ምነው ጃል፡ ክብራችን የት ሄደ ፧ ኢትዮጵያውያን ፡ በሴት ግብረሰዶማውያን (Lesbian) ሠርግ ታድመው አድማቂ ሆነዋል!



ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ

https://www.youtube.com/watch?v=P3ewxTd7H1M&feature=youtu.be

 መጽሐፍ ቅዱስ በኦሪት ዘፍጥረት መጽሐፍ ስለ ግብረ ሰዶማዊነት ይናገራል፡፡ የሰዶምና የገሞራ ሰዎች ግብረ ሰዶማውያን ነበሩ፡፡ ሰዶምና ገሞራ በዮርዳኖስ ሸለቆ የተቆረቆሩ ከተሞች ነበሩ፡፡ በእነዚህ ሁለት ከተሞች ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ግብረ ሰዶማውያን ማለትም ወንድ ከወንድ፣ ሴት ከሴት ጋር ዝሙት የሚያደርጒ ይህ ኃጢአትም በእነርሱ ይበዛ ስለነበር ስያሜው የቦታውን ስም በመያዝ ግብረ ሰዶም ተባለ፡፡ በዘመናት ሁሉ ይህን ኃጢአት የሚሠሩ መጠሪያ ሆኖ አገለገለ፡፡ ዛሬም በግብር የሚመስሉአቸው ሰዎች ግብረ ሰዶማዊ ወይም ሰዶማውያን እየተባሉ ይጠሩበታል፡፡ የሰዶምና የገሞራ ሰዎች ወንድ ከወንድ፣ ሴት ከሴት ጋር የሚፈጽሙት ዝሙት አጸያፊ ስለነበር እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ወሰነ፡፡ (ዘፍ. 18÷20፣ ዘፍ.19÷5-9)፡፡ ሁለት መላእክትን ወደ ሰዶም ላከ፡፡ ሁለቱ መላእክት የእግዚአብሔር ሰው እና ከሰዶማዊነት ግብር ንጹሕ የነበረውን ሎጥን ከከተማው እንዲወጡ ካደረጉ በኋላ እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን በእሳትና በዲን አጠፋ፡፡ (ዘፍ.19÷10-26) ሰዶምና ገሞራ አሁን በጨው ባሕር እንደተሸፈኑ የሥነ ምድር ተመራማሪዎች ይናገራሉ፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ ሰዶምና ገሞራ የክፋት ሁሉ የፍርድም ምሳሌ በመሆን ተጠቅሰዋል፦
[ኢሳ. 1÷9-10፣ ኢሳ. 3÷9፣ ኤር. 23÷14፣ ሰ.ኤ.4÷6፡፣ ሕዝ. 16፡46፣ ማቴ.10÷15፣ ራእ. 11÷8]
መጽሐፍ ቅዱስ ግብረ ሰዶማዊነት ነውር እና አጸያፊ እንደሆነ ይመሰክራል
[ዘሌ. 30÷13] [ዘፍ. 13÷13] [ይሁዳ. ቁ. 7] [ሮሜ. 1÷24-27] [ቆሮ. 6÷9-10] [ዘሌ 20: 13]
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment