የዓለም ቁንጮ ሰላቢ እጆች በረቀቀ ዘዴ ከሚፈፅምዋቸው ሴራዎች የዓለም ህዝብ ቁጥር መቀነስ (depopulation) ዋነኛው ነው። ተከታዮ የ Afrihealth TV ዘገባም ይህንን የሚያረጋግጥ ነው።
ላንሴት በተሰኘው የምርምር መጽሔት ላይ የታተመ አንድ ጥናት የዓለም የወሊድ ምጣኔ እየቀነሰ መሄዱን ይፋ አድርጓል፡፡
አዲስ ይፋ የተደረገው ጥናት ከአውሮፓውያኑ 1950 እስከ 2017 ያለውን ጊዜ የዳሰሰ ሲሆን በውጤቱም የዓለም ሀገራት ግማሽ ያህሉ የችግሩ ተጋላጭ መሆናቸውን አትቷል፡፡
ከዚህም ሌላ በ1950ዎቹ ከነበረው አንዲት እናት የመውለድ ምጣኔ 4 ነጥብ 7 የነበረ ሲሆን ባለፈው ዓመት ወደ 2 ነጥብ 4 በመቶ መውረዱን ጥናቱ አሳይቷል፡፡
ይህ በዚህ የሚቀጥል ከሆነ አለምን ስጋት ውስጥ እንደሚከታት ጥናቱ አመላክቷል፤ በተለይም በኢኮኖሚ የዳበሩ የዓለም ሀገራት ዋነኞቹ ሰለባዎች ናቸው ተብሏል፡፡
ባለሙያዎች እንደሚሉት የዚህ ችግር ምክንያት የልጆች ሞት፤ የወሊድ መከላከያዎች እንደልብ መስፋፋት እና ሴቶች ከየትኛውም ጊዜ በላቀ በትምህርትና በስራ መጠመዳቸው ነው፡፡
# ዘርአዳዊት_ዘ_ኢትዮጵያ
# ኢትዮጵያ_አውታር
# ሰላቢ_እጆች
Blogger Comment
Facebook Comment