ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
የአንደኛው የዓለም ጦርነት የመታሰቢያ ምልክት በሆነውና በተለምዶ "የሰላም መስቀል" ተብሎ የሚጠራው ይህ አስራ ሁለት ሜትር ከፍታ ያለው አንጋፋ የሲሚንቶ መስቀል ከመቶ ዓመታት በፊት ነበር በ ሜሪላንድ(ማርያም) ግዛት የተሠራው። የብላንድበርግ የአንደኛው የዓለም ጦርነት መታሰቢያ በመባል ይታወቃል።
ባለፉት ወራት ግን የዲያብሎስ አርበኞች የሆኑት ኢ-አማንያን መስቀሉን እዚህ ቦታ ላይ ማየት አንፈለግም መነሳት አለበት በማለት ተቃውሞዋቸውን ሲያሰሙ ቆይተው ነበር። በመጨረሻም ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስደውታል። በዚህ ሳምንት የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኢ-አማንያኑን ተቃውሞ ውድቅ በማድረግ መስቀሉ ከቆመበት ቦታ እንዳይነካ ወስኗል። ይህ ትልቅ ድል ቢሆኑም፡ ግን ጉዳዩ ይህን ያህል እና እዚህ ደረጃ ላይ መድረሱ፡(ያውም ጠቅላይ ፍርድ ቤት ድረስ) የአሜሪካ ማኅበረሰብ ምን ያህል እየወደቀ መምጣቱን ይጠቁመናል።
የሜሪላንድ ግዛት፡ ስሟ ሄነሪታ ማሪያ(1609-1669)ተብላ በምትታወቀዋ የእንግሊዝ ንግሥት ነው የተሰየመችው። ሜሪላንድ በዋሽንግተን ከተማ የመኖሪያ ክልል ሥር የምትገኝ ሲሆን በውስጧ እስከ ሁለት መቶ ሺህ የሚሆኑ ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ይኖራሉ። ከጥቂት ዓመታት በፊት እዚህ አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለወስላታው ኦባማ ከፍተኛ ድጋፍ ለመስጠት መንግደ ላይ ሲወጡ ታይተው ነበር።
መስቀል የሰላም ምልክታችን በመሆኑ እናከብረዋለን። ጠላታችን ድል የተነሳበት ነውና እንሸከመዋለን። ምክንያቱም ጠላቶቻችን አጋንንትን እንወጋበት ዘንድ ከእግዚአብሔር ተሰጥቶናል።
የመስቀል ጠላቶች ከእለተ ዓርብ ጀምሮ የምላስ ጦራቸውን ስለው፣የቅናት እና የምቀኝነት ምላሳቸውን አጠንከረው፣ መስቀልን ከምእመናን ልቡና ለማጥፋት መላ ጊዜያቸውን አጥፍተዋል፤ ሊያጠፉት ግን አልቻሉም ኃይል አለውና። አይሁድ መስቀሉን ለሦስት መቶ ዓመታት ጥራጊ ደፍተውበታል። እነርሱ የሉም መስቀሉ ግን አለ። ዛሬም የመስቀሉ ጠላቶች ይጠፋሉ እንጂ መስቀሉ እየጎላ ነው የሚሔደው።
ቅዱስ ጳውሎስ፡ "ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶቹ ሆነው ይመላለሳሉና ብዙ ጊዜ ስለ እነርሱ አልኳችሁ፤ አሁንም እያለቀስኩ እላለሁ መጨረሻቸው ጥፋት ነው ሆዳቸው አምላካቸው ነው፤ ክብራቸው በነውራቸው ነው አሳባቸው ምድራዊ ነው"። ---[ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች ምዕራፍ ፫፥፲፱]
Blogger Comment
Facebook Comment