ላለፉት ዓመታት ሕዝበ ክርስቲያን በየቀኑ በሚታረዱባት ሰሜናዊው ናይጄርያ፡ የአዳማዋ አውራጃንወክላ የህዝብ ተወካይ የሆነችው፡ ቢንታን ማሲ ጋባ፡ ህይወቷን ለኢየሱስ ክርስቶስ በመስጠቷ ምክንያት አባቷ ንብረቷን ሁሉ እንዳቃጣለባት ተናግራለች። የ 50 ዓመት የልደት ቀኗን ለማክበርበተዘጋጀው የምስጋና አገልግሎት ላይ ነበር እንባ እያፈሰሰች ይህን የተናገረቸው። ከእግዚአብሔር ጋር፥ የጥላቻን፣ የፍቅር እጦትንና ተቀባይነት የማጣትን ፈተናዎች አሸንፌአቸዋለሁ።
አዳማ = አዳማዋ፤ ቢሾፍቱ = ቢሾፍቱዋ
በአገራችንም ተመሳሳይ ሁኔታ እየተፈጠረ መሆኑን፤ ክርስቶስን በመካድ ወደ ሰዶምና ገሞራ መለወጡን የመረጡት የናዝሬት እና ደብረ ዘይት ከተሞች እያሳዩን ነው።
እግዚአብሔር በነፃነት እንኖር ዘንድ ይጠራናል፦
እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው ፍፁም ነፃነትን ሰጥቶ ነው። ነገር ግን ሰው ነፃነቱን አላግባብ በመጠቀሙ የኃጢአት ባሪያ ሆነ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ዋጋ ከፍሎ ደግሞ ነፃነትን ሰጠን። “በነፃነት ልንኖር ክርስቶስ ነፃ አወጣን” [ገላ. ፭፥፩]። ዛሬ ላይ ደግሞ ለኃጢአት፣ ለሥጋ ፈቃድ፣ ለኑፋቄ፣ ለባዕድ አምልኮ፣ ለዘረኝነት እና ለክህደት እንዳንገዛ በነፃነት እንኖር ዘንድ አምላካችን ይጠራናል። “ወንድሞቼ ሆይ፥ እናንተስ ለነፃነት ተጠርታችኋል፤” [ገላ. ፭፥፲፫
]
Blogger Comment
Facebook Comment