የምሥራች | የኢየሩሳሌሙ ገዳም የኢትዮጵያውያን መሆኑን እስራኤል እውቅናውን ልትሰጥ ነው!


ግብጾች ግን እንደገና በመንጫጫት ላይ ናቸው። በታሪክ ብዙ
መለኮታዊ ማስጠንቀቂያዎች የተሰጣቸው ግብጾች አሁንም ታሪክን እንዳፈለጋቸው ከልሰው ለመጻፉ ይሻሉ፤ ኮፕት ወገኖቻችን ለመማርና ንስሃ ለመግባት እስካሁን ፈቃደኞች አይደሉም፣ የፈርዖን ልበ ደንዳናነት አልተዋቸውም፥ እንኳን የአረብ ሙስሊም ቆሻሻነት ታክሎበት፥ ኢትዮጵያውያን መነኮሳትን አንለቅም እያሉ ነው።
እንግዲህ፤ በእግዚአብሔር እዉነት መገለጥ ማመን የእግዚአብሔር ሥጦታ እንደሚያሰጥ አለማመንም ለቅጣት ይዳርጋልና እውነትን ባለመቀበል ከክርስቲያን ወገኑ ጋር የማይተባበርም እንዲሁ በእራሱ ላይ መዘዝ ያመጣል።
በጣም የሚገርመው፡ ከ 1978 ዓ.ም እ.አ.አ ጀምሮ ግብጻውያኑ ኮፕቶች ወደ እስራኤል ወይም ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይጓዙ የኮፕት ሲኖዶስ ያወጣው ድንጋጌ ይከለክላቸዋል። እንግዲህ ከአረብና ፍልስጤም ሙስሊሞች ጋር ትብብርነት ለማሳየት ሲሉ።
በኢየሩሳሌም የኮፕቲክ ኦርቶዶክሱ የከተማ አስተዳዳሪ የሆኑት
አባ አንቶኒየስ, ወቅታዊውን የዴር ሡልጣን ሁኔታ በማስመልከት የሚከተለውን አግባብ የሌለው መግለጫ ሰጥተዋል፦
"ችግሩ ገና መፍትሄ አላገኘም ነገር ግን በቅርብ የእስራኤል ፍርድ ቤት ውሳኔዎች አንዳንድ ነጥቦችን አዘጋጅተዋል። የእስራኤሉ መንግስት የገዳሙን ጥገና ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ
መላው ቤተክርስቲያን ለማስፋት ይፈልጋል። ይህ ለኢትዮጵያ መነኮሳት ድል ይሰጣል [ኢትዮጵያውያኑ በአሁኑ ጊዜ አላግባብ
መያዝ አልበቃ ብሏቸው ከእኛ ኮፕቶቹ የመብት ባለቤቶች
ነጥቀው ሊወስዱት ይሻሉ] እና በገዳማት ውስጥ እንዲቆዩ ይደረጋል። በተጨማሪም በዚህ የእስራኤል ፍርድ ቤት ውሳኔ የኮፕቲክ ማንነት የሚጠፋ ይሆናል።"
"እ.አ.አ በ 1654 ዓ.ም የኢትዮጵያ መነኮሳት የታክስ ቀረጥ ለመክፈል ስላልቻሉ የኢትዮጵያውያን መነኮሳት በጊዚያዊነት በኮፕቲክ ቤተክርስትያን ውስጥ ለጥቂት ጊዜ መጠለያ አገኙ። የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን በዚያ ጊዜ በግሪክ እና አርሜኒያ
ዓብያተክርስቲያናት ይዞታ ሥር ቆይታለች። ኮፕቶች ኢትዮጵያውያንን በእንግድነት ተቀብለው በዴር ሡልጣን
አስተናገዷቸው፤ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ግን እንደ እንግዳ ሆነው ነበር የቆዩት። የኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያን ገዳሙን በ 1820 ዓ.ም
ማደስ እና ነዋሪዎቹን ማስወጣት ሲኖርበት ኢትዮጵያውያን እንደገና በ 1840 ዓ.ም ወደ ታደሰው ቦታ እንዲገቡ
ፈቀደችላቸው። በወቅቱ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አካል ነበረች።
እ.ኤ.አ. ኤፕሪል 1970ዓ.ም የኮፕት መነኮሳት የትንሳኤ ዋዜማን ለማክበር ወደ ቅዱስ ሴፕቸር ቤተክርስቲያን ሲያመሩ እንግዶቹ
የኢትዮጵያ መነኮሳት አጋጣሚውን በመጠቀም ገዳሙን ከቤተክርስቲያን ጋር የሚያገናኘውን በር ቁልፍ ቀይረው ገዳሙን
በተግባር ተቆጣጠሩት። ይህም የተደረገው በእስራኤል መንግስት ድጋፍ እና ከእስራኤል ወታደሮች ጥበቃ ስርዓት ጋር
ነው። በወቅቱ ግብጽ እና እስራኤል ጦርነት ላይ ነበሩ።"

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment