ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
የ 5ኛው ትውልድ (5G) አውታረ መረብ (network) ዓለምን በከፍተኛ ደረጃ ይቀይራል ተብሎ የሚገመት አዲስ የቴክኖሎጂ ደረጃ ነው። ወደ 5ኛው ትውልድ የሚደረገው ሽግግር የበይነመረብ ፍጥነትን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ቴክኖሎጂዎች ሙሉ አቅም እንዲኖራቸው ያስችላቸዋል። 5ኛው ትውልድ በተጨማሪም የዓለም አቀፍ አውታረ መረብ እድገት (internet) ለማፋጠን ያስችላል። ይህ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተራዘመ እና ዘላቂ እና ዘመናዊ ከተማዎችን ለመገንባት ዕቅድ-2030 በሚል በቀረጸው ዕቅድ አካል ነው። በመጨረሻም፣ ሊገናኙ የሚችሉ ማንኛውም ነገሮች ፡ ይገናኛሉ።
ምንም እንኳን 5G የላቀ ቴክኖሎጂ ቢሆንም ከጎጂ ጨረር ጋር የተቆራኘ ነው። 5G አነስተኛ ድጝሞሽን ባንዶች በመጠቀም የተገነባ እንደመሆኑ መጠን፣ በየ 60 ጫማ ርዝመት ብዛት ያላቸው አንቴናዎች ማሰራጫዎችን ይጠይቃል። ወደ ሽቦ አልባ ጨረር መጋለጥ የካንሰር፣ የአንጎል ዕጢዎች እና የልብ እና የደም ሥር (Cardovascular) በሽታዎች ይዳርጋል። እነዚህ ሁሉ መርዛማ ጨረሮች የዲ. ኤን.ኤ ጉዳት እና የዘረመል ቅየራ (Genetics mutation) ያስከትላሉ። እንዲያውም አንዳንድ ሰዎች ይህ ቴክኖሎጂ የሰውን ዘር ፍፃሜ ያፋጥነዋል ብለው ይናገራሉ።
በአምሳለ እግዚአብሔር የተፈጠረው ክቡር የሰው ልጅን ቁጥር የመቀነስ ዕቅድ ያላቸው የዓለማችን የሥልጣን ቁንጮዎች ይህንን ቴክኖሎጂ ለክፉ ዓላማቸው ይጠቀሙበታል። አጀንዳው ሰውን ከሰው ሰራሽ ማሽኖች ጋር ማዋሃድ ነው። በቅርቡ ኢትዮጵያውያን የተሳተፉባት ወደ ሃገራችን መጥታ የነበረቺው የ 666 መልዕክተኛ “ሶፍያ” ሮበት ማስታወስ በቂ ነው። እነዚ የስማዝያ ጭፍሮች እኛን ሊገድል የሚችል ከባቢ አየር እየሰሩ ወይም እየበከሉ ናቸው። ይህንን ተከትሎ መፍትሄ ሰጪዎች ሆነው በመቅረብ ድህረ-ሰዎች ወይም H+ ለመፍጠር ይፈልጋሉ። የ H + ትውክልት ፕላኔቷ ሳተርን ነች። ሳተርን ባዕድ አምልኮ ከሚፈጸምባቸው ግዑዝ ነገሮች አንዷ ነች።
እነዚህ መናፍስታዊ እምነት ተከታዮች ዘመናዊው የሰው ልጅ የ 5 ኛ ወይም 6 ኛ መሠረታዊ ዘር ነው ብለው ያምናሉ። ማሻሻያውን የማይቀበሉ ሁሉ ይገደላሉ። ነገር ግን ክርስቲያኖች ይቅር የማይባል ኃጢአትን ስለሆነ የሰይጣንን አስመሳይነት አንፈልግም። በቴክኖሎጂ ሽፋን እየመጣብን ያለው ፈተና ወደ እግዚአብሔር ፊታችን በመመለስ እናሸንፈው።
ንቁ! እንንቃ!
እሁድ ጥቅምት 04, 2011 ዓ/ም
Blogger Comment
Facebook Comment