የትራምፕ ሴት ልጅ ትላንት ኢትዮጵያ ገብታለች!


ኢቫሪካ ትራምፕ የሽሮሜዳ ሽመና ጎብኝታለች። አውሬው ከነጫማው ሀገረ–ኢትዮጵያ ውስጥ እየገባ ነው፤ ከሁለት ዓመት በፊት “የጌታችን መስቀል ጫማ ላይ እንዲረገጥ ጫማዎችን እያመረተች ወደ ኢትዮጵያ የምትልከው ፀረ–ክርስቶሷ ቱርክ ናት” የሚል ፅሑፍ ለጥፌ ነበር።
አሁን ደግሞ ኢ–አማኒ ቻይና ከፕሬዚደንት ትራምፕ “ለዘብተኛ” ሴት ልጅ፤ ኢቫንካ ጋር በመተባበር የጫማ ፋብሪካዎችን በማስፋፋት ላይ ትገኛለች። ጉድ ነው፤ ኢትዮጵያውያንን ቻይኖች የማድረግ ሥራ እየተሠራ እንደሆነ ልንገነዘብ ይገባል። ኢትዮጵያውያን ማንንታቸውን እስከካዱላቸው ድረስ፣ ወደ ክርስቲያን ሃገር አይጠጉ እንጂ፤ ኢ–አማኒዎቹን ቻይናን፣ ምዕራቡን ወይም አረቡን ቢመስሉላቸው ግድ የላቸው፤ እንዲያውም ይህ ነው የሚፈለገው፤ ኢትዮጵያዊነታቸውን እንዲተው። “እኔ አማራ ነኝ፣ ትግሬ ነኝ፣ ኦሮሞ ነኝ…” የሚያስብሉንም “ኢትዮጵያዊ” ነኝ ማለቱን እንድናቆም ነው። ኢትዮጵያዊነታችንን እየተነጠቅን ነው፡ ወገን!

ሴትነታቸውን እየካዱ የመጡት ምዕራባውያን ሴቶች “የአፍሪቃን ሴቶች እናጎልብታለን” በሚል ተልካሻ መርሕ ሞኙ ሕዝባችንን ይደልሉታል።
ሴቶች ከምዕራቡ ዓለም ይልቅ በአፍሪካ ከፍተኛ የሴትነት ሚና ይጫወታሉ፤ በተለይ ልጆችን ወልደው በማሳደግ፣ ቤተሰብን በመንከባከብ። አውሬው ግን ይህን አይወድም፡ ስለዚህ “ሴቶችን እናጎለብታለን” በማለት የአፍሪቃ ሴቶች እንዳይወልዱና እውነተኛውን ሴትነታዊ ማንነታቸውን ይክዱ ዘንድ ወሊድ መከላከያን እንዲጠቀሙ፣ እንዲያመነዝሩና ወንድን በመጥላት በግብረሰዶማዊ ተግባር ላይ እንዲሰማሩ ይገፋፏቸዋል። ሁሉም ተግባራቸው ከ 666ቱ ነው።

በዓለማችን ላይ ከሚታዩት የክርስቶስ ተቃዋሚ ግለሰቦች መካከል የኢቫንካ ትራምፕ ባለቤት ያሬድ ኩሽነር ነው። የሚገርም ነው፡ የዚህ ቀፋፊ ሰው ቢሮ የሚገኘው በ ኒው ዮርክ ከተማ “666 Fifth Avenue/ 5ኛው ጎዳና” ላይ ነው።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment