የጌታ ስቅለት | በዚያን ዕለት የከርስቶስ ልጆች ክርስቲያን፤ የፀረ-ክርስቶሱ እስላም ተባሉ


ከመጽሐፈ ጸሎት የተወሰደ
ሕማማተ መስቀል
ጌታም ቆላተ ዮሳፍጭ ከሚባል በረሀ አውርዶ መናውን ውሀውን ከወትሮ አብልጦ አወረደላቸውና ኃይሉን ከሂሎቱን አሳይቶ ወእንዘ ዓዲ መብልዖሙ ውስተ አፋሆሙ ነዘር እባብ አስንቶ ጐዳናቸውን እየስቀደደ አስፈጃቸው። ሙሴም አቤቱ ጌታዬ አሕዛብ ፳ኤልን የሚመግባቸው ቢያጣ ከበረሀ አውርዶ አስፈጃቸው እንዳይሉህ መድኃኒት ፈልግላቸው ብሎ ጸለየ። ጌታም የወዳጁን ጸሎት ፈጥኖ ይሰማልና ብርቱን እባብ አስመስለህ በተራራ ላይ ተራዳ ተክለህ ብርቱን በዚያ ላይ ሰቅለህ አሳያቸው ያን አይቶ ሰምቶ ያመነ ይዳን ያላመነ ይፈጸም አለው። ተራራው በቀራንዮ አምሳል ነው፤ ተራዳው የመስቀል ብርቱ የወልደ እግዚአብሔር እባብ የዲያብሎስ ቍስሉ የኃጢአት መርዙ የመርገመ ሥጋ የመርገመ ነፍስ በረኃው የገሃነም እሳት አምሳል ነው።
ያን አይተው ሰምተው ይዳኑ ማለት ስቅለተ ክርስቶስን አይተው ያመኑ ሐዋርያት፣ ሰምተው ያመኑ ምዕመናን የመዳናቸው አምሳል ነው። ያላመኑ ይፈጸሙ ማለቱ፡ ስቅለተ ክርስቶስን አይተው ያላመኑ አይሁድ ሰምተው ያላመኑ አይሁድ፣ ሰምተው ያላመኑ አሕዛብ ያለመዳናቸው አምሳል ነው።
ነፍስ ያለው እባብ የገደላቸውን ሰዎች ነፍስ የሌለው ብርት እንዳዳናቸው በባሕርዩ ሞት የሌለበት አምላክ ዲያብሎስ ያስገራቸውን ነፍሳት ተሰቅሎ ሞቶ የማዳኑ አምሳል ነው።
ጽዮን የተባለች ማኅፀነ ማርያም ደብረ መቅደሱ የተባለ አካሏ ነው
ጌታም እነዚያ አላወቁም እንጂ እኔስ በማኅፀነ ማርያም አድሬ ለጻድቃን ለሰማዕታት ነገሥሁላቸው በአይሁድ በመናፍቃን ነገሥሁባቸው ሲል ነው። አንድም ጽዮን የተባለ መሰቀሉ ደብረ መቅደሱ የተባለ አካሉ ነው
እነዚያ አላወቁም እንጂ እኔስ በመስቀል ተሰቅዬ ለጻድቃን ለሰማዕታት ነገሥሁላቸው በአይሁድ
በመናፍቃን ነገሥሁባቸው ሲል ነው እንዲህ ፯ት ተአምራት ሲሠሩ አይተው የባሕርይ አምላክ ነው እንጂ የባሕርይ አምላክማ ካልሆነ እንዲህ ያሉ ተአምራት ባልተሠሩ ነበር ያሉ ክርስቲያን ተባሉ።
አምላክ አይደለም፣ አልተወለደም፣ አልተሰቀለም፤ የአምላክ ወዳጅ ደግ ሰው ነብይ ብቻ እንጂ ያሉት እስላም ተባሉ። እስላምና ክርስቲያን የተባለበት ያን ዕለት ነው።
አይሁድ ግን አላክም ነብይም አይደለም ሐሳዌ መሲሕ ነው ከቄሣር በቀር ሌላ ንጉሥ የለም ብለው ካዱት።
መናፍቃን ካህናት አላውያን መኳንንት ከሀድያን ነገሥታት ሃይማኖታችሁን ጣሉ ፈጣሪያችሁን ካዱ ለጣኦት ስገዱ ብለው እንደ እኔ እራሳችሁን እየመቱ አክሊለ ሦክ ግንድ አሸክመው በብረት ቢቸነክሯችሁ መራር ሐሞት ቢያጠጧችሁ ዋጋችሁን በመንግሥት ተቀበሉት እንጂ ሃይማኖታችሁን አትጣሉ፤ ፈጣሪያችሁን አትካዱ፤ ለጣኦት አትስገዱ!” በማለት ጌታችን አስተምሮናል
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment