"እርዳታ ሰጪ ነኝ" የሚለው እንግሊዛዊው ድርጅት ኦክስፋም/ Oxfam በአገሮቻችን
ሲፈጽም የነበረው ስውር ተግባሩ አሁን እየተጋለጠበት ነው። በጣም የሚደንቅ ነው፤ በሄይቲ ደሴት አሳፋሪ የሆኑ
ወሲባዊ ድርጊቶችን ሲፈጽም የነበረው የኦክስፋም ሠራተኛ በዚህ ቅሌት ከሥራው ከተባረረ ከጥቂት ቀናት በኋላ ወደ
ኢትዮጵያ ተልኮ ህፃናቶቻችንን እንዲተናኮል በር ተከፍቶለት ነበር። ከጥቂት ሳምንታት በፊት ኡጋንዳዊቷ የኦክስፋም
ዋና አስተዳዳሪ ከስልጣኗ እንድትወርድ ተገዳ ነበር።
ሉሲፈራውያኑ አገሮቻችንን ለመተናኮል የእኛኑ ሰዎች ስልጣን ላይ ያስቀምጣሉ፦
ልክ ኡጋንዳዊቷን ወ/ሮ ዊኒ ቢያኒያምን የኦክስፋም መሪ (የዊኒ ማንዴላን ስም ይዛለች) አድርገው እንደሾሟት፤ ሊቀ ጳጳሳት ዴስሞንድ ቱቱን ልዩ አምባሳደር አድርገው እንደመረጧቸው፤ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖምን የአለም ጤና ድርጅት ሃላፊ አድርገው መሾማቸው ያለምክኒያት እንደማይሆን መጠራጠር ግድ ነው። በሮበርት ሙጋቤን በመምረጥ ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ሊያስተዋውቋቸው ሞክረው ነበር። እነዚህ አረመኔዎች የአለማችን ገዢዎች ዓላማቸው የህዝብ ቁጥር ቅነሳ፡ በተለይ የክርስቲያን ህዝብ ቅነሳ፡ መሆኑን እያየነው ነው።
የህዝባችንን
ቁጥር ለመቀነስ፡ ውሃችን፣ አየራችንንና ምግቦቻችንን ለዘመናት ሲበክሉ ቆይተዋል፤ አሁን ደግሞ ወሊድ
መከላከያዎችን፣ ህፃናት ማስወረጃ ቅመሞችን እንዲሁም በሽታዎችን ይዘው መጥተውብናል። በማደጋስካርና ምስራቅ አፍሪቃ
በቅርቡ ተቀስቅሶ የነበረው “ወረርሽኝ በሽታ” ያቀዱለትን
ያህል ጥፋት አላመጣላቸውም።
በዚህ ሳምንት “ኢቦላ” እንደገና ተመልሶ መጥቷል ተብሏል። በመጪዎቹ ዓመታት በአገሮቻችን የተለያዩ ህይወት ቀጣፊ
የበሽታ ዓይነቶችን በላብራቶሪ እየቀመሙ ወደ አገሮቻችን ያስገባሉ፤ ይህ አሁን ድብቅ ነገር ሊሆንብን አይችልም። ለዚህም ዲያብሎሳዊ ተግባራቸው የእኛኑ ሰዎች መርጠው የኃላፊነት” ቦታዎች ላይ ያስቀምጣሉ። የግብጹን ቦትሮስ ጋሊን እና ጋናውን ኮፊ አናንን የተባበሩት መንግስታት ዋና \ጸሐፊዎች አድርገው በመረጧቸው ማግስት ነበር ኤርትራ ከእናቷ የተገነጠለችው፣ የባደሜ ጦርነት የተቀሰቀሰው፣ የሩዋንዳ፣ የሱዳን እና እስካሁን ድረስ የቀጠለው የኮንጎ እልቂቶች የተከሰቱት።
በመጨረሻ ለዚህ ሁሉ ዕልቂት ተጠያቂዎቹ እኛው እራሳችን እንደሆንን ከሳሹ ሰይጣን ባሽሙር ይነግረናል።
ባራክ ሁሴን ኦባማን ከመረጡት በኋላ ነበር “ጥቁሮች” እና ክርስቲያኖች ለአስከፊ ዘረኝነትና ለከፍተኛ እልቂት የተጋለጡት። ጋቦን፣ ናይጀሪያና ደቡብ አፍሪቃን ያልተባበሩት መንግሥታት ጸጥታው ምክር ቤት አባል እንዲሆኑ በመረጧቸው ማግስት ነበር ኮሎኔል ቀጣፊን የገደሏቸውና ሊብያንም የሙስሊም ሽብር ፈጣሪዎችና የ”ሂጂራ” ስደተኞች መናኽሪያ ለመሆን ያበቋት። ሁሉም በአጋጣሚ አይደለም።
ወስላታው ኦባማ በአሜሪካ ላይ ያመጣውን መዘዝ አሁን የምናየው ነው፤ ትናንትና የወጣ አንድ መረጃ እንደሚናገረው 62% የሚሆኑት ወይም 96ሚሊየን
የሚደርሱት አሜሪካውያን ስራ አጦች ወይም ስራ ፈላጊዎች ናቸው። በአፍጋኒስታን ብቻ የሚከሰከሰው ብዙ ትሪሊየን
ዶላር እነዚህ አሜሪካውያንን ለሺህ ዓመት ሊቀልብ የሚችል ነበር። ኦባማ ለአሜሪካ የተላከ መቅሰፍት ነው። ተጠያቂ
የሚሆኑት ግን የርሱን ቆዳ ቀለም የተቀቡት ጥቁሮች ናቸው፤ “ውሻውን መጥፎ ስም ሰጥተህ ግደለው!“ እንዲሉ።
ሉሲፈራውያኑ ጊዚያቸው እያለቀ ነው፡ ወደ እሳት መወርወሪያቸው ተቃርቧል!
Blogger Comment
Facebook Comment