Don’t Let Ethiopia Become the Next Yugoslavia አሳቢ መስለው ሴራ የሚገነጉንብን ምዕራባውያን!

ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ
ምዕራባውያኑ ዔሳውያን እና ምስራቃውያኑ እስማኤላውያን ከጡትነካሾቹ ኢትዮጵያውያን ጋር በማበር በአገራችን እና በተዋሕዶ ክርስትና እምነት ላይ በጣም ትልቅ የሆነ ሤራ በመጠንሰስ ላይ ናቸው፤ ይህንንም አይደብቁትም፣ በግልጽ እየነገሩን ነው፦ የሉሲፈራውያኑ መጽሔት Foreign Policy“ ሰሞኑን እባባዊ የሆኑ ጽሑፎችን በተከታታይ በማቅረብ ላይ ይገኛል። በዛሬው ዕለት Don’t Let Ethiopia Become the Next Yugoslavia “ኢትዮጵያን የምትቀጥለው ዩጎዝላቪያ እንዳታደርጓት” በሚል ር ዕስ ሌላ የማታለያ ጽሑፍ ይዞ ቀርቧል። ይህ መጽሔት Council on Foreign Relations“ በተሰኘው የኢሉሚናቲዎች ተቋም ነው የሚታተመው)
ዩጎዝላቪያ ለመበታተን የበቃችው ኦርቶዶክስ ክርስቲያን የሆነችውን ሰርቢያን በማጥቃት ነበር። በአሜሪካና አውሮፓውያን ሤራ። ልክ አሁን ኦርቶዶክስ ሩሲያን ለመምታት በዩክሬይን እየጠነሰሱት እንዳለው ሤራ ማለት ነው። ባለፈው ገና ዋዜማ የዩክርየን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከእናቷ ከሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በይፋ እንድትከፈል ተደርጓል። ያውም በገና ዋዜማይህ ብዙ ያልተወራለት አሳዛኝ የታሪክ ክስተት ነበር።
በኢትዮጵያና ኤርትራም ይህን አይተናል፥ አይደልያው እንግዲህ ሉሲፈራውያኑ ላለፉት 50 ዓመታት የቀመሙትን ተንኮለኛ ሥራ በአገራችንም በማከናወን ላይ ናቸው። ሰሞኑን በይበልጥ የምናየው ነው!
ብዙዎቻችን እስካሁን በደንብ የተረዳነው አይመስለኝም፤ በትግርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ላይ እየተካሄደ ያለው የጥላቻ ዘመቻ ለተዋሕዶ ክርስትናችን የጀርባ አጥንት የሆነውን የአገራችንን ክፍል ለመምታት የታሰበ ዲያብሎሳዊ ሤራ ነው። ተዋሕዶ ነኝ የሚል ይህን በግልጽ ማየት ይኖርበታል። ዱሮ በጦርነትና ረሃብ በቀጥታ ተፈታተኑት፤ አሁን ደግሞ የራሳችንው ሰው እየተጠቀሙ ነው፤ የራሳችንን ፖለቲከኛ፣ የራሳችንን የቤተክርስቲያን አገልጋይ፣ የራሳችንን ፀሀፊና ጋዜጠኛ። ክርስቲያን ወገኖች ተጠንቀቁእንጠንቀቅ!
በተለይ በምዕራቡ ዓለም የምንገኝ ወገኖች፤ ከዛሬ ኅዳር ፯ እስከ ወሩ መጨረሻ ድረስ የዲያብሎስ ሠራዊት የክርስቶስ የሆነውን ሁሉ ከያቅጣጫው ያጠቃናል፤ ይህን የጨለማ ጊዜ ተግን በማድረግ በትምህርት ቤት፣ በሥራ ቦታ ወይም በመኖሪያ ቤቶች አካባቢ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ጥቃት ለመፈጸም ይሻሉና ይህን አውቀን ለሌሊት ጸሎት እንዘጋጅ፣ ዳዊታችንን እንድገም ዲያብሎስ ሥራው ሲነቃበት ካጠገባችን ይሸሻልና!
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment