የእንግሊዙ “ደይሊ ሜይል” ጋዜጣ ትልቅ ውሸት!



ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ

 “ኢትዮጵያውያን ‘ጋኔን ለማስወጣት’ የወር ደሞዛቸውን ለመምህር ግርማ ይከፍላሉ” --ደይሊ ሜይል

በእውነት ምዕራባውያን የኢትዮጵያውያን የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ለመቃወምና ለማጥላላት ቆርጠው ተነስተዋል። አስገራሚው  ነገር እኛው ራሳችን ጳጳስ፣ ዲያቆንና መምህራን ተብለን የመምህር ግርማ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ መቃወማችን ነው፤ ምዕራባውያን ድሮውንም መቃወም ሥራቸው ነበር።

ዲያብሎስ ሲያሽሟጠጥብን ደስ ሊለን ይገባል፤ ምክኒያቱም የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ለማወቅ እንችላለንና።
ይህን ቪዲዮ የሠራሁት የእንግሊዙ “ደይሊ ሜይል” በድህረ ገጹ ላይ ትናንትና ካወጣቸው ፎቶዎች ነው።
እነዚህን የመሳሰሉት ፎቶዎችና ቪዲዮዎች ለእኛ የተለመዱ ናቸው፤ መንፍሳዊ ውጊያ ምን እንደሚመስል በግልጽ የሚታይባቸው ፎቶዎች ናቸው። ለዲያብሎስ አሽሟጣጩና ተከታዮቹ ግን በተቃራኒው ከንቱ ነገር ነው። ዓይኖቻችን የተለያዩ ናቸው!
ይህ ታዋቂ የእንግሊዝ ጋዜጣ አንድ ዳዊት Tesinsky የተባለ ወስላታ የቼክ ሪፓብሊክ ፎቶ አንሺን ወደ መምህር ግርማ ልኮ ምስሎቹን ካገኘ በኋላ በድህረ ገጹ ላይ በጣም ቅጥፍት በተሞላበትና እጅግ በጣም አንቋሻሽ በሆነ መልክ ረጅም ዘገባ አቅርቧል። ኢትዮጵያውያንን፣ ተዋሕዶ ክርስትናን እና መምህር ግርማን እያንቋሸሸ፡ ማለት ነው። እንዴት ፈቀዱለት?!
ዲያብሎስ ቀናተኛው ከጻፋቸው ዓረፍተ ነገሮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፤ ለማሽሟጠጥ ሲሻ ቃላቶቹን በቅንፍ ውስጥ አስቀምጧቸዋል፣ ምንም እንኳን በእንግሊዝኛው በ አንተ‘ እና በ አንቱ‘ ልዩነት ባይኖርም፤ ግን ስለ መምህር ግርማ አንተ‘ በሚል መንፈስ ነው የተጻፈው፦
ርዕሱ፦ “በአንድ የጅምላ የጥምቀት ሥርዓት 150 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን “ጋኔን ለማስወጣት” የወር ደሞዛቸውን ለአንድ ቄስ ይከፍላሉ” የሚል ነው።
  • + ተወዳጅ የጊዜ ማሳለፊያ፦ ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ በሚገኝ መንደር (የረር ሥላሴመቶ አምሳ የሚሆኑ ሰዎች “ጋኔን አውጭውን” ዝነኛ ፈዋሽ ቄስ ለማየት መጥተዋል
  • + ቄ የምዕመናኑ ግንባር ላይ መስቀሉን በማሳረፍ ‘ተቀደሰ ውኃ‘/ ጸበል ያርከፈክፍባቸዋል።
  • + ፎቶው፡ በሁሉም የዕድሜ ክልል ያሉ ሰዎች በህውከት ሲያለቅሱ፣ ሲጮኹና ሲፈራገጡ ያሳያል።
  • + ‘የአምላክ ሥራ፦ ጋኔን አውጭው ፈዋሽ ቄስ መምህር ግርማ ወንድሙ የሰውየው ግንባር ላይ መስቀሉን ሲያሳርፉበት በእብደት ሲጮኽ ፎቶው ያሳያል
  • + ሌላው ፎቶ ላይ፡ አንዲት ሴት እየጮኸች ወደ መምህር ግርማ ስትመጣ እና ጎልማሶች ጸበል እየተረጩ ሲያለቅሱ ይታያል።
  • + ብዙ ዝናብ፦ ከ እርኩሳን መናፍስት ነጻ‘ ለመሆን የመጣችው ሴት ላይ የጸበል ፉፏቴ ተለቀቀባት።
  • + የነፃነት ዋጋ፦ እንደሚባለው ከሆነ መምህር ግርማ ጋኔን የሚያወጡት‘ ተፈዋሾቹ የአንድ ወር ደሞዛቸውን ሲከፍሏቸው ነው።
  • + የዘመናዊ መድኃኒትን መቀበል የማይችሉት ኢትዮጵያውያን የወር ደሞዛቸውን ከፍለው “ጋኔን ያስወጣሉ”።
ቀጣፊው ቼክ ፎቶ አንሺ ይህን ብሏል፦
መምህር ግርማ በእዚህ ቦታ የበለጠ ገንዘብ ስለሚያገኝ በሌሎች ዓብያተክርስቲያናት ለማገልገል አሻፈረኝ ብሏል፤ እንዲያውም የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከምታገኘው ገንዘብ በላይ ያገኛል።”
አቤት ቅጥፈትአቤት ተንኮልአቤት ጥላቻያሰኛል። ግን በድጋሚ ደስ ይበለን። እግዚአብሔር በራሱ መንገድ የራሱን ፎቶዎች ያነሳል።
[የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፰፥ ፵፬]
እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።
እኔ እስከማውቀው ድረስ፡ መምህር ግርማ በየረር ሥላሴ የሚሰጡትን ታታሪ የሆነ መንፈሳዊ አገልግሎት ካቆሙ ቆይተዋል፤ ታዲያ ይህ የእንግሊዝ ጋዜጣ ስለ እርሳቸው አሁን ለመናገር የወሰነው ከምን የተነሳ ነውከማንስ ጋር በመተባበርኃይሌ ገ/ሥላሴ (የረር ሥላሴይኖርበት ይሆንእነ አንዳርጋቸውስ?
የእንግሊዝ ሜዲያ ይህን የመሰለ ተንኮልና ጥላቻ በእንግሊዝ፣ በደካማው የአንግሊካን ቸርቻቸው እና በጨካኙ የንጉሣውያን ቤተሰብ ላይ ተንፍሶ አያውቅም፤ ፀረክርስትና ዘመቻው ግን ያው በመጧጧፍ ላይ ነው። ከሃዲዎች!
ሊሲፈራውያኑ የአንግሎአሜሪካውያኑ ስውር የዓለማችን መሪዎች የመፍንቅለ መንግስት በኢትዮጵያ አደረጉ፤ ያዘጋጇቸውን ሰዎች ሥልጣን ላይ አስቀመጡ፣ ቢቢሲ በኢትዮጵያ ቋንቋዎች አገልግሎት ጀመረ፣ እነ አንዳርጋቸውን እንዲለቀቁ ወተወቱ፣ ክትባት እየወጉ ያሳደጓቸውን እነ ኃይሌ ገ/ሥላሴን ፀረተዋሕዶ የሆነ ነገር እንዲናገሩ አዘዟቸው፣ የኦጋዴን ነዳጅ እንዲወጣ ተፈቀደ፣ የኢትዮጵያ ግድብ ኬኒያ ልጃቸውን እንደሚጎዳ ተዘገበ፣ ደቡብ ኢትዮጵያውያን የብጥብጥ እሳት እንዲፈጥሩ ተቆሰቆሱ፣ 666ቷ ሮቦት ሶፊያ ወደ ኢትዮጵያ ተላከች።
እኅተ ማርያም ትክክል ናት “አቤት እንግሊዝ ጉዷ” ስትለን። በትናንትናው ዕለትም ሰሬ ወረዳ እና ጋትዊክ አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ በድጋሚ ተሰምቶ ነበርታይቶ የማይታወቅ ኃይለኛ የአየር ሙቀት በመላው አውሮፓ አለ፣ የድርቅ ዘመን እየመጣባቸው ነው ፣ የእስልምና እና የግብረሰዶም መቅሰፍት ያመጣባቸው መዓትማ ተዘርዝሮ አያልቅም።
መምህር ግርማ፡ እንኳን ገንዘብ ሊቀበሉ ይቅርና፡ በተማሪዎቻቸው በሚዋጣው ገንዘብ የተለያዩ አብያተ ክርስትያናት ያሣነጹ ሲሆን፡ በተጨማሪም የተለያዩ ደጋፊ የሌላቸው፡ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፡ በተደጋጋሚ ሲረዱ አይተናል። ሳናይ ሳናጠና መፍረድ ግን የተጣናወተን በሽታ ነው። ይህንን የውሸት መረጃ ከወጣ በኃላ እንኳን፡ ባለፈው የቅዳሜ ዕለት፡ በመላው ዓለም ካሉ ተማሪዎቻቸው በተውጣጣ ገንዘብ የተለያዩ አብያተ ክርስትያናት ያሣነጹ ሲሆን፡ በተጨማሪም የተለያዩ ደጋፊ የሌላቸው፡ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፡ በተደጋጋሚ ሲረዱ አይተናል። ሳናይ ሳናጠና መፍረድ ግን የተጣናወተን በሽታ ነው። ይህንን የውሸት መረጃ ከወጣ በኃላ እንኳን፡ ባለፈው የቅዳሜ ዕለት፡ በመላው ዓለም ካሉ ተማሪዎቻቸው በተውጣጣ ገንዘብ መልአከ መንክራት መምህር ግርማ መንድሙ በዛሬው እለት 30/10/2010 ብርሃን ታዬ በአለርት ግቢ የሥጋ ደዌ አካል ጉዳተኞች ማህበር በመሄድ የራሳቸውን የበረከት ስራ ( 100 ,000 ብርየአንድ መቶ ሺህ ብር የበረከት ቱሩፋት አድርገዋል በተጨማሪም የማፅናናትና የማበረታታት የሞራል ድጋፍ አድርገዋል

በክርስቶስ ሰላም ሀገራችን ኢትዮጵያ የጀመረችው የስላምና የእርቅ እንዲሁም የአንድነት ስሜት እንዲቀጥል ተግተን ልንፀልይ ያስፈልጋል አንዱ ላንዱ ጠላቱ አንዱ ላንዱ አሳዳጁ ከሚሆን በፍቅር በጋራ በመተሳሰብ ያለምንበት ቦታ ላይ መድረስ እንችላለን በማለት ተናግረዋል እንዲሁም ማህበሩ የመጀመርያው እኛን ሊጎበኙ የመጡ አባት በማለት የምስጋና ምስክር ውረቀት እና አረጋውያኑ የሰሩትን ጋቢ አልብሰዋቸዋል

ሰኞ ሓምሌ 2, 2010 ዓ.ም.
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment