ባለቤቱን ካልፈሩ፡ አጥሩን አይነቀንቁ | እነ ኦባማ የሰፉት የግብረሰዶም መለያ ባንዲራ በአዲስ አበባ




አቤት ተንኮል! አቤት ድፍረት! አቤት ንቀት!


ኦባማ ምንም ሳይሠራ የኖቤልን የሰላም ሽልማት ከኢ-አማንያውያኑ ስካንዲኔቪያኖች ያገኘው ያው ግብረ ሰዶማዊነት በአፍሪካ መናገሻ አዲስ አበባ ለማራመድ እንዲችል ማበረታቻ መሆኑ ነው። 2015 ዓ.ም ላይ አዲስ አበባ ለጉብኝት ሲገባ ሰማይ ላይ ወጥታ የነበረችው የማርያም መቀነቷ እንደ ኃይለኛ ማስጠንቀቂያ ትታያለች።

የፊንላንድና ዴንማርክ ኤምባሲዎች የሰዶማውያኑን ባንዲራ መስቀላቸው፡ ከአባታችን ኖህ ያገኘንውን፣ እንዲሁም እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያሰረችልንን የማርያም መቀነት በድፍረት ለማርካስና ሰንደቅ ዓላማችንንም ለማጥቆር ሲሉ ነው። መጀመሪያ ላይ ባለ አምስት ማዕዘኑን ኮከብ......አዎ! እንቁላል ቀስ በቀስ በእግሩ ይሄዳልና።
አዲስ አበባ ከአፍሪካ ህብረት ጀርባ አውሮፓ ህብረት ቢሮ ላይም ተመሳሳይ የግብረሰዶም መለያ ባንዲራ በይፋ ተሰቅሎ ይታይ ነበር።

ለመሆኑ እነዚህ ኢምባሲዎችና ድርጅቶች ለዓደዋ መታሰቢያ በዓል ዕለት የኢትዮጵያን ሰንደቃላማ ለመስቀል ፈቃደኞች ናቸውን? ወይም የኢትዮጵያ ኢምባሲ በዋሽንክግተን ወይም በለንደን የፀረ-ዘረኝነትን ባንዲራ ቢያውለበልቡ ዝም ይሏቸዋልን፡ በጭራሽ! ባለፈው ዓመት አሜሪካ የሚገኙ የሩሲያ ቆንስላቶች ባንዲራዎቻቸው በግድ እንዲነሱ ተደርጎባቸው።
አሁን በመላው ዓለም በግልጽ እየደፈሩ መውጣት ጀምረዋል። ግድየለም፤ ይታዩን፤ እንያቸው! ለዓለማችን፡ በተለይ ለክርስቲያን ኢትዮጵያ የተላኩት ሁለት ኃይለኛ መቅሰፍቶች ግብረ-ሰዶማዊነት እና እስልምና መሆናቸውን አሁን ማየት እየተቻለን ነው። ሁለቱም እጅግ በጣም አስቃቂ የሆኑ ድርጊቶችን በመላው ዓለም እየፈጸሙ ነው። ሁለቱም ከዲያብሎስ የተላኩና አንድ አምላክ ያላቸው ናቸው። ሁለቱም የአዳምን ዘር መንፈስ ለማድከም ዲያብሎስ የሚጠቀምባቸው መሣሪያዎች ናቸው። ለዚህም ነው ለአንድ ዓላማ እርስበርስ ተመሳጥረው ዲያብሎሳዊ ስራ የሚሠሩት። እስማኤል + ዔሳው።

መጽሐፍ ቅዱስ በኦሪት ዘፍጥረት መጽሐፍ ስለ ግብረ ሰዶማዊነት ይናገራል፡፡ የሰዶምና የገሞራ ሰዎች ግብረ ሰዶማውያን ነበሩ፡፡ ሰዶምና ገሞራ በዮርዳኖስ ሸለቆ የተቆረቆሩ ከተሞች ነበሩ፡፡ በእነዚህ ሁለት ከተሞች ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ግብረ ሰዶማውያን ማለትም ወንድ ከወንድ፣ ሴት ከሴት ጋር ዝሙት የሚያደርጒ ይህ ኃጢአትም በእነርሱ ይበዛ ስለነበር ስያሜው የቦታውን ስም በመያዝ ግብረ ሰዶም ተባለ፡፡ በዘመናት ሁሉ ይህን ኃጢአት የሚሠሩ መጠሪያ ሆኖ አገለገለ፡፡ ዛሬም በግብር የሚመስሉአቸው ሰዎች ግብረ ሰዶማዊ ወይም ሰዶማውያን እየተባሉ ይጠሩበታል፡፡ የሰዶምና የገሞራ ሰዎች ወንድ ከወንድ፣ ሴት ከሴት ጋር የሚፈጽሙት ዝሙት አጸያፊ ስለነበር እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ወሰነ፡፡ (ዘፍ. 18÷20፣ ዘፍ.19÷5-9)፡፡ ሁለት መላእክትን ወደ ሰዶም ላከ፡፡ ሁለቱ መላእ ክት የእግዚአብሔር ሰው እና ከሰዶማዊነት ግብር ንጹሕ የነበረውን ሎጥን ከከተማው እንዲወጡ ካደረጉ በኋላ እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን በእሳትና በዲን አጠፋ፡፡ (ዘፍ.19÷10-26) ሰዶምና ገሞራ አሁን በጨው ባሕር እንደተሸፈኑ የሥነ ምድር ተመራማሪዎች ይናገራሉ፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ ሰዶምና ገሞራ የክፋት ሁሉ የፍርድም ምሳሌ በመሆን ተጠቅሰዋል፦
[ኢሳ. 1÷9-10፣ ኢሳ. 3÷9፣ ኤር. 23÷14፣ ሰ.ኤ.4÷6፡፣ ሕዝ. 16፡46፣ ማቴ.10÷15፣ ራእ. 11÷8]
መጽሐፍ ቅዱስ ግብረ ሰዶማዊነት ነውር እና አጸያፊ እንደሆነ ይመሰክራል፦
[ዘሌ. 30÷13] [ዘፍ. 13÷13] [ይሁዳ. ቁ. 7] [ሮሜ. 1÷24-27] [ቆሮ. 6÷9-10] [ዘሌ 20: 13]
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment