የኬንያው ሜሪስቶፕስ የውርጃ አገልግሎት እንዳይሰጥ ታገደ!




ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ አውታር የሜሪ ስቶፕስ ሰይጣናዊ የውርጃ ሥራ ለዓመታት ስትቃወም ነበር!
የኢትዮጵያ መንግሥት ከኬንያ ሊማር ይገባል!

የኬንያ መንግስት የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት የሚሰጠውን ሜሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል ድርጅት ማንኛውንም አይነት የፅንስ ማቋረጥ አገልግሎት መስጠት እንዲያቆም አገደ፡፡

መንግስት ይህን ውሳኔ ያስተላለፈው ድርጅቱ ፅንስ ማቋረጥን እንደሚያበረታታ ባደረኩት ምርመራ አረጋግጫለው ማለቱን ተከትሎ ነው፡፡

በኬንያ የእናት ህይወት አደጋ ላይ እስካልጣለ ድረስ ውርጃ ህገወጥ ነው፡፡

ሜሪስቶፕስ በበኩሉ በኬንያ ህጉን ተከትሎ አገልግሎቱን ከፅንስ ማቋረጥ በኋላም ለእናቶች የጤና ክትትልና የማማከር አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡
አንዳንድ ኬንያውያን የመንግስት ውሳኔ ተከትሎ ሴቶች ለህገወጥ ውርጃ እንዳይጋለጡ ስጋት አላቸው፡፡
ሜሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል በአለም ትልቁ የወሊድ መቆጣጠሪያና ደህንነቱ የተጠበቀ የውርጃ አገልግሎትን በ37 አገራት የሚሰጥ ተቋም ነው፡፡
ድርጅቱ በኬንያ 22 ቋሚ እና 15 ተንቀሳቃሽ ክሊኒኮች አሉት፡፡ዘገባው ቢቢሲ ነው፡፡
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment