“አፍሪካ፡ ከአጋም የተጠጋ ቁልቓል…”


አንዱ ከአንዱ እየተጠጋ አንዱ የአንዱ ደጋፊ እየሆነ፡ በዓለም ህዝብ ላይ በሽታና ባሩድ ሲያቃጥል እየታዘቡ፡ ከመመልከት በቀር በህግ አምላክ ቁጥራችንን ለመቀነስ ስትሉ በፈጠራችሁት “የኢቦላ በሽታ” አትግደሉኝ፡ ብላ በክትባትም በታብሌትም የሚላክባትን የሞት መልዓክተኛ አትድረስብኝ ለማለት አልቻለችም አፍሪካ !!!

ቀድሞውኑ የአሜሪካ ምክር ቤት (ኮንግረስ) ለአሜሪካ መከላከያ ሚኒስተር “ፔንታጎን” በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ሲሰጥኖ የኬሲንጀር ጥናት ዘመንም ዘመን እየተሻገረ ሲገድል እንዲኖር በጥናቱ ላይ የአሜሪካ መንግስት ማህተሙን አትሞበት፡ የትኛው የአፍሪካ ሀገር ሊያስቆመው ይችላል፡ እስኪባል ድረስ የጥፋት ስራውን አሁንም ድረስ እያከናወነ ይገኛል::

አፍሪካ “ከአጋም የተጠጋ ቁልቓል…” ሆና እንደጅረት የሚፈስባትን የልጆችዋን ሞት መመልከት እንጂ ሞት ለሞት አምራቾች ለማለት የምታሰማው ድምፅና የምትዘረጋው ክንድ ከወዴት ታመጠለች ? እግዚአብሔር ካልረዳት በስተቅር !

እነ “ዳዊት ሮክፊለር” የተበተቡት የጥፋት ልቃቂት እየሆነ የሕዝብን ቁጥር ይቀንሳል እንጂ፡ ውሉ ተገኝቶ ቋጠሮውም ተፈቶ “የሦስተኛውን ዓለም” ህዝብ ከሞት ነፃ ሊያወጣው እንዴትስ ይቻለው ይሆን ? የኛዎቹ ለሆዳቸው ያደሩ “ዶክተር” ተብየዎች የምዕራባውያንን የሞት ድግስ አስተናጋጅ ሆኖው አረፉት። “የዓለም የጤና ድርጅት” የመሪነት ስልጣን ለኢትዮጵያዊው ቴዎድሮስ አድሃኖም የሰጡት ሊጠቀሙበት ነው። ራሳቸው በሽታ አምርተው ራሳቸው ተቆርቋሪ መስለው መቅረብ ተክኖውበታል።
በጥቁር ሕዝቦች ላይ ያነጣጠረው ‘ኢቦላ’ እንደገና አገርሽቷል | ዶ/ር ቴዎድሮስን ያለምክኒያት መርጠዋቸዋልን?

አረመኔዎቹ የምዕራቡ ዓለም “ሊቃውንት” እና ባለ ሃብቶች፡ አፍሪቃውያኑን እርስ በርስ በጦርነት ከማባላት አልፈው የአፍሪቃን ሕዝብ ቁጥር ለመቀነስ ኢቦላን፣ ኤች አይ ቪንና የመሳሰሉትን ቫይረሶች ላብራቶሪ ውስጥ ቀምመው እንዳሰራጯቸው ነው።

በዚህ ሳምንት ላይ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የኢቦላ ቫይረስ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች።
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኢቦላ ቫይረስ እንደገና አገርሸቷል። ነገር ግን በሽታው መቼ እና እንዴት በድጋሚ ሊከሰት እንደቻለ የሚታወቅ ነገር የለም፤ ሁሉም ነገር “ድብቅ” ነው።
የተጋረጠውን አደጋ እንዴት መከላከል ይቻል ይሆን?

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሰሜን ምዕራብ አካባቢ የምትገኘው ቢኮሮ ከተማ የታየው የቫይረሱ ማገርሸት ከዚህ ቀድሞ የተከሰተውንና በምዕራብ አፍሪካ አስራ አንድ ሺህ ሰዎች ህይወት መቀጠፍን እንዲሁም ሃያ ስምንት ሺህ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙበትን አስደንጋጭና አስፈሪ ጊዜ ያስታውሰናል።
ትናንትና ሚሊየን ሰው በሚኖርባት የኮንጎ ከተማ ቫይረሱ መዛመቱ ተወስቷል።
ልክ በዚህ ሰሞን ከዓመት በፊት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን የአለም ጤና ድርጅት ሃላፊ አርገው መሾማቸው በአፍሪቃውያን ላይ ያዘጋጁት ተንኮል ስላለ ነው። ለምሳሌ፡ የ ዶ/ር ዴዎድሮስን መመረጥ ቶሎ ብለው ካወደሱት ቡድኖች መካከል ለህጋዊ ፅንስ የማስወረድ መብት ጠበቃ የቆሙ ድርጅቶች ይገኙበታል።

ይህን መረጃ እንመልከት፦
http://www.lifenews.com/…/pro-abortion-groups-celebrate-ne…/

በሌላ በኩል፡ አውሮፕላኖች እንደ ኢቦላ የመሳሰሉ ቫይረሶችን በፈጠነ መልክ ለማሰራጨት አስተዋጽኦ ያበረክታሉ የሚለውን መረጃ ሳነብ፡ የታየኝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው። ሁሌ የምጠይቀው፡ ከጥንት ጀምሮ፣ በማንኛውም የኢትዮጵያ መንግስታዊ መስተዳደር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያለምንም ተንኮልና መሰናክል እንዲያድግና እንዲስፋፋ መደረጉ ከምን የመጣ ይሆን? የሚለው ጥያቄ ነው።

ይህን መረጃ እንመልከት፦

https://www.nytimes.com/2017/05/23/health/tedros-world-health-organization-director-general.html

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment