ኢትዮጵያ በእግዚአብሔር የመሰረተችና በቅዱሳን ቃል ኪዳን የተጠበቀች፤ ከሁል በላይ ደግሞ የድንግል ማርያም አስራት አገር ስለሆነች እንኳን በአገር ዉስጥ ለጥፋቷ የተሰለፉ ፖለቲከኞችና አስመሣዮች አይደለም፤ እርሷን ለማጥፋት የተሰለፉ የዉጭ መንግሥታት ሰላቢ እጆች (Illuminati) በሙሉ በእግዚአብሔር ቁጣ ይጠፋሉ፤ ከምድር ይጠረጋሉ። እርሷ ግን በእግዚአብሔር መንግሥትነቷ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ትቆያለች። ታዲያ አሁን ቢሆን "የአዲሲቷ ኢትዮጵያ መሪዎች ነን" እያሉ ህዝባችን በተለይ ወጣቱ ግራ በማጋባት በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ላይ የሚያላግጡ ፥ እርሷን ለማጥፋት የተሰለፉ የተለያዩ ቡድኖችና ድርጅቶች እንዲሁም መንግሥታትና ግለሰቦች ዛሬ ነገ ሳይሉ በእዉነተኛ ንስሐ ለእግዚአብሔር እጃቸዉን ቢሰጡና ወደማንነታቸዉ ወይንም ወደ ኢትዮጵያዊነታቸዉ ቢመለሱ የሚበጃቸዉ እንደሆነ በዚሁ አጋጣሚ መልእክቱን አቀርባለሁ።
ኢትዮጵያ እንኳን ዜጎቿን "ኢትዮጵያዉያን ነን" የሚሉትን ቀርቶ የዓለምን ሕዝብ ትመራለች ብንላችሁ "ኡ!ኡ!"ልትል ስለምትችሉ የንስሐ እድሜ ካገኛችሁ ተፈጽሞ እንደምታዩ እንነግራችኋለን።
ኢትዮጵያዊነት ታላቅ ክብር ነው!
#ዘርአዳዊት_ዘ_ኢትዮጵያ
Blogger Comment
Facebook Comment