በሴቶች እኩልነት ሽፋን እየተደረገ ያለ ሴራ በኢትዮጵያ!


ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ


ምዕራባውያን ፡ የዘቀጠ ፡ ከእግዚአብሔር ፡ የእውነት ፡ መንገድ ፡ ያፈነገጠ ፡ ባህላቸው ፡ ልምዳቸውና ፡ ድርጊታቸው ፡ ከሚጭኑብን ፡ መንገዶች ፡ አንድ ፡ የተለያዮ ፡ ድርጅቶች ፡ ማህበራት ፡ የበጎ አድራጎት ፡ ድርጅቶች ፡ በመመሥረት ፡ ድብቅ ፡ ዕቅዳቸው ፡ በሚልዮን ፡ የሚቆጠር ፡ ብር ፡ በመበጀት ፡ ማሥፈፀም ፡ ነው።

በማህበራዊ ፡ የትሥሥር ፡ ድረ - ገፆች ፡ The Yellow Movement ፡ በተሰኝ ፡ የሴቶች ቡድን  #የጳጉሜንቅናቄ #PagumeActivism በሚል ፡ እየተካሄደ ፡ ያለው ፡ ንቅናቄ ፡ ተፈጥሮ ፡ ምሥክር ፡ የሆነቺው ፡ የሴትና ፡ ወንድ ፡ ልዮነት ፡ Feminism ፡ በሚል ፡ የምዕራባውያን ፡ የሰይጣን ፡ ፍልስፍና ፡ ሴቶችን ፡ ከወንድ ፡ ጋር ፡ እኩል ፡ ናቸው ፡  በሚል ፡ የተሳሳተ ፡ መፈክር ፡ ሴት ፡ ልጆች ፡ ወንድ ፡ እንዲጠሉ ፡ በማድረድ ፡ ሴቶች ፡ ከሴቶች ፡ ጋር ፡ ኢ-ተፈጥራዊ ፡ የሆነ ፡ የወሲብ ልምድ (Lesbian) ፡ እንዲያዳብሩ ፡ በማድረግ ፡ እግዚአብሔራዊ ፡ የሆነው ፡ ጋብቻ ፡ እንዲቀር ፡ በማድረግ ፡ ልጆች፡ እንዳይፈጠሩና ፡ የሰው ፡ ቁጥር ፡ ለመቀነስ ፡ የሚደረግ ፡ በውጩ ፡ በጎ ፡ የሚመሥል ፡ ውስጡ ፡ ግን ፡ የጥፋት ፡ ዓላማ፡ ያነገበ ፡ ዘመቻ ፡ ነው።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment