ለ አንደኛው እና ለሁለተኛው የዓለም ጦርነቶች መንሥኤዋ ኢትዮጵያ ናት፦


ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብ በአሰቃቂ ሁኔታ ያለቀበት አንደኛው የዓለም ጦርነት ካበቃ ባለፈው እሁድ 100 ዓመት አስቆጠረ። እለቱ ከትናንት በስቲያ ፓሪስ ፈረንሳይ ውስጥ የዓለም መሪዎች በተገኙበት ታስቧል።

በዚሁ የመታሰቢያ ስነ-ስርዓት ላይ የፈረንሳዩ ፕሬዚደንት ንግግር ሲያሰሙ፤የአረብ ሞሮኮ ንጉስ ሲያንቀላፉ የአሜሪካው ፕሬዚደንት ትራምፕ ክፉኛ ሲገላምጧቸው ታይተዋል።

ለ አንደኛው እና ለሁለተኛው የዓለም ጦርነቶች መንሥኤዋ ኢትዮጵያ ናት፦

የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት በአውሮፓ አገሮች መኻል ከ ፲፱፻፮ 1906 ዓ/ም እስከ ፲፱፻፲፩ 1911ዓ/ም መግቢያ፣ ለአራት ዓመታት የተካሄደ ጦርነት ነው። ይኼ ግጭት የዘመኑ ኃያላን አገራት በሁለት ተቃራኒ ወገን ተሰልፈው ያካሄዱት ግብግብ ሲሆን እስከ ሰባ ሚሊዮን ታጣቂዎች የተካፈሉበትና እስከ አስራ አምስት ሚሊዮን አውሮፓውያን ሕይወታቸውን ያጡበት ትልቅ ጦርነት ነው።

በ ፲፰፻፹ 1880 ዎቹ እኤአ የአውሮፓ መንግሥቶች በበርሊን ጉባኤ ተስማምተው አፍሪካን በቅኝ ገዢነት መከፋፈል ጀመሩ። በኢትዮጵያ እና ጣልያን መካከል የነበሩ የዚያ ዘመን ውዝግቦች ወደ አድዋ ጦርነት በ ፲፰፻፹፰1888 ዓም አመሩ። በጦርነቱ የጣልያን ትልቅ ዘመናዊ ጦር በኢትዮጵያ ጦር ትልቅ ሽንፈት የደረሰበት መሆኑ ዓለምን አስደነቀ።

አንደኛው የኢትዮጵያና ጣሊያን ጦርነት በኢጣሊያ እና ኢትዮጵያ መካከል፡ እ.ኤ.አ ከ1895 እስከ 1896 ድረስ የተካሄድ ጦርነት ነው። የኢትዮጵያ በአድዋ ላይ ድል መቀናጀት አውሮፓን ከፍተኛ ቀውጥ ውስጥ ጣላት።

በድኽረ ፪ኛው የዓለም ጦርነት ወቅትም አገራችን ኢትዮጵያ በ፲፱፻፳፰ ዓ/ም በፋሽስት ኢጣልያ በግፍ መወረር የሁለተኛው የዓለም ጦርነት መነሻ ምክንያት ነበር።

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment