ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ ብዙ መኖሪያ ቤቶች ከሰማይ በሚዘንበው እሳት በመቃጠል መውደማቸውን የወረዳው የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
ጸሎት ይደረግ ብሎም ተማጽኗል የወረዳው የመንግሥት ኮመሚዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት።
አሁን አድማሱን አስፍቶ ጠንከር ብሎ የታየው ከሰማይ እየዘነበ ቤቶችን የሚያቃጥለው እሳት ከጥቂት ዓመታት በፊት በዚሁ በሐረርጌ ክፍለ ሀገር ተከስቶ እንደነበር ይታወቃል።
አሁን ግን በምስራቅ ሐረርጌ ግራዋ ወረዳ በመ/ጀ/በሊና ቀበሌ ውስጥ ከሰማይ ላይ እየወረደ በንብት ላይ ጉዳት እያደረሰ የሚገኘው እሳት ትንሽ ጫንና ጠንከር ያለ ይመስላል።
የወረዳው ኮሚዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤትም እንዲህ በማለት ነው ለሚመለከተው ሁሉ በፌስቡክ ገጹ መልእክት ያስተላለፈው።
የፈጣሪ ተአምር የእሳት አደጋው እንደቀጠለ ነው።
በዐይናችን እያየ እዚያው አጠገቡ ቆመን ቤት እየተቃጠለ ነው።
በምስራቅ ሐረርጌ ግራዋ ወረዳ በመ/ጀ/በሊና ቀበሌ ውስጥ ከሰማይ ላይ በሚወርድ የእሳት አማካኝነት በአካባቢው ዛሬም ቤት ሲቃጠል ነበር። ቃጠሎው ዛሬም እንደቀጠለ ነው።
ዛሬ ጠዋት ሁለት ቤቶች ተቃጥለዋል። አሁን በዚህ ጊዜም ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ላይም ቤቶች በመቃጠል ላይ ናቸው ።ወገኖቻችን እባካችሁ ለህዝባችን ጸሎት(ልመና) አድርጉላቸው። ብሏል።
የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችም ጸሎት አድርጉ ማለታቸውን ግን ወድጄዋለሁ። ከልባቸው ከሆነ መልካም ነው። ሲኖዶሱና ሙጅሊሱ ካድሬ ሆኖ ጮጋ ሲል ምን ያድርጉ? የጨነቀ'ለት እኮ ነገሮች ይዘበራረቃሉ።
አሁን በኢትዮጵያ ግፍ በዝቷል። ከዚያ በፊት በነገሥታት ፍርድ እንጂ በህዝብ ዘንድ ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ ወንጀልና የድፍረት ኃጢአት በዝቷል። በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያውያን ክፋት መጠን በዓይነትም በብዛትም ጣሪያ ነክቷል።
በምሥራቅ ኢትዮጵያ ካህናት ታርደዋል። ቤንዚን ተርከፍክፎባቸውም በመንበሩ ፊት ከመሰዊያው አጠገብ ተቃጥለው እንዲሞቱ ተደርገዋል። አብያተ ክርስቲያናትም በእሳት እንዲወድሙ ተደርገዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያም ሰው በቁሙ ቤንዚል ተርከፍክፎ ሲቃጠል አይተናል። ያው ቢንዚን አርከፍካፊዋ፣ ክብሪት ጭራ አቃጣይዋ ሴት መሆኗን አይተናል። በሻሸመኔም ፅንፈኛው ቄሮ ኢትዮጵያዊ ወንድሙን በአደባባይ ከዶሮ እንኳ ባነሰ ክብር አንጠልጥሎ ቀጥቅጦ ገድሏል።
በጎጃም በደቦ ፍርድ ለጥናት የሄዱ ምሁራን ተቀጥቅጠው በአደባባይ ተገድለዋል፣ በወልቃይት፣ በራያ፣ የብዙ ንፁሐን ህይወት ለ27 ዓመታት በግፍ ተቀጥፏል። አሁንም እየተቀጠፈ ነው።
