የእመቤታችን አሥራት አገር ኢትዮጵያ፡ መሠረቷ ክርስቶስ ነው!
ወገኖች መንግስቱን ዘረኛ ነው እያሉ፡ “ነፃነት ባለበት” ውጭ አገር እንኳን ሳይቀር በጎሣ ተከፋፍለዋል። አይገርምም! ከተዋሕዶ ትግሬ መሪ ሙስሊም ኦሮሞ መሪ የተመረጠበት ግዜ ላይ ደርሰናል፤ ሆይሆይ የሚለውን ሰው ብዛት ስናይ፡ ለስላሳው ፀረ-ክርስቶስ ጨረቃዋን መጎተት ሲጀምር ምን ያህል ተከታይ እንደሚኖረው መገመት አያዳግተንም። የሚፈለገው ይህ ነው፤ አላማውም ያ ነው።
ሰው በኢትዮጵያ መሠረት ላይ (ትግራይ ነው የሚገኘው) ጥላቻ እንዲኖረው በማድረግ መሬት መንቀጥቀጥ መፍጠር መቻል፡ ነው አላማው። በዚህም መልክ በተዋሕዶ ሃይማኖት አማኙ ህዝብ መካከል ልዩነትን ለመፍጠር ሙከራ ተደርጓል። ላለፉት ሺህ ዓመታት ጦርነቱ፣ ረሃቡና በሽታው ሁሉ ይከሰት የነበረው በወሎ ላሊበላ አካባቢ እና በትግራይ ነው። በዱሮ ጊዜ ጣዖት አምላኪዎችን (ራያ) ወደ ሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል አምጥተው አስፈሩ፤ በኋላ ላይ ደግሞ የደርግ መንግስት ትግርኛ ተናጋሪ ክርስቲያኖችን ከትግራይ በማፈናቀል በደቡቡ ኢትዮጵያ ለማስፈርና ትግራይን ከተዋሕዶ ለማጽዳት ሞክሯል። “Problem – Reaction – Solution” ብሎታል፡ ተንኮለኛው ፈላስፋ ሄገል።
ልክ በአይሁዶች በኩል የእስራኤልን መሠረት ለመነቅነቅ እንደሚሞክሩት፡ አሁን በአገራችንም በትግሬዎች በኩል የኢትዮጵያን መሠረት ነቅንቀው ለማፍረስ እየታገሉ ነው። ይህ ቁልጭ ብሎ እየታየ ነው።
Blogger Comment
Facebook Comment