ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
የዓለማችን
፡ የፊልም ተመልካች ፡ብዙ ያነጋገረው ፡ ብላክ ፓንተር ፊልም ፡ ክርስትያናዊ ፊልም እንዳልሆነ ፡ አውቃለው። በማርቫል ከተደረሱት
ፊልሞች አንዱ የሆነው ፡ ይህ ፊልም በርከት ካለው የፊልሙ ይዘቶች ፡ ጥቂት ነገሮች ትኩሬቴን
ስቦታል። ይህም ደራሲው ፡ የፊልሙ መሠረት ያደረገው ፡ የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ማንነት ላይ መሆኑ ነው። ማርቫል ይህ ድርሰት ሲጽፍ “ኢትዮጵያ/ዩቶጵያ” [ዋካንዳ በሚል ቀይሮታል} በምናቡ እያሰበ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለዉም።
በዚህ
ጽሑፍ ፡ የማካፍላቹ ጥቂት ነገሮች ፡ ደራሲው ከኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ ፡ የወሰደው ነው እኛምን ያስተምራሉ ብየ ያመንኩባቸው ፫ ነገሮች
ናቸው።
፩፡ ለማንነታችን ዘብ መቆም ፡ እንደሚገባን ፦
ከእግዚአብሔር
የሆነው ኢትዮጵያዊነት ፡ በአሁኑ ወቅት በምዕራባውያንና ፡ በኢትዮጵያውያን የውስጥ የፖለቲካ ጠላቶች ሴራ ፡ በትውልዱ ዘንድ እንዳይታወቅና እንዲጠፋ እየተደረገ በመሆኑ ፡ ኢትዮጵያዊነት በፖለቲካ አተያይ እንጂ ፡ በእውነተኛ ማንነቱ እንዳይታወቅ ሆኗል።
ቲቻላ
፡ በፊልሙ ያለ ፡ ልብወለዳዊ ገጸ ባህሪ ነው። በፊልሙ እንደሚታየው ፡ ቲቻላ ምናባዊ የሆነችውን “ዋካንዳን” ምናባዊ በሆኑ ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም ፡ ከጠላቶች ይጠብቃታል። እኛም ፡ ቴክኖሎጂው በጥቂቱም ቢሆን አስተዋጽኦ እንዳለው ብናውቅም ፡ እውነተኛው የአባቶቻችን መንፈስ በመላበስ ፡ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ከተዘጋጀላት የምዕራባውያንና የውስጥ ጠላቶች የጥፋት ድግስ ፡ በአቅማችን ልንከላከላቸው እንደሚገባ ፊልሙ ያስተምረናል።
፪፡ ኢትዮጵያን ፡ መጠበቅ እንደሚገባን፦
ምናባዊትዋ
“ዋካንዳ” ደህንነትዋ በተጠበቀ ሁኔታ ፡ ከዓለም
ተሰውራ ትገኛለች። ይህ የሆነበትም ምክንያትም ከሌላው ዓለም ልዩ የሚያደርጋት ቴክኖሎጂና ውድ የሆኑ መዓድናት ስላልዋት ከስግብግቦች ለመጠበቅ ነው። ኢትዮጵያም ተዋህዶ ሃይማኖት መሠረቱ የሆነ ፡ ቅርሶችና
የተፈጥሮች ስጦታዎች አልዋት። ይህ በሚገባ የሚያውቁ ምዕራባውያን ፡ ወደ ኢትዮጵያ በተለያዩ መንገድ በመግባት ፡ ቅርሶችዋንና ተፈጥራዊ
የእግዚአብሔር ስጦታዎች የሆኑ ነገሮች ፡በመዝረፍ ወደ ሃገራችን በተለያየ መንገድ እየወሰዱ ነው። ይህ ማስቆም ደግሞ የኛ ድርሻ
መሆኑ ፡ ከብላክ ፓንተር ፊልም መማር እንችላለን።
፫፡ ኢትዮጵያዊ ማንነታችንን ሊነጥቀን የሚፈልግ ኃይል እንዳለ ማወቅ እንደሚገባን ፦
የቲቻላ
የአጎት ልጅ የሆነው ፡ ኤሪክ እጅግ ክፉ ሰው ነበር። የዋካንዳ የንግሥና ዙፋን ለማግኝት ፡ በከፍተኛ ሁኔታ ትግል ሲያደርግ ይታያል። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ፡ ከኛ በላይ በሚባል መልኩ የተገነዘቡ ፡ የጨለማው ገዢ አገልጋዮች ምዕራባውያን የምስጥር ማኅበራት ፡ ኢትዮጵያን በመንፈሳዊ ኃይል እየተዋጓት መሆኑ ፡ መገንዘብ እንዳለብን ያስተምረናል።
ቅዳሜ
ግንቦት 18,2010 ዓ.ም
Blogger Comment
Facebook Comment