፈሳዊ መንገድ መጓዝ ለክርስቲያን አምላካዊ ትእዛዝ ነው፡፡ ማቴ. ፯–፲፫–፭ የሐዋ.፲፬–፳፪ ይህ ጠባብ በርና ቀጭን መንገድ የሃሪካችን መዛባት የለበትም፡፡ ተቆርቋሪዎች እንሁን፡፡ የወይራ ዛፍ ተቀጥላው ብሳና ቢሆን እጅግ ያሳፍራልና፡፡ በነገረ ጠቢባን «ሳይረቱ አይበረቱ» ተብሏልና፡፡
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment