ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
[ኢትዮጵያ አውታር 11 ቀን, 2011 ዓ.ም.] - የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትላንት የስደተኞች አዋጅ አጽድቋል። አዋጅ ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ ስደተኞች በድህንነት ተቋማት ከመሳተፍ ውጪ ልክ እንደ ኢትዮጵያ ዜጋ ሁሉንም መብቶች የሚያጎናጽፍ ነው። ምንም እንኳን በመንግሥታት መብቶች ተከብረው ባያውቁም። አዋጁ መጽደቁ በበጎ የሚታይ ቢሆንም ከጀርባው ግን የተጠነሰሰ ሴራ ለመኖሩ በእርግጠኝነት መናገር ይሆናል። የራሱን ዜጋ በየቀኑ ባሕርና በረሃ እያቋረጠ በሚሰደድባት ሀገር ፡ ሌሎችን ከበቂ በላይ በሆነ ሁኔታ ለመንከባከብ መወሰኑ በጥርጣሬ እንዳየው አድርጎኛል። ይህም ከምዕራባውያን
በስደተኞች ምክንያት የሚቀርብለት ዳጎስ ያለ ገንዘብ ብቻ አይቶ ያጸደቀው አዋጅ ነው።
ይህንን የሰደተኞች አዋጅ መጽደቅ
ተከትሎ የኢሉሚናቲ ጽንሰ ሓሳብ የሚያራምድ ኢትዮጵያ የመጽሐፈ ገጽ አድራሻ የሚከተለው መልዕክት አስተላልፚል። ምዕራባውያን በዓይነ ቁራኛ የሚከታተልዋት ሀገራችን ኢትዮጵያ ይህንን አዋጅ በመጠቀም የራሳቸው ሰዎች በሚፈልጉት መዋቅር በመሰግሰግ ሊፈጽሙት ለሚያስቡት ሴራ ምቹ ሁኔታ ይፈጥርላቸዋል።
Blogger Comment
Facebook Comment