ከሁሉም ከሁሉም ደግሞ ታላቁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቅ መሪጌታ እንደሥራቸው አግማሴ ለ25ዓመታት በትግራይ ምድር በግፍ ያለ ፍርድ ታስረው እየማቀቁ ይገኛሉ። እነሰም በዛም ግን ግፍ ፈጻሚዎች ሁላቸውም በያሉበት የእጃቸውን ያገኛሉ።
እናም የዚህ ሁሉ ግፍ ድምር ውጤቱን ዐይናችን እያየ፣ ጆሮአችንም እየሰማ እናጭደዋለን። የመንገድ መዘጋጋቱ ሲገርምህ እሳት እየዘነበብህ ነው። ይሄኔ ነው መባነን። ይሄኔ ነው መሸሽ።
አሁን በኢትዮጵያ የጭንቀት ዘመን ነው። ከትግራይ አንስቶ እስከ ሶማሌ። ከአፋር እስከ
አሶሳ፣ ደቡብም ሰሜንም ጭንቀት ላይ ነው።
ነብየ እግዚ አብሔር ዕንባቆም በትንቢት መጽሐፉ " የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ። " ዕንባ 3፣ 7 ያለው ትንቢት እየተፈጸመ ይመስላል። ይሄ በእግዚአብሔር ቁጣ የሚመጣ እንጂ በፀረ ሰላም ሃይሎች የሚፈጸምና የጦስ ዶሮ የምንፈልግለት ዜና አይደለም። በቃ የእግዚአብሔር ቁጣ ነው።
ኃጢአትና ግፍ በምድር ላይ በበዛ ጊዜ እግዚአብሔር እሳትን ከሰማይ አዝንቦ ምድርንና በምድር ላይ ያሉትን ይቀጣ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። ይሄ የቆየ ልማድ ነው። "
[ዘፍ 19፣ 24]
እግዚአብሔርም በሰዶምና በገሞራ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሰማይ እሳትና ዲን አዘነበ፤"።
ቅዱሳንም በሰዎች ልጆች ግፍ ባዘኑ ጊዜና ወደ ፈጣሪያቸው ምርር ብለው ባመለከቱ ጊዜ በበረዶና በእሳት እልኸኞችንና የማይታዘዙትን ሁሉ እግዚአብሔር ይቀጣ እንደነበር በ በኦሪት ዘጸ 9፣ 23 ላይ ተጽፎ እናነባለን። "ሙሴም በትሩን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ነጎድጓድና በረዶ ላከ፥ እሳትም ወደ ምድር ወረደ፤ እግዚአብሔርም በግብፅ አገር ላይ በረዶ አዘነበ።"
ቅዱስ ጳውሎስም ይኸውም፥ ለበደለኞችና ለማይታዘዙ፥ ለዓመጸኞችና ለኃጢአተኞች፥ ቅድስና ለሌላቸውና ለርኵሳን፥ አባትና እናትን ለሚገድሉ፥
ለነፍሰ ገዳዮችና ለሴሰኞች፥ ከወንድ ጋርም ለሚተኙ፥ በሰዎችም ለሚነግዱ፥ ለውሸተኞችም በውሸትም ለሚምሉ፥ የእግዚአብሔር ፍርድ ቅርብ እንደሆነች ይነግረናል። 1 ጢሞ 1፣ 9-11 "በምድር የሚደረግ ከንቱ ነገር አለ፤ በኀጥኣን የሚደረገው ሥራ የሚደርስባቸው ጻድቃን አሉ።" መክ 8፣ 14። ይኼ ማለት ለኃጥአን የታዘዘ ለጻድቃን ይተርፋል እንደማለት ነው።
መጥፎነቱ ደግሞ በዚህ ዘመን ከፈጣሪ ጋር የሚያስታርቁ የሃይማኖት አባቶች አለመኖራቸው ነው። ማስታረቁ ይቅር ለራሳቸውም አስታራቂ የሚፈልጉ፣ ከገዳም ይልቅ ኒውዮርክ መመደብን በዚያም ማገልገልን የሚሹ እነ " ሰው ቢቸግር፣ እነ ሰው ቢጠፋ " የሆኑ በእነ አቡነ ጴጥሮስና በእነ አቡነ ሚካኤል ዘጎሬ ወንበር ላይ የተቀመጡ መብዛታቸው ነው።
በሐረርጌ ክፋለ ሀገር እሳት ዘነበ። ለጅጅጋው ግፋ ፍርድ ይሆን?
On Nov 9, 2018 2:35 AM, wrote:
Blogger Comment
Facebook Comment