የዴንማርክ ልዕልት በኢትዮጵያ

ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

ምዕራባውያኑ ዔሳውያን "ሜሪ" ወይም "ማሪያ"፣ ምስራቃውያኑ እስማኤላውያን ደግሞ "መሪያም" የሚለውን የመጠሪያ ስም ለሴት ልጆቻቸው ይሰጣሉ። የንጹሗን ድንግል እናታችንን ስም በድፍረት ይሰጣሉ ማለት ነው፤ ልከ ኢየሱስ፣ ኢሳ እያሉ እንደሚሰጡት። ትሁቶቹ ኢትዮጵያውያን ግን "እህተ ማርያም፣ ሐብተ ማርያም፣ ወዘተ እያሉ ነው ልጆቻቸውን የሚሰይሙት እንጂ "ማርያም" ወይም "ኢየሱስ " የሚለውን ስም በጭራሽ ለልጆቻቸው አይሰጡም። ይህ በጣም ትልቅ የሆነ ነገር ነው።

የዴንማርኳ ልዕልት ሜሬ ምነው ለድንግል ማርያም ልዩ ፍቅር ወዳላት ኢትዮጵያችን መመላለስ አበዛች? ለእስክስታ ብቻ ይሆን? ለማንኛውም፡ ዔሳውያን እና እስማኤላውያን በኢትዮጵያ ላይ ተፅዕኖ ለማድረግ የተለያየ ሚና በመጫወት ላይ ናቸው።


ባለፈው ዓመት፡ ልክ በዚህ ወቅት፤ ግራኝ ዐቢይ አሕመድ በተመረጠ ማግስት፡ ዴንማርክ በአዲስ አበባ ኤምባሲዋ ፊት ለፊት የግብረሰዶማውያንን ባንዲራ በመስቀል ኢትዮጵያውያንንን ተፈታተነች/ፈተነች። እኅተ ማርያም ባለፈው ተንቀሳቃሽ ምሥል ወድምፅ ላይ "ወንድ የሆነችው ሴት በኢትዮጵያ ሥልጣን ተሰጥቷታል" እንዳለችው፤ ግራኝ ዐቢይ  አሕመድ በምዕራባውያኑ ግፊት የዔሳውን እና የእስማኤልን ሴቶች ስልጣን ላይ አውጥቷል፤ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ለመሆን የበቃችውን / የበቃውን መዓዛ አሸናፊ ጨምሮ። ከዚህ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያን ለማንቋሸሽ "ድፍረት" የተሰኘው ፊልም መሠራቱን እናስታስውስ። ይህ ፊልም የተሠራው የባሏን ደም ትመጥ በነበረችውና እስማኤላዊቷን "ዛሃራ" በጉዲፈችነት ከኢትዮጵያ በወሰደቻት በአንጀሊና ጆሊ ነበር። ሁሉም ነገር በቅርቡ ይገለጣል። አዎ! ሁሉም ነገር፡ ኡኡ! እርርይ! የሚያሰኝ ነው።

አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያስረድት ከሆነ የሚመጣው የክርስቶስ ተቃዋሚ ከዳን ነገድ ነው የሚሆነው። ዲንማርክ = ዳን። አብዛኞቹ አውሮፓውያን መኳንንት (ጥቁር መኳንንት ይባላሉ) እርስበርስ የተደቃቀሉ ሲሆኑ፤ ሁሉም የዴንማርካውያን ደም አላቸው።

የሚገርም ነው፦ ዴንማርክን የምታክል ትንሽ አገር (42 ሺህ ካሬ ኪ.ሜ / 5 ሚሊየን የሕዝብ ቁጥር አላት) ርቃ ሄዳ ግዙፉን ግዛት ግሪንላንድን (2 ሚሊዮን ካሬ ኪ.ሜ) መያዟ ነው።

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment