ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ፖለቲካ ዕውነት በመደፋጠጥ በምናብ ብቻ እንድትኖር የሚያደርግ የመናፍስታውያን (occulist) መሣርያ ነው።
አዎ! ዲያብሎስ በቋንቋ እርስበርሳችን እንድንጨፋጨፍና በእንግሊዝኛ ወይም በአረብኛ እንድንነጋገር ከማስገደዱ በፊት ፈጥነን ግዕዝ ቋንቋን መማር አለብን።
ግእዝ የእግዚአብሔር ቋንቋ ነው ተብሎ በትዉፊት ይነገራል
ትውፊታዊ ታሪኩ
ግዕዝ የእግዚአብሔር ቋንቋ ነው ተብሎ በትዉፊት ይነገራል። ፍጥረታት በሐሌዎ‘ በነቢብና በግብር የተፈጠሩ ሲሆን በተለይ ነቢቡ (ንግግሩ) ግዕዝ ነበር ብለዉ የሚከራከሩና የራሳቸውን ማስረጃ የሚያቀርቡ ሊቃውንት አሉ። ግዕዝ የመጀመሪያ ቋንቋ ነው ስንል አዳም ማለት ያማረ የተዋበ ማለት ሲሆን አባቶቻችን በመንፈስ ቅዱስ እየተመሩ ከጻፏቸው መጻሕፍት እና ሌሎች ድርሰቶች ተነስተን ቅዱስ ገብርኤል “ንቁም በበህላዌነ” ብሎ ሠራዊተ መላእክትን ያረጋጋው በግዕዝ ነው፤ አዳምም ለ ፯ ዓመታት በገነት ሳለ በፀሎት ሲተጋ የነበረውና ከሄዋን ጋር ይነጋገርበት የነበረው ቋንቋ በግዕዝ ነው በማለት ቋንቋውን የመላእክትም የሰውም መግባቢያ ያደርጉታል።
ግዕዝ የአዳምና ሔዋን (የተፈጥሮ ቋንቋ) የመጀመሪያው መነጋገሪያ ልሳን መኾኑ ለማረጋገጥ ከሚያቀርቧቸው ፲ ምክኒያቶች መካከል፦
፩ኛ. የ ”ግዕዝ” የጥሬ ዘሩ ቃል ትርጉም፡ “መጀመሪያ”, “ነፃ” እና “የጥንት ተፈጥሮ ጠባይ ወይም ባህሪይ” ማለት መኾኑ
፪ኛ. የእያንዳንዱ ፊደል የመጀመሪያ ቅርጽ አፍ ሳያስከፍት በድን በኾነው በተፈጥሮ ድምፅ ብቻ የሚነገር መኾኑ
፫ኛ. የፊደሉ መነሻ “አ” “አዳም” በሚል ቃል በወንድና ሴት ጾታ ለተፈጠሩት ለመጀመሪያዎቹ ሰዎች መጠሪያ መኾኑ
፬ኛ. በሰባት ብዛት የሚወሰን ቁጥር፤ የመለኮታዊ ሥራ ምሥጢር እንዳለበት ስለሚታመን፤ እያንዳንዱ ፊደል፤ በሰባት ስሞች ድምጾችና መልኮች ተለይቶ የሚታወቅና የሚነገር መኾኑ
፭ኛ. ሌሎቹ የሰዎች ቋንቋዎችና ፊደሎቻቸው በተናጋሪዎቻቸው ሕዝቦች ወይም ጎሣዎች ስም ለምሳሌ፤ ዐማርኛ፤ በዐምሓሮች፤ ትግርኛ በትግሬዎች፣ ኦሮምኛ በኦሮሞዎች፣ ሶማልኛ በሶማሌዎች፣ ዕብራይስጥ በዕብራዊያን፤ ዐረብኛ በዓረቦች፣ እንግሊዝኛ በእንግሊዞች፣ ቻይንኛ በቻይኖች ስም ሲጠሩ “ግዕዝ” ግን በራሱ ብቻ የሚጠራ መኾኑ
፮ኛ. በ ”አ” ጀምሮ በ “ኦ” የሚፈጸም ፊደል ያለው እርሱ፤ ግዕዝ ብቻ ከመኾኑ ጋር “አልፋና ኦሜጋ፤ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ” ብሎ፡ ኃላ “ኢየሱስ ክርስቶስ” ተብሎ፤ ራሱን በሰውነት የገለጸው “እግዚአብሔር” በዚህ ስሙ የታወቀበትና አምልኮቱ የሚፈጸምበት ቋንቋና ፊደል ኾኖ በሕያውነት እስከዛሬ መቀጠሉ
፯ኛ. በምድር ላይ የሚኖሩ የሰው ልጆች ኹሉ፡ ተወልደው በሕፃንነታቸው መናገር በሚጀምሩበት ጊዜ ቋንቋቸውና ፊዲፈላቸው የተለያዩ ሲኾኑ፤ አፋቸውን መፍታት አባቶቻቸውናና እናቶቻቸውንም ለይተው መጥራት የሚጀምሩበት “አባባ”፤ “እማማ!” የሚባሉት ቃላት “አብ አብ አብ”፤ “እም እም እም” የተባሉት፤ ትርጉማቸው፡ “አባት አባት አባት”፡ “እናት እናት እናት” የኾነውን ቀጥታ የግእዙን ቃላት መኾኑ ናቸው።
፰ኛ. «ግዕዝ» የሚለው ቃል እራሱ አንደኛ፣ የመጀመሪያ ማለት ነው። የሰው ልጅ የመጀመሪያ የሆነው ቋንቋ “አንደኛ” ቢባል ይስማማዋል።
፱ኛ. የዚህ ቋንቋ የመጀመሪያው ተናጋሪ ሰው አዳም ነው። የዚህ ሰው ስም በቋንቋው ትርጉም ሊኖረው ይገባል። በግዕዝ «አዳም» ማለት ያማረ ማለት ነው።
፲ኛ. ሌላው ነገር የግዕዝ ፊደላት ከአምላክ የተገኙ ናቸው ለዚህም የአዳም ሶስተኛ ትውልድ የሆነው ሄኖስ በሰማይ ገበታ እንዳያቸው አባቶች ይናገራሉ።

Blogger Comment
Facebook Comment