የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የትግራይ ሀገረ ስብከት ትግርኛ ቋንቋ መጠቀም አለባት የምትሉ ለሃይማኖተ ተቆርቋሪ መሳይ የፖለቲካ ካድሬዎች

ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የትግራይ ኃገረ ስብከት ትግርኛ ቋንቋ የመጠቀም እግዚአብሔራዊ የሆነ "ነፃ ፍቃድ" አለው። የናንተ ተቆርቋርነት ግን መሠረቱ የፖለቲካ ጥላቻ በመሆኑ አስገራሚ ያደርገዋል።

ቋንቋን እግዚአብሔር አልፈጠረም፤ በቋንቋ መንግስተ ሰማያት አይገባም፡ ነገር ግን የመጀመሪያው አዳምም ለ ፯ ዓመታት በገነት ሳለ በፀሎት ሲተጋ የነበረውና ከሄዋን ጋር ይነጋገርበት የነበረው የመጀመሪያው ቋንቋ ግእዝ ስለሆነ እርስበርስ ለመግባባት እንችል ዘንድ ሁላችንም አሁን ግእዝ ቋንቋን ማወቅ ሊኖርብን ነው።

አዎ! ዲያብሎስ በቋንቋ እርስበርሳችን እንድንጨፋጨፍና በእንግሊዝኛ ወይም በአረብኛ እንድንነጋገር ከማስገደዱ በፊት ፈጥነን ግእዝ ቋንቋን መማር አለብን።

በእውነት ስለ ሃይማኖታቹ የምትቆሮቆሩ ከሆነ፥ የተዋህዶ ሃይማኖትና ዐምሓራ [ዐም ማለት ህዝብ፡ ሓራ ማለት ነፃ እግዚአብሔር ብቻ የሚያመልክ ነፃ ህዝብ ማለት ነው።] ዳግመኛ እንደማይነሣ አድርገን አከርካሪው መተነዋል የሚሉት የህወሓት አለቆች ተው በልዋቸው። በመቐለ ከተማ የከሣቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ በተሃዶሶ መዋቅር የመናፍቃን መናኸርያ ያደረግዋት የእናታቸው ጡት ነካሽ አካላት በሰላማዊ መንገድ አስቅምዋቸው። የተዋህዶ ሥርዓት በካቶሊክ ሥርዓት እየቀየሩ ያሉ አካላት ተው በማለት ተከራከሩ። በመቐለ ከተማ የሚገኝው "ደብረ ሰላም ቅድስ ሚካኤል ካቴድራል" እንደ ምሳሌ በመውሰድ ካቴድራል የሚል የካቶሊክ ሥርዓት መገለጫ የሆነው ቃል ከየተዋህዶ አብያተ ክርስትያናት እንዲነሱ አድርጉ።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment