ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
☞ ዓሲምባ በርዕሰ ኢትዮጵያ ትግራይ ክፍለሀገር ኢሮብ የሚገኝ ቦታ ነው።
☞ በዚህ ቅድስ ቦታ ብዙ ገዳማትና አብያተክርስትያናት ይገኛሉ።
☞ በነዚኽ ገዳማት በአረንጓዴ ፣ ብጫ ቀይ ቀለማት ያሸበረቁ ንግግራቸው ሁሉ ስለ ኢትዮጵያ ብቻ የሆነ አባቶች አሉ።
☞ በዓሲምባ ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያ በቀጣይ ዓለምን በቅድስና የምትገዛበት 'የኢትዮጵያ ትንሣዔ' ይሠበካል።
☞ ዓሲምባ ለ'ኢትዮጵያ ትንሣዔ' መዳረሻ ከሚሆኑ የኢትዮጵያ ሥፍራዎች አንድ ነው። ብዙ ሥውራን አባቶችና ቅድስ ሥፍራዎች ያሉት ነው።
☞ የዓሲምባ አባቶች ይህ ወቅት በቀጣይ ዓመታት በምድረ ኢትዮጵያ የሚከሠቱት አስከፊ ነገሮች በንስሐ ፣ በቁርባን ፡ በፆም እና በፀሎት በማለፍ ብቻ የ'ኢትዮጵያ ትንሣዔ' ማየት እንደምቻል ይናገራሉ። ይህ ወቅት እውነተኛ ኢትዮጵያዊ የሚለይበት ነው።
☞ በሊቀ ሠይጣኑ ወያነ የኅፅበተ አዕምሮ (brainwash)መሣርያ ኢትዮጵያዊነቱንና ኢትዮጵያን እንዲጠላና በጠላትነት እንዲነሣ የተደረገው የዘመኑ ወጣት ወደ ብቸኛው የእውነት መንገድ እንዲመለሥ ይመከራል።
☞ የትግራይ ህዝብ ሁሉ ፀረ ኢትዮጵያ የሚመስለው አካል ካለ ከነዚህ አባቶች በላይ ስለ ኢትዮጵያዊነት የሚመሰክር እንደሌለ ሊያውቅ ይገባል።
Blogger Comment
Facebook Comment