ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
የግብረሰዶማውያን አስጎብኚ ድርጅት በኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ ዓለምን በቁጥጥር አድርጋ በአንድ በቅድስና የምትገዛበት 'የኢትዮጵያ ትንሣዔ' መድረሱ የሚያውቀው ዲያብሎስ ኢትዮጵያ ለማርከስ አጠቃላይ ኃይሉ በመጠቀም እየሠራ ነው። ይህ ወቅትም ኢትዮጵያ ምጥ ላይ ያለችበት ሲሆን ደጉ ከክፉ የሚለይበት ጊዜ መቅረቡ የሚጦቁም ነው። ዲያብሎስ በአሁኑ ወቅት ዓለም በቁጥጥሩ ሥር ያደረጋት ሲሆን ፣ የቀረችው ምድር ኢትዮጵያ ናት። ቅድሳት ገዳማትና የቅድሳን አባቶች ምሕላ ከሴራው እየጠበቃት መሆኑ የሚያውቀው ዲያብሎስ ቅድሳት ገዳማት ማርከው ላይ እየሠራ ነው። ዋነኛው ዘዴውም የኢትዮጵያ መንፈሣዊ ኃብቶችና ቅርሶች በሉሲፈራውያኑ ድርጅት ዮኔስኮ (UNESCO) በማስመዝገብ ለእምነት አልባ ምዕራባውያን ፣ መናፍቃንና ግብረሰዶማውያን መረጃ በመስጠት ፣ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ቅርሶች እንዲዘርፉ እና እንዲያረክሱት ያደርጋል።
ሰሞኑን 'Toto International Gay Tour' የተሰኝ የግብረሰዶማውያን አስጎብኚ ድርጅት በኢትዮጵያ ገዳማት ለ፲፮ ቀናት ለማስጎብኝት መርሐ ግብር እንደያዘ በ ኅዋ ሰሌዳው ይፋ አድርጓል።
ይህንን የርኩሰት ድርጊት ከመፈፀሙ በፊት ኢትዮጵያውያን የግራኝ ዐቢይ አሕመድ ድርጊት ሳንጠብቅ ልናስቆሞው ይገባል።
መጽሐፍ ቅዱስ በኦሪት ዘፍጥረት መጽሐፍ ስለ ግብረ ሰዶማዊነት ይናገራል፡፡ የሰዶምና የገሞራ ሰዎች ግብረ ሰዶማውያን ነበሩ፡፡ ሰዶምና ገሞራ በዮርዳኖስ ሸለቆ የተቆረቆሩ ከተሞች ነበሩ፡፡ በእነዚህ ሁለት ከተሞች ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ግብረ ሰዶማውያን ማለትም ወንድ ከወንድ፣ ሴት ከሴት ጋር ዝሙት የሚያደርጒ ይህ ኃጢአትም በእነርሱ ይበዛ ስለነበር ስያሜው የቦታውን ስም በመያዝ ግብረ ሰዶም ተባለ፡፡ በዘመናት ሁሉ ይህን ኃጢአት የሚሠሩ መጠሪያ ሆኖ አገለገለ፡፡ ዛሬም በግብር የሚመስሉአቸው ሰዎች ግብረ ሰዶማዊ ወይም ሰዶማውያን እየተባሉ ይጠሩበታል፡፡ የሰዶምና የገሞራ ሰዎች ወንድ ከወንድ፣ ሴት ከሴት ጋር የሚፈጽሙት ዝሙት አጸያፊ ስለነበር እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ወሰነ፡፡ (ዘፍ. 18÷20፣ ዘፍ.19÷5-9)፡፡ ሁለት መላእክትን ወደ ሰዶም ላከ፡፡ ሁለቱ መላእክት የእግዚአብሔር ሰው እና ከሰዶማዊነት ግብር ንጹሕ የነበረውን ሎጥን ከከተማው እንዲወጡ ካደረጉ በኋላ እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን በእሳትና በዲን አጠፋ፡፡ (ዘፍ.19÷10-26) ሰዶምና ገሞራ አሁን በጨው ባሕር እንደተሸፈኑ የሥነ ምድር ተመራማሪዎች ይናገራሉ፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ ሰዶምና ገሞራ የክፋት ሁሉ የፍርድም ምሳሌ በመሆን ተጠቅሰዋል፦
[ኢሳ. 1÷9-10፣ ኢሳ. 3÷9፣ ኤር. 23÷14፣ ሰ.ኤ.4÷6፡፣ ሕዝ. 16፡46፣ ማቴ.10÷15፣ ራእ. 11÷8]
Blogger Comment
Facebook Comment