ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ 1960ዎቹ በምዕራባውያን የኢሉሚናቲ መንፈስ (ርዕዮተ ዓለም የሚሉት) የሠከሩ ራሥዎ ልጆች የእግዚአብሔር መንግሥት ጠባቂ የነበሩት ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ካስወገደች በኃላ በታላቅ ጥፋት ውስጥ ትገኛለች።
ህወኅትና አለቃዋ መለስ ዜናዊ ዐምሓራ (ነፃ ህዝብ ክርስትያን) በኢትዮጵዊ እንዲጠላ በማድረግ የኮሚኒስት የጥፋት መንፈስ አገልግሎ አልፏል። ይህ ደግሞ ከጊዜ በኃላ በትግራዋይ ላይ ጥላቻ እዲፈጠር አድርጓል። ይህም ምዕራባውያን ሰላቢ እጆች ኢትዮጵያን በዲያብሎስያዊ ሴራቸው ለመቆጣጠር የሚያደርጉት የሄግል problem -reaction - solution ቀመር ነው። የትግራይና የዐምሓራ ፖለቲከኞች፡ ሊህቃን ነን ባዮች ሳያውቁ አውሬውን እያገለገሉት ነው።
ሉሲፈራውያኑ ላለፉት 50 ዓመታት ከፍተኛ ትኩረት ያደረጉት የተዋሕዶ ክርስትና መሰረት በሆነው ሰሜናዊ ግዛት ላይ ነው። ለዚህም በተደጋጋሚ ሲታዩ የነበሩት፤ ረሃቡ፣ በሽታው፣ ጦርነቱ፣ አስገድዶ ማፈናቀሉ፤ ይመሰክራሉ። ከሌሎች የኢትዮጵያ ግዛቶች የበለጠ እዚህ ይፈጸም ነበርና።
በለንደኑ ስምምነት መሠረት፡ ላለፉት 27ዓመታት መንግስታዊ ሥልጣኑን በከፊልም ቢሆን ለትውልደ ትግራዮች ከሰጡ በኋላ፡ የደቡቡ ኢትዮጵያ ግዛቶች ተወላጆችን(ኦሮሞ፣ ወላሞ፣ ሶማሌ፣ ጉራጌ)በፖለቲካው፣ በተለይ ደግሞ በምጣኔ ኃብትና ሃይማኖት ዘርፍ አገሪቷን እንዲቆጣጠሩና አሁን ለደረስንበት ዘመን እንዲያዘጋጇቸው አደረጓቸው፤ አንድ አዲስ ትውልድ ፈጠሩ ማለት ነው።
ህወኃት ኢትዮጵያዊነት ለመግደል ዐምሓራ ላይ በፈጠራ ታሪክ እንዲጠላ ካደረገች በኃላ፡ ለዶ/ር ዐቢይና የትግል ዘመዶቹ በዚህ መልክ ሥልጠና ካደረጉ በኋላ አመቺ ጊዜ በመጠበቅ (የሰው በትግሬ ላይ ያለው ጥላቻ ከፍተኛ ደረጃ እስኪደርስ ድረስ)ሥልጣን ላይ አወጧቸው። የዶ/ር ዐቢይ በሞኙ ሕዝባችን ተወዳጅነት ማትረፍ ሰው ሁሉ በትግሬ ላይ ምን ያህል ጥላቻ እንዳለው ነው የሚያንጸባርቀው፤ ሌላ ለዚህ ዓይነት ተወዳጅነት የሚያበቃ ምክኒያት ሊኖር አይችልም፤ ዜሮ። ይህ ነው እንግዲ የምዕራባውያን ቀመር ኢትዮጵያን ማፈራረስ። መለስም ሆነ ዐቢይ የተለያየ መልክ ያላቸው የአንድ ሣንቲም ሁለት ገፅታ።
የሉሲፈራውያኑ ሤራ ዒላማውን እየመታ ነው፤ ዋናው ዒላማቸውም ተዋሕዶ ክርስትና ናት፤ የተዋሕዶ ክርስትና መሠረት ሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ነው። ትግራይና ዐምሓራ ከተዋጉ ለብዙ ዕቅዶቻቸው እንቅፋት የሆነችውን ተዋሕዶን አጠፉ ማለት ነው። አሁን ትግራይን በመክበብ፥ ልክ አረቦችና ፀረ-ሴማውያን የሆኑት ኍ በአይሁዶች ላይ እንደሚያሳዩት ጥላቻ፤ ትግሬዎችንም እንዲሁ መጥፎ ስም እየሰጡ በመኮነን እና በመተናኮል ላይ መሆናቸውን ሁላችንም የምናየው ነው።
ብዙ ጊዜ የሕዝቦች እልቂት ከመጀመሩ በፊት አንዱ የሕዝብ ክፍል ይለይና መጥፎ ስም እንዲሰጠው ይደረጋል፣ ይንቋሸሻል(ውሻውን መጥፎ ስም ሰጥተህ ገደለው!)እንዲሉ። ከዚያም የራሴ ነው፣ እወደዋለሁ፤ "በውስጤ ነው" የምንለውን ሰው እንድናጣው እንደረጋለን። ብዙ ጊዜ በደንብ በተቀነባበሩ ስሜታዊና አስደናቂየአውሮፕላን ላይ ግድያዎች።
ግራኙ ዐቢይ አሕመድን ተወዳጅ እንዲሆን ለማድረግ ከሁሉም አቅጣጫ ተሞክሯል፤ የእኛን በጎ መሆን የማይመኙት ምዕራባውያን እና አረቦች እንኳን ያጨበጭቡለታል። ቀጣፊው የእንግሊዝ መንፍስት ቱልቱላ፡ ቢቢስ እንኳን ባለፈው ዐርብ "Abiy-mania: Ethiopia Transformed" በሚል አርዕስት ውዳሴ ዐቢይን ፅሑፍ አትሟል።
ዐቢይን የአውሮፕላን በረራዎች እንዲያበዛ፥ በተለይ ደግሞ ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ቶሎ ቶሎ እንዲገናኝ ወይም አብሮ እንዲበር አዘውታል።
ይህ ሁኔታ ምንን ነው የሚያስታውሰን?አዎ! እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 6 ቀን 1994 ዓ.ም ምሽት የሩዋንዳን እና የቡሩንዲን ፕሬዚደንቶች ይዛ ትበር የነበረች አውሮፕላን በሚሳኤል ተመታ ፕሬዚደንት ጁቨን ሀቤራማና እና ሲፕሪንኔታሪማ ተገድለዋል። የሁለቱ ፕሬዚደንቶች መገደለም ለሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀል መንስኤ ነበር።
የፕሬዚደንቶቹን አውሮፕላን ለመምታት ተጠያቂዎቹ ምዕራባውያን እንደሆኑ አንዳንድ መረጃዎች ይናገራሉ። በጊዜው የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ የነበሩት ግብጻዊው ቦትሮስ ቦትሮስ ጋሊ በአንድ ወቅት፡ "ለሁሉቱ ፕሬዚደንቶች መገደል የአሜሪካው የስለላ ተቋም፡ ሲ አይ ኤ ተጠያቂ ነው" ብለው ነበር።
በኢትዮጵያችንስ ተመሳሳይ ፅንፈኛ የሆነ ተግባር ለመፈጸም ታቅዶ ይሆን?
እስኪ እናስበው፡ ሞኙ ሕዝባችን አሁን በሚገኝበት ስሜታዊ ቅዠት ላይ ጠ/ሚንስትር አብይ አህመድን እና ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቅን የያዘቸው አውሮፕላን ተመታ ሕይወታቸውን ቢያጡ ምን ሊከተል እንደሚችል። ትግሬዎች ናቸው አውሮፕላኑን የመቱት በማለት፤ በትግራይ እና ትግሬዎች ላይ የሩዋንዳ ዓይነት እልቂት ይመጣል ማለት ነው። አዎ! በቂ የጦር መሣሪያ ከሱዳን በጎንደር በኩል፣ ከሶማሊያ በጅጅጋ በኩል በማስገባት ላይ ናቸው።
ይህ ዕልቂት የማይቀር ይመስላል። ከ40 ዓመት በላይ በኢትዮጵያ ላይ በልጆችዎ የተፈፀመው ክህደትም ይቋጫል። ኢትዮጵያ ግን ትቀጥላለች።
Blogger Comment
Facebook Comment