ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ አውታር ከሳምንታት በፊት “ሶፍያ” የተሰኝት የኢሉሚናቲ ሴራ አስፈጻሚ ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ እንደምትመጣ ገልጸን ነበር። አሁን ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከዐቢይ አሕመድ ጋር ተገናኝታለች።
ለጠቅላይ ሚኒስትሩም “ኢትዮጵያ በመምጣቴ በጣም ደስ ብሎኛል፤ እኔ ኢትዮጵያን የምወድ
ሮቦት ነኝ” ብላቸዋለች።
ከመጣች አራተኛ ቀኗን ያስቆጠረችው ሶፊያ በቆይታዋ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተሰናዳው
ዓለም አቀፍ አይ ሲቲ ኤክስፖ ላይ ተገኝታ ከታዳሚያን ጋር ተዋውቃለች።
ባለስልጣናት፣ የጃዝ ሙዚቃ አባት ሙላቱ አስታጥቄን ጨምሮ የኪነጥበብ ባለሙያዎች በተገኙበት
በቶቶት የባህል አዳራሽ የዳንስ ትርዒትም አቅርባለች።
ምንም እንኳን በጀርመን በርሊን ኤክስፖ ቆይታዋ የተወሰነ የአካል ክፍሏን የያዘ ሻንጣ
መጥፋት አማርኛ መናገር እንዳትችል የተፈታተናት ቢሆንም በትንሹም ቢሆን ተናግራለች።
“ከዚህ የበለጠ አማርኛ ስለምድ እናወራለን” ስትል ተናግራለች። ንግግሯ ጠቅላይ ሚንስትሩን
ፈገግ ያሰኘ ነበር ።
ታድያ ኢትዮጵያውያን የዚች ሮቦት ምስጥር የገባቸው አይመስልም፤ ቴክኖሎጂው ሲያደንቁና
ሲያሞግሱ ይታያሉ ይደመጣሉ። ቴክኖሎጂ፡ የሰው ልጅን ኑሮ ካቀለለበት መንገድ ይልቅ፡ ያወሳሰበበትና ምስቅልቅሉን ያወጣበት ሁኔታ
ይበልጣል።
ግብዞች በእግዚአብሔር አፈጣጠር እና ፍጥረታት ላይ እያመጹ ነው፤ እራሳቸውን አምላክ ለማድረግ ይሻሉ። በትንቢተ ዳንኤል እና በ ዮሐንስ ራዕይ
መጻሕፍት ላይ ሁሉም ነገር ተብራርቶ ይነበባል። አሁን ብዙ እየትወራለት ያለው የሰው ሠራሽ አዕምሯዊ ጥናት ዘመቻ የፀረ–ክርስቶሱና የአውሬው መንፈስ የቀሰቀሰው ዘመቻ እንደሆነ ምንም አያጠራጥርም።
ተራቅቀናል የሚሉት አመጸኞቹ ሰዎች አሁን ሮቦቶችን እየሠሩ ቀስ በቀስ እንደ እግዚአብሔር እንዲመለኩ ማድረግ ይጀምራሉ።
ባለፈው ዓመት፡ “ሶፍያ” የተሰኘች “ሴት” ሮቦት በሳውዲ አረቢያ ተወዳጅነት ማትረፏና ከሁሉ አገሮች ቀድማ የሳውዲ አረቢያን ዜግነት ለመጀመሪያ ጊዜ ማግኘቷ፡ የፀረ–ክርስቶሱ ኃይል በምዕራባውያኑ ኤዶማውያን ቴክኖሎጂና በእስማኤላውያኑ ዶላር ድጋፍ በመላው ዓለም እንደሚሠራጭ ይጠቁመናል። ሆንግ ኮንግ የተሠራችው “ሶፊያ” በሳውዲ አረቢያ በ፮፮፮ቱ መንፈስ ከተጠመቀች በኋላ፡ ወደ ተመረጡ አገሮች ተጓዘች።
“ሶፊያ” ከመሠራቷ ከአምስት ዓመታት በፊት ቅሌታሙ ባለ ኃብት አሜሪካዊ፡ ሕፃናት ደፋሪው፡ ‘ጀፍሪ ኤፕሽታይን‘ የሚደግፈው የሰው ሠራሽ አዕምሯዊ ጥናቶችን ማካሄጃ ተቋም በኢትዮጵያ ተምሠረተ፤
(በአዲስ አበባ ‘ሉሲ‘ አጠገብ) ፤ እዚያም ‘አበበ‘
የተባለ እግር ኳስ ተጫዋች ሮቦት ተሠራ፤ ከዚያ በኋላ ሮቦት “ሶፊያ” ተሠራች፤ ከሳምንት በፊት ሮቦት “ሶፊያ”ን ወደ ኢትዮጵያ እንድትመጣ የጋበዛት ይህ ተቋም ነው። (አዳም እና ሔዋን መሆናቸው ነው)
የዚህ ተቋም ኃላፊ የሆነው ሊቅ ጌትነት አሰፋ የሚከተለውን ከንቱ ዓረፍተ ነገር ተናግሯል፦
“በመጪዎቹ አሥር ወይም ሃያ አመታት ውስጥ የሰው ልጅ የሚባል አይኖርም፤ በማሽን ወይም በሮቦት ይተካል”
“I
don’t think Homo sapiens-type people will exist in 10 or 20 years’ time.”
ይህን ዲያብሎሳዊ ህልምና ዕቅድ በሥራ ላይ ለማዋል፡ ሰኔ ፪ሺ፲ ዓ።ም፡ “ሶፊያ ወደ ኢትዮጵያ እንድትጓዝ ታዘዘች፣ የባህል ልብሳችንን አለበሷት፣ ቋንቋችንን ተናገረች፣ ሰንደቅ ዓላማችን ላይ ካረፈው የሉሲፈር አምስት መዓዘናዊ ኮከበ እና ከዶ፨ር አብይ ጋር አብራ እንድትታይ ተደረገች። ጎልቶ የሚታየው ኮከቡ ነው፦
[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፲፫፥፲፭]
“የአውሬው ምስል ሊናገር እንኳ ለአውሬውም ምስል የማይሰግዱለትን ሁሉ ሊያስገድላቸው፥
ለአውሬው ምስል ትንፋሽ እንዲሰጠው ተሰጠው።”
ሰኞ ሰኔ 25, 2010 ዓ.ም.
Blogger Comment
Facebook Comment