በጣም የሚገርም ዘመን ላይ ደርሰናል፦
ቅዳሜ ሐምሌ ፯፤ ፪ሺ፲ ዓ.ም (ስላሴ + ዓመታዊ የድንግል ማርያም ጽንሰት በዓል) የኤርትራው ፕሬዚደንት በደጉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ታላቅ አቀባበል ሲደረግላቸው፤ የአንግሎ–አሜሪካኑ መሪ ፕሬዚደንት ትራምፕ በእናታቸው አገር በስኮትላንድ ተቃውሞ ብቻ ሳይሆን የግድያ ሙከራም ሳይቀር ታቅዶባቸው ነበር።
ስለዚህ
ታሪካዊ ጉብኝት ምዕራባውያኑ የፌንጣ ድምጽ ከማሰማት በቀር ጸጥ ብለዋል፤ በኮርያዎቹ መካከል ተደርጎ ስለነበረው
የሰላም እንቅስቃሴ ግን በአርዕስት ዜና መልክ ሳምንቱን ሙሉ ሲለፈልፉ ነበር። ትናንትና ፕሬዚደንት ትራምፕ ወደ
እንግሊዝ መሄዳቸው፣ ኤርትራውያን በሚሳተፉበት የፈረንሳይ የብስክሌት ውድድር (ቶር ዴ ፍራንስ) ሰሞንና የፈረንሳይ ብሔራዊ ቀን በሚከበርበት ዕለት ፕሬዚደንት ኢሳያስ ወደ አዲስ አበባ መጓዛቸው እንዲሁም በዛሬው ዕለት ፈረንሳይ የዓለም ዋንጫ ባለቤት ለመሆን መብቃቷ (በአፍሪቃውያን የተደገፈና አረቦችን ያገለለ ቡድን ስላላት)፡ ሁሉም ብዙ ነገሮችን ይጠቁሙናል። ምልክቶችን ማየትና ማሳየት የሚወድ ዓለም ላይ ነንና?
ያም ሆነ ይህ፤ ባሁን ሰዓትም ቢሆን፡ ሉሲፈራውያኑ፡ ከበስተጀርባ፡ ተንኮል ያለበት ዕቅድ ባገራችን ላይ እንዳላቸው ቢታወቅም (በተለይ ሳውዲዎች) በሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ላይ የበላይ ወይም አሸናፊ የሚሆኑበት ዘመን አሁን ያከተመ ይመስላል።
Blogger Comment
Facebook Comment