ሀገረ አሜሪካ በየቀኑ ንጹሃን ሰዎች በማያገባት እየገባች በጦርነት የምትገድና ለስደት የምትዳርግ የዲያብሎስ አገልጋይ ሀገር ነች። የኢቫንካ ትራምፕ የኢትዮጵያ ጉብኝትም በጥርጣሬ የሚታይ ነው። የነጩ ቤተመንግስት አማካሪና የዶናልድ ትራምፕ ልጅ የሆነችው ኢቫንካ ትራምፕ በዚህ በያዝነው የአፕሪል ወር ወደ አፍሪካ መጥታ በኮትዲቯርና በኢትዮጵያ የአራት ቀን ቆይታ እንደሚኖራት ተወርቷል።
የሴቶች አለም አቀፋዊ ተሳትፎ፣ እድገትና ልቀት ላይ የሚያተኩረው (Women’s Global development and Prosperity initiative) አመራር መሆኗን ተከትሎ ነው የመጀመሪያ አፍሪካዊ ጉዞዋን የምታካሂደው።
በትናንትናው እለት ከነጩ ቤተመንግስት ቃል አቀባዮች እንደተሰማው በአይቮሪኮስት የሚካሄደውን ሴቶችን በኢኮኖሚ ተሳትፎ ሀይል የማስታጠቅ ስብሰባ (women’s economic empowerment summit) የምትካፈል ሲሆን በኮትዲቯር ቆይታዋም ከስብሰባው ውጭ ሴት ፖለቲከኞችን ኢንተርፕረነሮችን እና የዋአኔ ሰጪ ቦታ ላይ የሚገኙ ሴቶችን ታገኛለች ብሎ አሶሺየትድ ፕሬስ አውርቷል።
ከዚያም በኋላ ከፍተኛ የሴቶች ተሳትፎ በፖለቲካ እያሳየች ወደምትገኘው ኢትዮጵያ ትመጣለች። በቢዝነሱ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ እንስቶችን፣ በፖለቲካው ምህዳር ሚናቸው ያደጉ ሚኒስትሮችና ባለስልጣናትን እንዲሁም የእናቶችን ሞት ለመቀነስ ሚናቸው ከፍ ያሉ ባለሙያዎችን ያገኛሉ ተብሏል።
አብረዋትም የአለም አቀፍ የአሜሪካ እድገት ኤጀንሲ ዳይሬክተር ማርክ ግሪንና የውጭ የግል ንግዶች ፕሬዚዳንት ዴቬድ ቦሄይን እና ከአለም ባንክ ክሪስቲና ጂኦርጂቫ ያጅቧታል።
ለአሶሽየትድ ፕሬስ በሰጠችው ቃልም ወደ አፍሪካ ለምታደርገው ጉዞ ዝግጁ መሆኗን ተናግራ በጉዞውም ደስተኛ እንደሆነች ገልጻለች።
በፌብርዋሪ የተመሰረተው የኢቫንካ ኢኒሼቲቭ በ2025 50 ሚሊየን የሚደርሱ ሴቶችን በኢኮኖሚ ለማንቃት እየሰራ የሚገኝ ኢኒሺዬቲቭ ነው።
በስቴት ዲፓርትመንት በጀት የሚደገፈው የኢቫንካ ኢኒሺዬቲቭ በተለይ በታዳጊ አገራት የሚገኙ ሴቶችን በኢኮኖሚ ለማብቃትና ለማሳደግ የሚሰራ ሲሆን እስካሁን በተመደበለት የ100 ሚሊየን ዶላር ፕሮጀክቶችን አቀናጅቶ ለሴቶች የገንዘብ ድጋፍ፣ ስልጠናዎችንና የህግ ማዕቀፎችን ለማስተካከል ይውላል ተብሏል።
ከዚህ ቀደም በህንድና በጃፓን ተመሳሳይ ጉዞ እንዳደረገች ይታወሳል።
Blogger Comment
Facebook Comment