የሀገረ እንግሊዝ ሴራ በኢትዮጵያና በተዋኅዶ ኃይማኖታችን እንደቀጠለ ነው!

ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

ከመቶ ኃምሳ ዓመታት በፊት በመቅደላ ጦርነት ወቅት ከኢትዮጵያ በብሪታኒያ ጄነራል ናፒይር የተሠረቀው ቅዱስ ታቦት ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ጥረት ቢደረግም እንግሊዛውያን ግን ዛሬም ለመመለስ ፈቃደኞች አይደሉም።

በሀገረ ብሪታኒያ በጣም ቁልፍ እንደሆነ በሚነገረለትና በነጻ ግንበኞች (freemason) በተገነባው ህንጻ፡ በዌስትሚኒስተር አቤይ ውስጥ ከመንበሩ ጀርባ ተደብቆ ይገኛል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሊቀጳጳሳት ዌስትሚንስተር ቤተ–ክርስቲያን በሚገኘው ታቦት አቅራቢያ ቅዳሴ ለማድረግ ይችሉ ዘንድ ፈቃድ እንዲያገኙ ለንደን የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቀሳውስት ብዙ ሙከራ አድርገዋል፥ ግን አልተሳካላቸው።

ዲያቆን ሳሙኤል ብርሃኑ የዌስትሚንስተር አቤይ አስተዳዳሪዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሊቀጳጳሳትን ጉብኝት ሊያስትናግዱ ባለመቻላቸው የተሰማቸውን ሃዘኔታ እንደሚከተለው ገልጠዋል፦

"በ ፳፩ ኛው መቶ ዘመን የባህላዊና ኃይማኖታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ይህን ያህል ግድየለሾች ይሆናሉ፤ እንዲህ የመሰለ አመለካከት ሊኖራችሁ ይችላል ብዬ አላምንም ነበር። ለመወያየት እንኳ ፈቃደኞች አይደሉም"

"እንደሚታወቀው ታቦቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መሠረት ሲሆን የቤተክርስቲያንን ሕንፃ የሚባርክና የሚቀድስ ነው።"

"እንደ ክርስቲያን ይህን ዓይነት አስተያየት እንዴት ይይዛል?፤ የቤተክርስቲያን በር እንዴት ይዘጋብናል? የዌስትሚንስተር አቤይ አቀራረብ "በጣም አሳፋሪ" ነው – በተለይ የዌስትሚንስትር ቤተክርስቲያን እራሷ ለመጸለይ ፈቃድ አለመስጠቷ ተጨማሪ ቅሌት ነው።"

ይሁን! ለጊዜው ግድየለም፡ አባቶች! ብሪታኒያ ቅዱስ ታቦታቱን ለኢትዮጵያ ሀገራችን መመለስ ፈርታለች፤ ምክኒያቱም ራቁቷን ትቀራለችና፣ ታላቋ ብሪታኒያ ታንሳለችና፤ ተስጥቷት የነበረውን ኃይልና ሞገስ ትነጠቃለችና። እንደ እኔ ከሆነ ብሪታኒያ ታላቅ ለመሆንና አብዛኛውን የዓለማችንን ክፍል ለመቆጣጠር የበቃችው፣ እንግሊዝኛ ቋንቋዋ የዓለም ሁሉ መነጋገሪያ ቋንቋ ለመሆን መቻሉ እንዲሁም ብሪታኒያ በአንደኛውና ሁለተኛው የዓለም ጦርነቶች ድል አድራጊ ለመሆን የተቻላት የተዋኅዶ ታቦታትን በእጆቿ ስላስገባቻቸው ነው።

በአፄ ቴዎድሮስ ዘመን ሀገራችንን የወረረችው፥ በትምህርት ቤት ለመማር እንደተገደድነው ፥ የታሠሩትን ዜጎቿን ለማስፈታት(ማታለያ False Flag Operation ነበር)ሳይሆን፤ እነዚህን ታቦታት ለመስረቅ ነው። መጽሐፈ ሄኖክን ከኢትዮጵያ ሰርቆ የሄደውን ሌባውን ነፃ–ግንበኛ ጀምስ ብሩስን ቀደም ሲል ለስለላ ልከውት ነበር።

ግን የብሪታኒያ እና አጋሮቿ የክብርና ታላቅነት ዘመን ኢየሱስ ክርስቶስን መክዳት ከጀመሩበት ሰዓት አንስቶ ቀስበቀስ እየመነመነ መጥቷል። ለዚህም ነው እስልምና እንደ መቅሰፍት ሆኖ እየተላከባቸው ያለው። እባቦቹ ትውልደ ፓኪስታን የለንደን ከንቲባ እና የሀገር ውስጥ ሚንስትር እስከመሆን በቅተዋል። በቅርቡ ደግሞ የክርስቶስ ተቃዋሚ ከሆነችው ቱርክ የመጀመሪያው የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚንስትር ይሾማል። ለንደንን ለፓክሲታን መንፈሳዊ ወንድሙ አስርክቦ ገለል ያለው የቀድሞው የለንደን ከንቲባና የቱርኩ ፖለቲከኛ አሊ ከማል የልጅ ልጅ የሆነው ቦሪስ ጆንሰን ወስላታዋን ተሪዛ ሜይን ይተካት ይሆናል።
ካሁን በኋላ የምዕራባውያኑ ምርጫ በኮሌራ እና ወረርሽኝ መሃከል ነው፤ ንስሐ ገብተው እካልተመለሱ ድረስ ሀገራቱን የሚያጠነክርና የሚጠቅም ሰው ከእንጊድህ አያገኙም።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment