ጴንቴኮስታሊዝም በኢትዮጵያ | አምላክ ኢትዮጵያውያንን እንዲበለጽጉ ይመኛል!
የምዕራቡን ዓለም ነዋሪዎች መንፈሳዊ ሕይወት ያደቀቀው የ “ብልጽግና ወንጌል” ወይም “Prosperity Gospel“ በመባል የሚታወቀው የ666ቱ አምልኮ ኢትዮጵያን ኃብታም ሊያደርጋት ነው፥ ማለቱ ነው…
የእንግሊዙ “ዘ ኢኮኖሚስት” (የምጣኔ ኃብት ጉዳዮች ላይ ማተኮር የሚገባው ጋዜጣ ስለ ሃይማኖት ያወራል) በሚል ርዕስ ጴንጤዎች በኢትዮጵያ ድል እየተቀዳጁ መሆናቸውን በመኩራራት ይናገራል፤ አብይ አህመድ፣ ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ ለማ መገርሳ እና ሌሎች ቁልፍ የሆነውን ስልጣን የያዙትም ጴንጤዎች ናቸው፤ እንኳን ደስ ያለን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን ድል በማድረጋቸው፥ ይለናል ይህ ታዋቂ የእንግሊዝ ጋዜጣ።
የሚገርመው በእንግሊዝ አገርም ሆነ በአሜሪካ የጴንጤዎች ቁጥር በጣም ዝቅተኛ መሆኑ ነው፤ መኖራቸውም አይታወቅም። ጴንጤዎችን እና ሙስሊሞችን እንደ ኢትዮጵያ በመሳሰሉት የደቡብ አገራት ያዘጋጇቸው መሳሪያዎች መሆናቸውን የምናየው ነው። ይህ ጋዜጣ ይህን ጽሑፍ ከምስራች ጋር ማቅረቡ ሌላ ምክኒያት የለም፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ላይ ጥላቻ ስላላቸው፤ ለረጅም ጊዜ በኢትዮጵያ ላይ የጠነሱስት ሤራ በፈጠነ መልክ ግቡን እየመታላቸው እንደሆነ መስሎ ስለተሰማቸው ነው። ለጊዜው ያቀዱትና ያዘጋጁት ዕቅድ ሁሉ ቅደም ተከተሉን ይዞ በመጓዝ ላይ ይገኛል፤ የተንኮል ችግኛቸውም በመብቀል ላይ ነው።
በ “እንግሊዛዊ” ተንኮል ከተሞላባቸው ዓረፍተ ነገሮች መካከል የሚከተለው ይገኝበታል፦
“Although there are few signs that Abiy favours Pentes at the expense of other faiths…”“ምንም እንኳን አቢይ የሌሎች እምነት ተከታዮችን በመጨቆን ለጴንጤዎች ማዳላቱን የሚጠቁሙ ጥቂት ምልክቶች ቢኖሩም….”
ይህ ሁሉ ነገር በገጠመኝ እንዳልሆነ ብቻ ሳይሆን፤ ለምን እንደሚሆንና መቸ እንደሚሆን በጥሞና መከታተል ይኖርብናል።
ይህ ሁሉ ውጣ ውረድ ዓለምንና ህዝቦቿን በረቂቅ ቴክኖለጂ አጋዥነት ጠቅልሎ በአንድ በሳጥናኤል አገዛዝ ስር ለማድረግ ሲባል ነው። ለዚህም ሁሉም በየፊናው ተሰማርቶ ይገኛል። የአገር መሪ፣ የሃይማኖት መሪ፣ ሳይንቲስቶች፣ ጋዜጠኞች፣ የሙዚቃውና የስፖርት ኢንደስትሪ ወዘተ… የሁሉም ትኩረት ኢትዮጵያ ናት፤ እንቅፋታቸው / መሰናክላቸው ተዋሕዶ ክርስትና ናት።
Blogger Comment
Facebook Comment